• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዲሱ የአሜሪካ ምክርቤት ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦች ላይ ጭንቀት ፈጥሯል

July 28, 2017 11:55 am by Editor Leave a Comment

ትላንት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ የፀደቀው ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባልሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ሥጋት፥ ፍርሃትና ጭንቀት መፍጠሩ ተሰማ።

ረቂቅ ሕጉን ገና ከአወጣጡ ጀምሮ ሲከታተሉና ግብዓት ሲሰጡ የቆዩ ወገኖች እንደሚሉት ይህ ያሁኑ ረቂቅ ሕግ የህወሓት ሰዎች አንገት ላይ ገመዱን ያስገባ ነው። ኢትዮጵያውያንን በመግደል፥ በማሰቃየትና በማንኛውም መልኩ የሰብዓዊ መብቶቻቸውን በመርገጥ ስማቸው የሚገኝ የህወሓት ሹሞችና ተባባሪዎቻቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ከገንዘብ ሚ/ር መ/ቤት ጋር በመተባበር በዓለምአቀፍ ሕግጋት በተደነገገው መሠረት ዕቀባ እንዲያደርግባቸው ረቂቅ ሕጉ ያዛል። ይህ ማለት በሌላ አነጋገር ህወሓት/ኢህአዴግ ለዚህ የአሜሪካ የለውጥ ዕቅድ የማይገዛ ከሆነ የህወሓት ሹሞችና ቤተሰቦቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ማዕቀብ ይጣልባቸዋል፥ ሃብታቸው እንዳይነቃነቅ ይደረጋል። የአሜሪካንን ፈለግ የሚከተለውና ከህወሓት ጋር የላላ ወዳጅነት ያለው የአውሮጳ ኅብረትም ተመሳሳይ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ያሁኑ ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ ምክርቤት በሚገኙት ሁለቱም ፓርቲዎች ሙሉ ድጋፍ ያገኘ በመሆኑ ሊታጠፍ እንደማይችልና የወትዋቾች (ሎቢይስቶች) ድለላ የማይበግረው እንደሆነ ተነግሯል።

የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ (July 27, 2017 08:43 pm)

የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን ኮሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ጋር በእኩል ቀርቦ መታየቱ “የአሜሪካና ኢህአዴግ ወዳጅነት ወዴት?” አስብሏል፡፡

መለስ በG-20 ስብሰባ

በዕለቱ ዘጠን አጀንዳዎች ለውሳኔ የቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያን ጉዳይ ጨምሮ የአውሮጳ ህብረት ሒዝቦላን አሸባሪ ድርጅት በማለት እንዲጠራው፤ የሰሜን ኮሪያን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ከዚህ በፊት የወጣው እንደገና እንዲተገበር፤ ኬኒያ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዳታካሂድ፣ በቬኒዙዌላ ያለውን የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ የሚኮንን ረቂቅ ሕግ አቅርቦ ከማስወሰንና ከሌሎች አጀንዳዎች ጋር የቀረበ ነበር፡፡ (የስብሰባውን ሙሉ ውይይትና ውሳኔ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ)

ለምዕራባዊ ጌቶቹ በተለማማጭነትና በታዛዥነት የሚታወቀው መለስ አለቆቹ ያሉትን በመፈጸም አስፈላጊ ሲሆንም ከተጠየቀው በላይ በመሄድ ለመወደድ ያደርግ የነበረውን የአሁኖቹ የህወሓት አመራሮች ሊከውኑት ያልተቻለ ተግባር ሆኖ በተደጋጋሚ የታየ ሆኗል፡፡ በምዕራባዊ አገራት ሎሌነቱን በገሃድ ያስመሰከረው መለስ አገር ውስጥ “አሜሪካ አትረዳንም፤ የሰጡን ኮንዶም ነው፤ ሶማሊያ በኮንዶም አንዋጋም” እያለ በጠብመንጃ የሚገዛው ሕዝብ ላይ ሲደነፋ ቢኖርም ሃቁ ግን ኢህአዴግ አልሻባብን እዋጋለሁ እያለ ሲምታታ የኖረበት ዘመን ማለቁ ነው፡፡

ለዓመታት የህወሓት ቀንደኛ ተቃዋሚ በመሆን የሰላ ትችቶችን በአደባባይ በማድረግ የሚታወቁት የኒው ጀርዚው እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ዛሬም ኢህአዴግን አብጠልጥለውታል፡፡ በኢትዮጵያ “እየደረሱ ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም” በማለት ኢህአዴግም ሆነ ሰሚዎቹ ሊክዱት በማይችሉበት ሁኔታ ማስረጃዎችን እየጠቀሱ ተናግረዋል፡፡

ከኦባማ አስተዳደር የሥልጣን ማብቃት ጋር ተያይዞ በወያኔነት ሲያገለግሉ የቆዩና በአሜሪካ ከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ላይ የነበሩ “ነጭ ወያኔዎች” መልቀቅ ህወሓትን እጅግ በርካታ ገንዘብ የሚያፈስበት የሎቢ (ውትወታ) “ፕሮጀክት” ውስጥ አስገብቶታል፡፡ ይህንኑ ውትወታ አልፎ “H. Res. 128, Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia.” በሚል ርዕስ በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ረቂቅ ሕግ ለህወሓት ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኖ እንሚቀጥልበት ይነገራል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ አሜሪካንን በተደጋጋሚ የጉዞ ማዕቀቧን እንድታነሳ ጠይቆ ፈቃደኛ ሳትሆን መቅረቷ የተቃዋሚው ጎራ አለመተባበርና አለመዘጋጀት ነው እንጂ አሜሪካንን ከኢህአዴግ ጋር ለማቆራረጥ ጊዜው አሁን ነው የሚሉ ወገኖችን አመለካከት ያጎላ ሆኗል፡፡

በኦባማ አስተዳደር ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የነበሩት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ በወቅቱ የተናገሩትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን ዘግቦ ነበር፡፡

ማሊኖውስኪ ይህንን ነበር ያሉት፤ “በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ ሥርዓቱን ለዝነተ ዓለም ለማፅናት በሚደረግ ትግል

ፎቶ: የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊ የUSAID በኢትዮጵያ ሃላፊ ጌይል ስሚዝ (በመኪናው ላይ የሚታየው ምህጻረ ቃል “ማረት” – ማኅበረ ረድኤት ትግራይ) – Photo: David Kahrmann USAID Ethiopia)

ወይንም ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሚወሰድ እርምጃም ሊሆን አይገባም፤ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሥልጣን ማስረከብ ደረጃ ሊደረስ ይችላል፡፡” ሲቀጥሉም “እንደ ወዳጅ መክረናል … ምክንያቱም … ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ቢፈጠር ሙሉ ምስራቅ አፍሪቃ ምን ሊከተል እንደሚችል ስለምናውቅ … ነው” ካሉ በኋላ አገሪቱን እሳት ላይ ተቀምጦ እንደሚንተከተክ ማሰሮ የመሰሉትና ማስሮው እንዳይገነፍል ብቸኛው አማራጭ ክዳኑን መክፈት እንደሆነ ያመለክቱት ቶም ማሊኖውስኪ፣ “ተስፋ አለን ይሰሙናል፣ መልካም ነገር እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡ ይህንን ማስጠንቀቂ በማሳያነት የሚጠቅሱ ክፍሎች ተቃዋሚው ጎራና ኢህአዴግ ተያይዘው ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲገቡ አሜሪካ አሁን ላይ የደረሰችበት እምነት ነው። ለዚህም ይመስላል ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠችው ይላሉ። ሌሎች ግን አሜሪካ ምንም የምታመጣው ነገር የለም፤ ብታመጣ ኖሮ እስከዛሬ አትቆይም ነበር፤ ይህ ተራ የፖለቲካ ጫወታ ነው ሲሉ የአሜሪካንን አካሄድ ያጣጥላሉ፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ “በአሻባሪነት” ስም በሶማሊ የሚያደርገው ማስፈራሪያ ጊዜው ያለፈበት ይመስላል፡፡ የህወሃትና የአልሸባብ ግንኙነት እንዳለ ሆኖ አሸባሪነትን ለመዋጋት በሚል አርባ ምንጭ የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ (ድሮን ቤዝ) ማቋቋም ደርሳ የነበረችው አሜሪካ ፕሮጀክቷን ያጠናቀቀች ይመስላል፡፡ “ሶማሊያ ውስጥ … በኮንዶም አንዋጋም!” እያለ የሚያምታታ መለስ የሌለው ህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮውን ብቻ ሳይሆን ከበረሃ ጀምሮ ሲያግዙት የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎችም” እያጣ ነው፡፡

ዛሬ በረቂቅ ህግነት በሙሉ ድምጽ ያለፈው አዋጅ ወደ እንደራሴዎች ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ ማጽደቁ ለእንደራሴዎቹ ምክርቤት የድጋፍ ድምጽ መስጠት በር ከፋች ነው ብለዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያቀናበረው የምስል ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule