• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ያልታሰበው H. Res. 128 ውሳኔ እና የህወሃት መብረክረክ

April 11, 2018 06:21 am by Editor 1 Comment

ያልታሰበ ነው። ፈጽሞ ያልተገመተ። አገዛዙን እንደ ቀትር መብረቅ ያስደነገጠ ውሳኔ። በጸረ-ሽብር ስም በሚተውኑት የፖለቲካ ድራማ ሳብያ አሜሪካ ይህን አይነት ውሳኔ አጋር በሆነ አካል ላይ ትፈጽማለች ብለው ለአፍታ እንኳን አስበውት አያውቁም። በዚያ ላይ ደግሞ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈላቸው ሎቢስቶች ጉዳዩን ይዘውልናል ብለው ተዘናግተዋል። “ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ዕድል እንስጥ” የሚለው የኦክሎሃማው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ ሃሳብ ያሸንፋል የሚል ግምትም ነበራቸው። ንቀታቸው እና ትዕቢታቸው የት እንደደረሰ የተመለከትነው፤ ሰነዱ ምክር ቤት ሊቀርብ ቀናት ሲቀረው እንኳ ዜጎችን ከእኩይ ተግባራቸው ያልመቆጠባቸው ነው። በሽብር የወነጀሏቸውን የዋልድባ መነኮሳት አሁንም እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። ሰነዱ ሊጸድቅ አንዲት ቀን ሲቀረው በምስራቅ ሀረርጌ፤ ቆቦ ከተማ ነፍሰጡርዋን በጥይት ደበደቧት። በመጀመርያ አስገድደው ደፈሯት። ከዚያ ገደሏት።

ለሰብዓዊ ክብር የቆመ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደርን የሚደግፍ ሰነድ፤ ውሳኔ H.Res 128። በዩናይትድ ስቴይትስ ምክር ቤት ፊት ቀርቦ ያለ አንዳች ተቃውሞ ጸድቋል። ይህ አስደንጋጭ ውሳኔ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነትን ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ይመስላል።

ይህ ሰነድ አያሌ መሰናክሎችን አልፎ ለውሳኔ በቀረበበት ቅጽበት አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን፤ ለአሜሪካ ኮንግረስ አንድ የተማጽኖ ደብዳቤ ልከው ነበር። እኚህ ሰው ከተለመደው የጸረ-ሽብር ማስፈራረያ ወጣ ብለው፤ መንግስታቸው ለለውጥ እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት ተናግረዋል። በነገሩ ላይ በግልጽ ለመምከር፤ ለጋራ ውይይትም ጋብዘዋል። “ውሳኔ ከማስተላለፍ ተቆጠቡ” ብለው የሕግ መምሪያ ምክር ቤቱን ቢጠይቁም፤ ጅብ ካለፈ… ሆነና አልተሳካም።

“በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ይቁም፤ ለሁሉም እኩል የሆነች ኢትዮጵያ እውን ትሁን!” የሚል ሰነድ ማውጣት፤ ከፋቱ ምኑ ላይ እንደሆነ የሚረዱት የአገዛዙ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። ይሁን እንጂ “አልሻባብ ምስራቅ አፍሪካን ይወርራታል” የሚለው የዘወትር የህወሃት ነጠላ ዜማ አሁን ስለተበላ ጨዋታቸውን የቀየሩ ይመስላል።

የእነ ስብሃት ነጋ “አይጋ ፎረም”፤ እንደ ደብተራ ክታብ በቀይ እና በጥቁር ቀለም አሸብርቆ አሜሪካን መሳደብ ጀምሯል። ውሳኔው አስገዳጅ ያልሆነ እና ተፈጻሚነትም እንደማይኖረው አይጋ ነግሮናል። በዚህ አላበቃም። በሃገር ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ ሲልም የአሜሪካ ኤምባሲን ያስጠነቅቃል። የአሜሪካው አምባሳደር በኢትዮጵያ የጀመሩትን “የብተና ተልዕኮ” አስመልክቶ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ ጠንካራ መልዕክት እንዲያስተላልፉም ያሳስባል።

የነ አባይ ጸሃይ “ትግራይ ኦንላይን” ድረ-ገጽም፤ የተለመደው የኒዮ ሊብራል ትርክት ይዞ ታላቋ አሜሪካን ለመሳደብ አፉን ከፍቷል። የሰብአዊ መብቱን ጉዳይ ሳይሆን የቻይና ጣልቃ ገብነት አሜሪካን እንዳላስደሰተ ሊነግረን ሞክሯል።

የወያኔ ብሎገሮችም ዝም አላሉም። የአንዳንዶቹ ሃሳብ እንደ ፔንዱለም መዋዠቁ ግን የተስፋ መቁረጡ እና የፍርሃቱን መጠን ይገልጸዋል። አንዱ ብሎገር “ውሳኔውን የሀዘን መግለጫ ነገር ነው። ለዛ ነው ድምጽ ራሱ ያልተሰጠበት።” ሲል ጽፏል።

“የሃዘን መግለጫ” ያሉት ይህ ውሳኔ እንዳያልፍ ከ80 ሚልዮን ብር በላይ ለምን እንዳወጡበት ግን ሊነግረን አይደፍርም። ውሳኔው “ምንም አያመጣም” ካሉን ታዲያ አሁን ሲጸድቅ ለምን ብርክ ያዛቸው?

ይህ ሰነድ ውሳኔ ሊሰጥበት የነበረው ባለፈው አመት ኦክቶበር 2/2017 ነበር። በወቅቱ በገጠመው የታሰበ እክል እንዲራዘም ተደረገ። የተራዘመበት ምክንያትም ግልጽ ነው። “ይህ ሕግ ካለፈ ከአሜሪካ ጋራ የሚኖረን ጸረ-ሽብርተኝነትን ድጋፍ እናቆማለን” በማለት የወያኔ መንግስት በይፋ ተናግሮ ነበር። ምክንያቱን ልብ በሉ! በንግድ ልውውጥ አይደለም። በባህልና ቱሪዝም ጉዳዮችም አይደለም። በጸረ-ሽብር ላይ አብሬ አልሰራም ነው ያሉት። የአሜሪካን ጦርነት የኢትዮጵያ ልጆች እንዲወጡት፤ ሁለቱ አካላት በፊት ለፊት ሳይሆን በጓሮ በር የተፈራረሙትን ሰነድ እንቀድደዋለን ሲሉ ነበር ያስፈራሩት። አንድ የአሜሪካ ዜጋ በሶማሊያ ምድር ላይ ከሚሞት ብለው፤ አንድ ሺህ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስንገብር ነበር።

ሰነዱ እንዲሞት አገዛዙ ከፍተኛ የማባበል (ሎቢ) እና የማስፈራራት ስራ አየሰራ እንደነበር የተከበሩ እንደራሴ ማይክ ኮፍማን ተናግረዋል። ሾልኮ የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመን አገዛዙ ይህን ለሚሰሩ ሎቢስቶች በወር 150ሺህ ዶላር ይከፍላል። ይህ ረቂቅ እዚህ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ ሃገሪቱ ካላት ውስን የውጭ ምንዛሪ 1.8 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏል። እየገደሉ መኖርን መብታቸው ካላደረጉት በስተቀር ይህንን ያህል ገንዘብ ለባዕድ ደላሎች ከማዋል ይልቅ በገንዘቡ በርካታ ትምህርት ቤቶችን እና ክሊኒኮችን ይገነቡበት ነበር።

“በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ክብር የቆመ ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር”፤ በማለት የሚጀምረው ይህ ሰነድ በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉትን የመብት ጥሰቶችና በደሎች ያወግዛል። የአገዛዙ አካል ከልክ ያለፈ ሃይል መጠቀም እንዲያቆም። በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተካሄደው ግድያ እና ስቃይ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ገዳዮቹ/አስገዳዮቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚሉ ጫና ሊፈጥሩ የሚችሉ ጠንካራ ድንጋጌዎችን ይዟል። ድንጋጌዎቹ ተፈጻሚ ካልሆኑ የሚወሰዱ እርምጃዎችም በአፈጻጸሙ ላይ ተገልጸዋል።

አሜሪካ እና አውሮፓውያን ላለፉት ሶስት አስርተ-ዓመታት ለራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም ሲሉ፤ የኢትዮጵያ ችግር ችላ ብለው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። የኢትዮጵያ ችግር አሁን ካለበት ጫፍ ደርሶ፤ ስርዓቱ ህዝባዊ እንቢተኝነት መንገዳገድ ሲጀምር የአሜሪካ የፖሊሲ ማሻሻል ለማድረግ መሞከርዋ፤ እንደተለመደው ሃይል ሚዛኑን ተከትሎ ቢሆንም አሁንም አልረፈደም። ህወሃት ሕዝባዊ መሰረት የሌለው፤ በመሳርያ ሃይል ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀመጠ ደካማ ድርጅት ነው። የአሜሪካ የገንዘብ እና ወታደራዊ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ እስካሁን በስልጣን ላይ ሊቆይ እንደማይችል ሁሉም ይገነዘባል።

በአሜሪካ ሳንባ የሚተነፍሱት የአውሮፓ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ከዚህ በኋላ ዝምታቸውን ይሰብራሉ። የዚህን ሰነድ መጽደቅ ተከትለው ለጋሽ ሃገሮች ተመሳሳይ እርምጃ በወያኔ ላይ መውሰዳቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ከአመታዊ በጀቱ አንድ ሶስተኛው ገንዘብ የሚመጣው ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት ነው። የሰራዊቱን እና የደህንነቱን ደሞዝ እየፈሉ ያኖሩት ሃይሎች ፊታቸውን ሲያዞሩበት በኒዮ-ሪበራል ዜማ አሲዮ ቤሌማን ቢዘፍን አይደንቀንም።

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: chris smith, Ethiopia, h res 128, hr 128, Left Column, sgr, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    April 11, 2018 10:52 pm at 10:52 pm

    ቂቂቂ!!! እናያለን ውጤቱን!!! ሞተናላ!!! ጨበርባሪዎች!!! ብርሃኑ ነጋ ቦንገር የከተማችን ከንቲባ ይሆናል። ቂቂቂ!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule