በቅርቡ አሜሪካ የሚኖሩት ወገኖቻችን በተባበረ ጥረታቸው ለብዙ ጊዜ ሲዋጉለት የነበረውንና የኢትዮጵያን መንግሥት ቢያንስ ቢያንስ ወደ ተከላካይነት ሊያወርደው ይችላል ተብሎ የታመነበት የአሜሪካ ኮንግረስ ውሳኔ በአደባባይ ለመላው ዓለም ሲታወጅ የተሰማን ደስታ ወሰን አልነበረውም። እኛ የአንጋፋው ትውልድ፣ ከሩቅ ሆነን ሲመቸን ብቻ “በርቱ” እያልን “ድጋፍ” ስንሰጣቸው የነበርነውን ይህን ያህል ያስደስተን፣ በቦታው ሆነው ሌት ተቀን ሳይታክቱ ከስቴት ወደ ስቴት እየተደዋወሉ በተወካዮቻቸው የኮንግረስ አባላት ዘንድ በመደወልና በመጻፍ ተጽዕኖ እያሳደሩ በመጨረሻ ላይ የለፉለት ግቡን ሲመታ ምንኛ እንደተደሰቱ ገምቼ እኔም በጣም ተደሰትኩላቸው። ብዙዎቹ እንደነገሩኝ ከሆነ፣ ያን ቀን በጥዋት ተነስተው ወደ ካፒቶል በማምራት፣ አሰልቺውን የጸጥታ ምርመራ በትዕግሥት አልፈው ወደ ኮንግሬስ ተወካዮቻቸው ቢሮ … [Read more...] about ኤች አር 128 ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የኛ ሚና
hr 128
ያልታሰበው H. Res. 128 ውሳኔ እና የህወሃት መብረክረክ
ያልታሰበ ነው። ፈጽሞ ያልተገመተ። አገዛዙን እንደ ቀትር መብረቅ ያስደነገጠ ውሳኔ። በጸረ-ሽብር ስም በሚተውኑት የፖለቲካ ድራማ ሳብያ አሜሪካ ይህን አይነት ውሳኔ አጋር በሆነ አካል ላይ ትፈጽማለች ብለው ለአፍታ እንኳን አስበውት አያውቁም። በዚያ ላይ ደግሞ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈላቸው ሎቢስቶች ጉዳዩን ይዘውልናል ብለው ተዘናግተዋል። “ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ዕድል እንስጥ” የሚለው የኦክሎሃማው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ ሃሳብ ያሸንፋል የሚል ግምትም ነበራቸው። ንቀታቸው እና ትዕቢታቸው የት እንደደረሰ የተመለከትነው፤ ሰነዱ ምክር ቤት ሊቀርብ ቀናት ሲቀረው እንኳ ዜጎችን ከእኩይ ተግባራቸው ያልመቆጠባቸው ነው። በሽብር የወነጀሏቸውን የዋልድባ መነኮሳት አሁንም እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። ሰነዱ ሊጸድቅ አንዲት ቀን ሲቀረው በምስራቅ ሀረርጌ፤ ቆቦ ከተማ ነፍሰጡርዋን በጥይት … [Read more...] about ያልታሰበው H. Res. 128 ውሳኔ እና የህወሃት መብረክረክ
H.R. 128 ያለ ተቃውሞ አልፏል!
የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን ዓቀፍ መንግሥት በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ለማስቻል በአሜሪካ የእንደራሴዎች ምክርቤት የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ያለአንዳች ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ኤፕሪል 10፤2018ዓም ጸድቋል። ህወሓት እጅግ ከፍተኛ የውትወታ ገንዘብ ያፈሰሰበትና በርካታ የፖለቲካ ሥራ የሠራበት ረቂቅ በምክርቤቱ በሚገኙ 108 እንደራሴዎች ስፖንሰር ያደረጉት ሲሆን የሁለቱም ማለትም የዴሞክራትና የሪፑብሊካን እንደራሴዎች በጣምራነት የደገፉት ረቂቅ ነበር። በዋሽንግቶን ዲሲ በ“አምባሳደርነት” ሹመት የኢህአዴግ ተወካይ ሆኖ የተቀመጠው ካሣ ተክለብርሃን ለምክርቤቱ ረቂቅ ሕጉ እንዳይፀድቅ ደብዳቤ ልኮ እንደነበር H.R. 128 ለኢትዮጵያ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባተመው የደብዳቤው ፎቶ አስታውቋል። በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ያደረጉት እንቅስቃሴ አንዱ የድሉ አካል እንደሆነ … [Read more...] about H.R. 128 ያለ ተቃውሞ አልፏል!
የHR 128 እና የማግኒትስኪ ሕግ ትሥሥር፤ የህወሓት ፍርሃቻ!
ተጨማሪ መረጃ፤ ያለፈው ሳምንት መገባደጃ አካባቢ የኮሎራዶ 6ኛው ወረዳ እንደራሴ ማይክ ኮፍማን በድረገጻቸው እንዳስታወቁት HR 128 በኤፕሪል ወር ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት ድምጽ ይቀርባል ብለዋል። ጉዳዩን ከሚከታተሉ በርካታ ወገኖች መካከል የቅርብ መረጃ ያላቸው አቶ ኦባንግ ሜቶ የቀጠሮው ቀን ኤፕሪል 9 (ሚያዚያ 1) መሆኑን በፌስቡክ ገጻቸው በለቀቁት መረጃ አስታውቀዋል። ይህ ረቂቅ ጸድቆ በሕግ እንዲወጣ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ የሚገኘውን የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግብረኃይል ፌስቡክ ገጽ በመሄድ ለረቂቅ ሕጉ እንዴት ድጋፍ መስጠት እንደሚቻል የበለጠ መረጃ ማግኘት ይቻላል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለፈው “ህወሓት፡ የHR 128 ፍርሃቻ እና የማግኒትስኪ ሕግ” የሚለውን ዘገባ በድጋሚ አቅርበናል። ይህ ዘገባ ህወሓት ለምን ረቂቅ ሕጉን እንደፈራውና እጅግ በርካታ ገንዘብ በማፍሰስ ለማጨናገፍ … [Read more...] about የHR 128 እና የማግኒትስኪ ሕግ ትሥሥር፤ የህወሓት ፍርሃቻ!
“የክርስቲያን አገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሡባት ነው” ህወሓት ለአሜሪካ እንደራሴዎች
የአስራ ሰባት ታዋቂ ኦሮሞ ሙስሊሞችን ስም ለማስረጃነት አቅርቧል ከዝርዝሩ ውስጥ የዶ/ር አቢይ አህመድ ስም ይገኝበታል ህወሓት ከፊቱ የተጋረጠበትን የፖለቲካ ቀውስና ቀውሱን ተከትሎ ከጌቶቹ የተነሳበትን ተቃውሞና ግፊት አቅጣጫ ለማስቀየር ሃይማኖትን የተንተራሰ ስልት ተግባራዊ ማድረጉ ተሰማ። የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አገሪቱን ለእስልምና አክራሪ አሳልፎ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ህወሓት በወኪሉ በኩል ስም ዘርዝሮ አቅርቧል። የጎልጉል ዲፕሎማት የመረጃ አቀባዮች ከዋሽንግቶን ዲሲ እንዳስታወቁት ህወሓት አሁን የተነሳበትን ዙሪያ ገጠም ተቃውሞ ከእስልምና አክራሪነት ጋር በማቆራኘት የአስራ ሰባት ኦሮሞ ሙስሊም ታዋቂ ፖለቲከኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ ወዘተ ስም ዘርዝሮ ነው ያቀረበው። ዙሪያው ገደል የሆነበት ህወሓት የስም ዝርዝሩን ባቀረበ ጊዜ ራሱን የክርስቲያን መንግሥት አድርጎ … [Read more...] about “የክርስቲያን አገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሡባት ነው” ህወሓት ለአሜሪካ እንደራሴዎች
Ethiopian Regime’s Misinformation Campaign On H. Res 128
FOR IMMEDIATE RELEASE Ethiopian Advocacy Network (EAN) and Ethiopian American Civic Council (EACC) would like to bring to our people’s attention a misinformation campaign aimed at thwarting the momentum of our efforts to pass H. Res 128 in the US House of representatives. It has come to our attention a high level misinformation campaign which has the hand print of the tyrannical regime in Addis is circulating false rumors to distract our people including. Deadline is postponed till … [Read more...] about Ethiopian Regime’s Misinformation Campaign On H. Res 128
ህወሓት፡ የHR 128 ፍርሃቻ እና የማግኒትስኪ ሕግ
ከዚህ በፊት በአሜሪካ ምክርቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በረቂቅ ሕግነት ከቀረቡት መካከል ህወሓት/ኢህአዴግ HR 128 እጅግ ፈርቶታል። ይህንን ረቂቅ ሕግ ለማክሸፍም የውትወታ (ሎቢ) ሥራ ከመሥራት ጀምሮ የአሜሪካ ባለሥልጣናትንና የፖለቲካ መሪዎችን በ“አልሻባብ ምስራቅ አፍሪካን ይወራል” ድራማ ለማስፈራራት ተደጋጋሚ በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም። ላለፉት በርካታ ወራትም (በቅርቡ ወደ አሜሪካ የመጡትን እነ ወርቅነህን ጨምሮ) ሊያሳምኑ ይችላሉ የሚላቸውን ሹሞቹን በመላክ ረቂቅ ሕጉ በተግባር እንዳይውል የአሜሪካ ባለሥልጣናትንን - ጊዜ ስጡን፣ ሁሉን እናስተካክላለን፣ … የመሳሰሉ ተማጽንዖዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በግምባር ቀደምትነትም የህወሓት ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ ኢትዮጵያ ድረስ እስኪሄዱ ያደረሰ የውትወታ ሥራ ተካሄዷል። ይህንን ረቂቅ … [Read more...] about ህወሓት፡ የHR 128 ፍርሃቻ እና የማግኒትስኪ ሕግ
ሕዝባዊ ጽናትና የHR 128 ጡንቻ “እስረኞች”ን አስፈቱ
አገሪቱን ከሁሉም አቅጣጫዎች ለዓመታት ሲያናውጥ የቆየው ሕዝባዊ ዓመጽ ከHR 128 ጋር ተዳምሮበት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባው ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እያለ በግፍ ያሰራቸውን እየፈታ ነው። የተፈቱት ተመልሰው ላለመታሰራቸው ምንም ዋስትና የለም ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚዳንትነቱን መንበር ከተረከቡ ጊዜ ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) የተባለው አሸባሪ የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን ስሉሱ እንደዞረበት አስተውሎ የራሱን ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። በጣም ይተማመንባቸው የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎች” ህወሓት መናፈቅ የጀመረው ኦባማ የሥልጣን መንበሩን በሚያስረክቡበት የመጨረሻ ዓመት መገባደጃ ላይ ነበር። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ October 3, 2017 ባቀረበው የዜና ዘገባ ላይ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይህንን ማለቱ ይታወሳል፤ ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመናቸውን … [Read more...] about ሕዝባዊ ጽናትና የHR 128 ጡንቻ “እስረኞች”ን አስፈቱ