ያልታሰበ ነው። ፈጽሞ ያልተገመተ። አገዛዙን እንደ ቀትር መብረቅ ያስደነገጠ ውሳኔ። በጸረ-ሽብር ስም በሚተውኑት የፖለቲካ ድራማ ሳብያ አሜሪካ ይህን አይነት ውሳኔ አጋር በሆነ አካል ላይ ትፈጽማለች ብለው ለአፍታ እንኳን አስበውት አያውቁም። በዚያ ላይ ደግሞ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈላቸው ሎቢስቶች ጉዳዩን ይዘውልናል ብለው ተዘናግተዋል። “ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ዕድል እንስጥ” የሚለው የኦክሎሃማው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ ሃሳብ ያሸንፋል የሚል ግምትም ነበራቸው። ንቀታቸው እና ትዕቢታቸው የት እንደደረሰ የተመለከትነው፤ ሰነዱ ምክር ቤት ሊቀርብ ቀናት ሲቀረው እንኳ ዜጎችን ከእኩይ ተግባራቸው ያልመቆጠባቸው ነው። በሽብር የወነጀሏቸውን የዋልድባ መነኮሳት አሁንም እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። ሰነዱ ሊጸድቅ አንዲት ቀን ሲቀረው በምስራቅ ሀረርጌ፤ ቆቦ ከተማ ነፍሰጡርዋን በጥይት … [Read more...] about ያልታሰበው H. Res. 128 ውሳኔ እና የህወሃት መብረክረክ
sgr
H.R. 128 ያለ ተቃውሞ አልፏል!
የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን ዓቀፍ መንግሥት በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ለማስቻል በአሜሪካ የእንደራሴዎች ምክርቤት የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ያለአንዳች ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ኤፕሪል 10፤2018ዓም ጸድቋል። ህወሓት እጅግ ከፍተኛ የውትወታ ገንዘብ ያፈሰሰበትና በርካታ የፖለቲካ ሥራ የሠራበት ረቂቅ በምክርቤቱ በሚገኙ 108 እንደራሴዎች ስፖንሰር ያደረጉት ሲሆን የሁለቱም ማለትም የዴሞክራትና የሪፑብሊካን እንደራሴዎች በጣምራነት የደገፉት ረቂቅ ነበር። በዋሽንግቶን ዲሲ በ“አምባሳደርነት” ሹመት የኢህአዴግ ተወካይ ሆኖ የተቀመጠው ካሣ ተክለብርሃን ለምክርቤቱ ረቂቅ ሕጉ እንዳይፀድቅ ደብዳቤ ልኮ እንደነበር H.R. 128 ለኢትዮጵያ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባተመው የደብዳቤው ፎቶ አስታውቋል። በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ያደረጉት እንቅስቃሴ አንዱ የድሉ አካል እንደሆነ … [Read more...] about H.R. 128 ያለ ተቃውሞ አልፏል!