• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሴናተር ኢንሆፍ ህወሓትን የመታደግ ዘመቻ ቀጥሏል!

October 13, 2017 04:00 am by Editor 4 Comments

  • ጉብኝቱ “ከHR 128 … ውጪ ሊሆን አይችልም” ኦባንግ

የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ በአዲስ አበባ ላይ ከኢህአዴግ ሹሞች ጋር መከሩ። አቶ ኦባንግ ሜቶ ጉብኝቱ “ከHR 128 የተያያዘ ነው፤ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም” ይላሉ።

በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት (2017) መጀመሪያ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የነበሩት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ከከፍተኛ የሕወሓት/ኢህአዴግ ሹሞች ጋር መነጋገራቸው ህወሓት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዜና አገልግሎቱ ውይይቱ መቼ እንደተደረገ ባይዘግብም ዜናውን ግን ጥቅምት 2/2010 በማለት ነው ያተተው።

በውይይቱ ላይ ሴናተሩ ሌሎች የአሜሪካ እንደራሴዎችንና የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አባላትን በመምራት እንደተገኙ ዜናው አስታውቋል። የውይይቱ ትኩረትም “በሠላምና ጸጥታ ማስከበር ጉዳዮች ላይ” እንዲሁም “የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ” እንደተካሄደ ተወስቷል።

ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ በውይይቱ ላይ ከወርቅነህ ገበየሁ በተጨማሪ የኃይለማሪያም ምክትል ደመቀ መኮንንና የክልል ኃላፊዎች ሌሎች ሹሞችን ጨምሮ ተገኝተዋል። የክልል ሹሞች በውይይቱ ላይ የመሳተፋቸው ጉዳይ የስብሰባውን አጀንዳ ክብደት የሚያሳይ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በፊት “የአፈጉባዔ ሥልጣኔን ለቅቄአለሁ” ያለው አባዱላ ገመዳ በቀዳሚነት መታየቱ “የለቀቀው ከየት ነው?” አሰኝቷል።

ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት የክልል ኃላፊዎች በውይይቱ ላይ መገኘታቸው የሕጉ መጽደቅ ሁሉንም የአገሪቱን ሕዝብ የሚነካ ጉዳይ ብሎ ለማሳሰብ በህወሓት በኩል የታቀደ “የከሸፈ ስልት” ነው ይላሉ፡፡

ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ “HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!” በሚል ርዕስ ከጥቂት ቀናት በፊት ሲዘግብ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የትራምፕ አስተዳደር “አልሻባብን ለአስር ዓመት ያህል ስንዋጋ ቆይተን ለምንድነው እስካሁን ያላሸነፍነው?” የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱን ዘግቦ ነበር። ይህም አስተዳደሩ ከኦባማ በተለየ መልኩ “አሸባሪነትን መዋጋት” ለሚባለው አጀንዳ ህወሓት/ኢህዴግን እንደ “ስትራቴጂካዊ አጋር” አድርጎ እንደማያየው አመላካች መሆኑን አብሮ በዘገባው ላይ መተንተኑ ይታወሳል።

“የትራምፕ አስተዳደር በአፍሪካ ላይ የተለየ አቋም የመያዙን ሁኔታ ተከትሎ በተለይ ከሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች አስመልክቶ የተቀናበረው HR 128 የህወሓት ሹሞችንና ቤተሰቦቻቸውን ያስጨነቀ መሆኑን ጎልጉል ዘግቦ ነበር። በዚህ ሁሉ መካከል የህወሓት ታዳጊ ሆነው ብቅ ያሉት የኦክላሆማው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ናቸው”።

ይህንን የታዳጊነት ተግባር ለመፈጸም ሴናተር ኢንሆፍ በሰባት ወር ልዩነት በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ አምርተዋል። “HR 128”ን ለማክሸፍ የሚጥሩት ኢንሆፍ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም እንዳሉበት በዚሁ የጎልጉል ዘገባ ላይ ተመልክቶ ነበር።

“ህወሓት ለወትዋቾች (ሎቢይስቶች) በጀት መድቦ መንቀሳቀስ ከጀመረ አስር ወራት ሆኖታል። በዋሽንግቶን ዲሲ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ተጠሪ የሆነው ግርማ ብሩ SGR Government Relations ከተባለ የወትዋቾች ድርጅት ጋር በተፈራረመው ሰነድ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ለዚህ የውትወታ ሥራ ድርጅቱ በወር 150ሺህ ዶላር፤ በጥቅሉ 1.8 ሚሊዮን ዶላር ይከፈለዋል። በርካታ የተቃዋሚ ድርጅቶችና ቡድኖች (በተለይ በዳያስፖራ ያሉቱ) ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ቀሩ እንጂ ሁኔታዎች እንዳላማሩለት የተረዳው ህወሓት የቤት ሥራውን መሥራት የጀመረው አስቀድሞ ነበር”።

የኢንሆፍን ጉብኝት “በሠላምና ጸጥታ ማስከበር ጉዳዮች ላይ” ነበር ቢባልም “HR 128”ን በቅርብ ከሚከታተሉት በቀዳሚነት የሚጠቀሱት አቶ ኦባንግ ሜቶ “ሴናተር ኢንሆፍ ወደ አዲስ አበባ የሄዱት ስለ ረቂቅ ሕጉ ለመነጋገር” ነው በማለት ከጎልጉል ጋር ባደረጉት አጭር የመልዕክት ልውውጥ አስታውቀዋል።

አቶ ኦባንግ እንደሚሉት ከሆነ ይህ ሕግ በህወሓት ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር ብቻ ሳይሆን ለኅልውናውም የሚያሰጋው ጠንካራ ረቂቅ ሕግ በመሆኑ ህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ መሸበር ስለመፍጠሩ መረጃ እንዳላቸው ጠቁመዋል። በተለይም በከፍተኛ የአገዛዙ ባለሥልጣናት ላይ ትልቅ ጫና የሚያስከትል በመሆኑ ሕጉ እንዳይጸድቅ መታገላቸው የሚደንቅ አይደለም በማለት “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ይናገራሉ።

ረቂቅ ሕጉ እንዳጸድቅ ህወሓት በወትዋቾች በኩል ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሆነ የጠቆሙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ከዚህም ሌላ ህወሓት ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ ጋር በአሸባሪነት ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር አልተባበርም ማለቱ የጭንቀታቸውን ልክ የሚያሳይ ነው ይላሉ። “ከዚህ ሁሉ አንጻር ስናየው” ይላሉ ኦባንግ ሜቶ “ህወሓት ጨንቆታል፤ በተፈጥሮው ደግሞ አጥፍቶ ጠፊ ነው፤ ትውልድ አምጾበታል፤ ስለዚህ እንደ ኢንሆፍ ዓይነት ታዳጊ ያስፈልገዋል፤ የሴናተሩም ጉብኝት ይህንኑ የማክሸፍ ሥራ ለመተግበር ነው” በማለት የማስጠንቀቂያ አስተያየት ይሰጣሉ።

“ይህ ረቂቅ ሕግ በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዲከሽፍ መፍቀድ የለብንም፤ ህወሓት በሁላችንም ላይ ጉዳት አድርሷል፤ ስለዚህ እንደ ተጎጂ ልዩነታችንን ወደጎን አድርገን በአንድነት ልንዋጋው ይገባናል፤ በተለይ በአሜሪካ ያለን ኢትዮጵያውያን የምንችለውን ሁሉ ተጽዕኖ ማድረግ አለብን፤ እንደራሴዎቻችንና ሴናተሮቻችንን በማግኘት የዚህን ሕግ መጽደቅ አስፈላጊነት በደንብ ማሳወቅ አለብን፤ ህወሓት ላመነበት ዓላማ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር እየከፈለ እንዴት እኛ ዝም እንላለን?” በማለት ምክር አዘል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሌሎች የረቂቅ ሕጉ ጉዳይ የሚያሳስባቸው ወገኖች “ሁላችንም አንድ የጋራ ጠላት እንዳለን በማመን የተባበረ ክንዳችንን በህወሓት ላይ በማሳረፍ ይህ በህወሓት አንገት ላይ ማነቆ ለማድረግ የተመቻቸ አጋጣሚ ልንጠቀምበት ይገባናል፤ ካልሆነ ግን ይህ ከአስራ አራት ዓመት በኋላ የተፈጠረ ዕድል ይከሽፋል፤ ብዙ ተስፋ የተጣለበት HR128 ፀሐይ ይጠልቅበታል፤ ህወሃትም አፈር ልሶ ይነሳል” በማለት ሥጋታቸውን ይናገራሉ። (ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከዚህ ላይ ነው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Grume T/Mariam says

    October 17, 2017 04:39 am at 4:39 am

    Is it something TPLF working on Aba Dula & Bereket. It is unbelievable there is something prepared by TPLF to resin. I think they prepare to eliminate the opposition or to calm down the people of Ethiopia.

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    October 18, 2017 03:56 am at 3:56 am

    ኣሜሪካ! አሜሪካ! አሜሪካ!!
    ያገር! የሁሉ አገር! ዋርካ!
    አለህ እንዴ በኛ አካባቢ ለካ!!!???
    አንተ በዲሞክራሲ ስትመካ!
    እኛ ለልማት ስናስካካ!
    ትለናለህ የሰው መብት ተነካ!

    ሆድ ሳይሞላ ዲሞክራሲ ብሎ
    ሳይበላ ሳይቆረስ በባዶ ሆድ ተንከባሎ
    ሰልፍ ቢወጣ ዝም ብሎ
    በማግስት ይሆናል ተስተውሎ!???
    አሜሪካ ያገር ዋርካ
    አለህ እንዴ ለካ!???
    እባክህ ሆዳችንን ሞልተን እናስካካ!

    Reply
  3. kedir Nigussie Megersa says

    October 31, 2017 11:34 am at 11:34 am

    keep it up

    Reply
  4. Enyew Damene says

    April 17, 2018 04:59 am at 4:59 am

    የሰው ዶማ በቅርቡ ክርስቶስ ያሰየናል እናምናለን የዚህ የጭቁኑ ሕዝብ እንባው ፈሶ አይቀርም

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule