• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

H.R. 128 ያለ ተቃውሞ አልፏል!

April 10, 2018 11:08 pm by Editor 2 Comments

የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን ዓቀፍ መንግሥት በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ለማስቻል በአሜሪካ የእንደራሴዎች ምክርቤት የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ያለአንዳች ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ኤፕሪል 10፤2018ዓም ጸድቋል።

ህወሓት እጅግ ከፍተኛ የውትወታ ገንዘብ ያፈሰሰበትና በርካታ የፖለቲካ ሥራ የሠራበት ረቂቅ በምክርቤቱ በሚገኙ 108 እንደራሴዎች ስፖንሰር ያደረጉት ሲሆን የሁለቱም ማለትም የዴሞክራትና የሪፑብሊካን እንደራሴዎች በጣምራነት የደገፉት ረቂቅ ነበር።

በዋሽንግቶን ዲሲ በ“አምባሳደርነት” ሹመት የኢህአዴግ ተወካይ ሆኖ የተቀመጠው ካሣ ተክለብርሃን ለምክርቤቱ ረቂቅ ሕጉ እንዳይፀድቅ ደብዳቤ ልኮ እንደነበር H.R. 128 ለኢትዮጵያ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባተመው የደብዳቤው ፎቶ አስታውቋል።

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ያደረጉት እንቅስቃሴ አንዱ የድሉ አካል እንደሆነ ተነግሯል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከዚህ በፊት ይህንኑ የህወሓት ውትወታ አስመልክቶ ሲዘግብ፤ “ይህንን ረቂቅ ሕግ ለማክሸፍም የውትወታ (ሎቢ) ሥራ ከመሥራት ጀምሮ የአሜሪካ ባለሥልጣናትንና የፖለቲካ መሪዎችን በ“አልሻባብ ምስራቅ አፍሪካን ይወራል” ድራማ ለማስፈራራት ተደጋጋሚ በርካታ ሙከራዎችን ህወሓት ቢያደርግም አልተሳካለትም። ላለፉት በርካታ ወራትም (በቅርቡ ወደ አሜሪካ የመጡትን እነ ወርቅነህን ጨምሮ) ሊያሳምኑ ይችላሉ የሚላቸውን ሹሞቹን በመላክ ረቂቅ ሕጉ በተግባር እንዳይውል የአሜሪካ ባለሥልጣናትንን – ጊዜ ስጡን፣ ሁሉን እናስተካክላለን፣ … የመሳሰሉ ተማጽንዖዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በግምባር ቀደምትነትም የህወሓት ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ ኢትዮጵያ ድረስ እስኪሄዱ ያደረሰ የውትወታ ሥራ ተካሄዷል።ይህንን ረቂቅ ህግ ገና ከጅምሩ የፈራው ህወሓት ለወትዋቾች (ሎቢይስቶች) በጀት መድቦ መንቀሳቀስ ከጀመረ አንድ ዓመት አልፎታል። በዋሽንግቶን ዲሲ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ተጠሪ የነበረው ግርማ ብሩ SGR Government Relations ከተባለ የወትዋቾች ድርጅት ጋር በተፈራረመው ሰነድ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ለዚህ የውትወታ ሥራ ድርጅቱ (SGR) በወር 150ሺህ ዶላር፤ በጥቅሉ 1.8 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሎት ረቂቅ ሕጉን የማክሸፍ ዘመቻ እንዲሠራ ስምምነት ተደርጓል” በማለት በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል።

ይህ በምክርቤቱ የፀደቀው ሕግ በኢትዮጵያ ያለውን ግድያ፣ ግፍ፣ እስራት፣ ሥቅየት፣ ወዘተ ከመዘርዘር ባሻገር አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ የሚከተሉትን ተግባራት እንዲፈጽም ውሳኔ የተላለፈበት ነው፤

  • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲያነሳ፤
  • የፀጥታ ኃይላት ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀማቸውን እንዲያቆሙ፤
  • በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከመጠን በላይ ኃይል በመጠቀም የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲመረመሩ፤
  • ሕገመንግሥታዊ መብቶቻቸውን በተግባር በማዋላቸው የታሰሩት የፖለቲካ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚዎች፣ … ከእሥር እንዲለቀቁ፤
  • በሰላም የመሰባሰብ መብት እንዲከበር እና የፕሬስ ነጻነት ዋስትና እንዲሰጠው፤
  • የልማት ስትራቴጂውን በተመለከተ ከዜጎች ጋር ግልጽ ውይይት እንዲካሄድ፤
  • የተባበሩት መንግሥታት ራፖርተር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነጻ ምርመራ እንዲያደርግ እንዲፈቀድ፤
  • በሕጋዊነት በተመዘገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን በማዳመጥ መፍትሔ እንዲያገኙ እንዲደረግ፤
  • ሕገመንግሥታዊ መብቶቻቸውን ተጠቅመው ሃሳባቸውን በነጻነት በገለጹ ዜጎች ላይ ግድያ፣ ስቅየት፣ ግፍ፣ ወዘተ የፈጸሙ በሕግ እንዲጠየቁ፤
  • ነሐሴ 28፤ 2008ዓም ቂሊንጦ እስርቤት ላይ በመተኮስና በእሣት በማቃጠል፤ መስከረም 22፤ 2009 በኢሬቻ በዓል ላይ የሞቱትን እንዲሁም በሶማሊያ ክልል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየውን ግድያ አስመልክቶ ምርመራ ተደርጎ ሪፖርት እንዲቀርብ የሚጠይቅ ነው።

ህወሓት/ኢህአዴግ የሚከተለውንና በተግባር አውሎ እየተጠቀመባቸው ያሉትን የአፋኝ ሕግጋት ስብስብ እንዲሰረዙ፤ እነዚህም የጸረ-ሽብር ሕጉ፤ የመያዶች ሕግ፣ ወዘተ የሚጠቀልል ነው።

በመጨረሻም ሕጉ፤

  1. አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ዕርዳታ የውጭ ጉዳይ (ስቴት ዲፓርትመት) መልሶ እንዲያጤነው፤
  2. የአሜሪካ ዓለምአቀፍ የልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ስትራቴጂዎችን እንዲነድፍ፤
  3. ስቴት ዲፓርትመንት ከአሜሪካው ገንዘብ ሚ/ር መ/ቤት ጋር በጥምረት በመሆን በኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ፣ ስቅየት፣ እንግልትና ግፍ የፈጸሙ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በዓለምአቀፍ ደረጃ በሚታወቁ ሕግጋት መሠረት አስፈላጊው ማዕቀብ እንዲጣልባቸውና በኃላፊነት እንዲጠየቁ በግልጽ አስቀምጧል፤

እነዚህንና ሌሎች ጠቃሚ አንቀጾችን ያካተተው ረቂቅ ሲጸድቅ በምክርቤቱ አዳራሽ ተገኝተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን በጭብጨባና በዕልልታ ደስታቸውን ገልጸዋል።

ቀጣዩ ጉዞ ይህ በምክርቤት የጸደቀ ሰነድ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክርቤት (ሴኔት) በመሄድ ድምጽ ይሰጥበትና ካለፈ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፊርማቸውን በማኖር በሕግ መልኩ ወጥቶ ተግባራዊ እንዲደረግ ይታወጃል።

ህወሓት ይህንን ተግባር የሚያስፈጽሙለት እንደነ ሴናተር ኢንሆፍ ያሉ “ወዳጆች” እንዳሉት ሲናገር ቢሰማም ሕጉ አስቀድሞ የበርካታ ሴናተሮች ድጋፍ እንዳገኘ ይነገራል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት 25 ሴናተሮች (18 ከዴሞክራቲክ፤ 7 ከሪፑብሊካን) S.Res.168ን ስፖንሰር አድርገዋል። ኢትዮጵያውንም H.Res. 128 ከጸደቀበት ሰዓት ጀምሮ በሴኔቱ የውሳኔ አሠራር ላይ የተጽዕኖ ሥራቸውን ማካሄድ ጀምረዋል።

(መግቢያ ፎቶ፤ ረቂቅ ሕጉ ያለተቃውሞ ሲያልፍ ሊቀመንበሩ መዶሻቸውን በመምታት ሲያረጋግጡ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, hr 128, kassa, lobby, Middle Column, sgr, sr 168, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    April 11, 2018 10:55 pm at 10:55 pm

    በናንተ ቤት፤ ሁሉም ነገር ተሳክቷል!!! መንግስቲ ግንቦት ሰባት!!! ቂቂቂ!!!ጨበርባሪዎች!!

    Reply
  2. Bekele tessema says

    April 14, 2018 11:11 pm at 11:11 pm

    አገር ወዳድ በጣም ወዳችሁሃለን ሴኔቱ ውሣኔ እንዲሠጥ የነዚ በግፍ የተገደሉት ነጳነት ፈላጊ ኢትዮጵያውያን አምላክ ይርዳችሁ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule