• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አሜሪካ ስለ ህወሃት – “እጃችንን ብናነሳ በህይወት አይኖሩም”

September 22, 2016 10:27 am by Editor 5 Comments

“አሁን አሜሪካኖቹ እያመረሩ ነው” የሚለው ዜና አየሩን ወጥሮታል። በተለይም የኦባማ አስተዳደር ለኢህአዴግ/ህወሃት የጻፈው የከረረ ደብዳቤና ትዕዛዝ ለአገዛዙ የመቀመጫ ላይ ቁስል ሆኖበታል። ለዚህም ይመስላል ሃይለማርያም ሳይፈልጉ መለስን እንዲሆኑ ታዝዘው አሜሪካንን ወርፈዋል። ይኸው የሃይለማርያም ዘለፋ ያበሳጫቸው የስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች “ሰዎቹ ከማን ጋር እንደሚያወሩም አያውቁም። ደቡብ ሱዳን መሰልናቸው” ማለታቸውን የመሰክሩ ለጎልጉል ገልጸዋል። ይህንኑ ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ባስቸኳይ አሜሪካ እንዲመጡ ታዝዘዋል።

በወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀውስ ዙሪያ የአሜሪካ መንግስት ከህወሃት/ኢህአዴግ ጋር እያደረገ ያለውን ግንኙነት በቅርብ የሚከታተሉና በቂ መረጃ ያላቸውን በመጠቀስ የጎልጉል የአሜሪካ ዜና አቀባይ እንደዘገበው፣ የኦባማ አስተዳደር የጻፈው ደብዳቤ ሃይለማርያምን አደባባይ ወጥተው እንዲዘላብዱ አድርጓቸዋል።

“ግድያ አቁሙ፣ ማስተካከል የሚገባችሁን አስተካከሉ” የሚል ቁልፍ መልዕክት የያዘው ይህ የኦባማ አስተዳደር ደብዳቤ የአገዛዝ ለውጥ (regime change) እስከማድረግ የሚጠይቅ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ህወሃትን የጎመዘዘው ደብዳቤው ከመጻፉ በፊት በተለያየ ደረጃዎች ባሉ ባለሥልጣናትና አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲ አማካይነት ህወሃት ከያዘው መንገድ እንዲታቀብ ሲጎተጎት እንደነበር የሚታወስ ነው።

በዚሁ መነሻ ሳይፈልጉ መለስን ሆነው መግለጫ እንዲሰጡ በህወሃት የታዘዙት ሃይለማርያም “ሪዢም ቼንጅ/አገዛዝ ለውጥ ይሉናል/” ሲሉ ስምና አገር ሳይጠቀሱ ተዛልፈዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ በራሱ በአገሩ ፖለቲካ ወሳኝ እንደሆነ ያወሱት ሃይለማርያም “በገንዘብ ድጋፍ” ዙሪያ ከደሰኮሩ በኋላ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት የአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ መፈትፈት እንደማይቻል “መለስን ሆነህ ተናገር” በተባሉት መሰረት ተጽፎ የተሰጣቸውን የሚችሉት ያህል ስሜታዊ ሆነው ተናግረዋል።

ልክ መለስ በ97 ምርጫ ወቅት እንዳደረጉት፣ ሃይለማርያምም ኢህአዴግ አሁን  ካለበት በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተግባር ራሱ ሊያቅብ እንደሚችልና፣ ከሶማሊያ ዘመቻ ጦሩን እንደሚያስወጣ አስጠንቅቀዋል። ህወሃት ችግር ሲገጥመውና የአንጋሾቹ ፊት ሲጨማደድበት “የምስራቅ አፍሪካን ክልል ለአልሸባብ አሳልፌ እሰጣለሁ” እያለ ሲያስፈራራና ሲነግድ የኖረ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ዛቻው የራሱን ገመድ የሚያሳጥር እየሆነ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

የሰላም ማስከበር “ዘመቻ እልል በቅምጤ” ለህወሃት አንድ የንግድ ኢምፓየሩ ነው። ብዙዎች እንደሚያውቁት በዚህ ዘመቻ የህወሃት ጄኔራሎች ዶላር ያፍሳሉ። በዶላር አበል ስለሚምነሸነሹ ምደባ ላይ እንኳን አይስማሙም። ቅሬታ የተፈጠረበት ጊዜም ጥቂት አይደለም። ለዚህም ሲባል ነው በየጊዜው ከፍተኛ መኮንኖች ቶሎ ቶሎ እየተፈራረቁ ከጸበሉ እንዲቋደሱ የሚደረገው።

እ.ኤ.አ. 2010 መጨረሻ ላይ በሰላም ማስከበር ላይቤሪያ ደርሰው የተመለሱ የሠራዊቱ አባላት “በውጭ ምንዛሬ ሲከፈለን የነበረው ገንዘባችን ሙሉ በሙሉ ይሰጠን” በማለት መሳሪያ በማንሳት ኮማንዶ የምትባል ከተማ ላይ የጎጃምን መንገድ ቆርጠው መደራደራቸውን የሚያስታውሱ ወገኖች፣ ከሰላም ማስከበሩ ስራ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ጥቅም ቀላል ባለመሆኑ “ተውት” ቢባሉ የህወሃት ጄኔራሎች እና የጥቅሙ ተቋዳሾች ለቅሶ እንደሚቀመጡ ብዙዎች ይስማማሉ። ከተራው ወታደር በስተቀር!!

ይህንን በመረዳት ይመስላል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት /የስቴት ዲፓርትመንት/ ሰዎች “የአሜሪካንን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችለው ህወሃት ብቻ አይደለም” ሲሉ የተደመጡት። አሁን አሜሪካ እየያዘች ያለውን አቋምና ከህወሃት ጋር እያደረገች ያለቸውን ግንኙነት በቅርብ የሚያውቁት መረጃ አቀባያችን “አሁን አሜሪካኖቹ የእኛን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉ ሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች አሉ” በማለት ከፍተኛ ባለስልጣናት መናገራቸውን ያስረዳሉ። ይህም ለዓመታት በተቃዋሚው ወገን ሲወተወት የነበረው ተፈጻሚነት የሚያገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላከተ ነው፡፡

መለስ በG-20 ስብሰባ
መለስ በG-20 ስብሰባ

አያይዘውም አንድ ከፍተኛ የስቴት ዲፓርትመንት ባለስልጣን በመገረም የተናገሩትን ይጠቅሳሉ። ህወሃት በሃይለማርያም አማካኝነት አሜሪካ እጇን ከኢትዮጵያ ላይ እንድታነሳ ይህ ካልሆነ ደግሞ ጠቅልሎ ከሶማሌ እንደሚወጣና በአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተግባሩን እንደሚያቆም ማስጠንቀቁን አስመልከቶ ባለስልጣኑ “እኛ የደቡብ ሱዳን ዓይነት መንግስት መሰልናቸው እንዴ?” ብለው ይጠይቁና አያይዘውም “እነሱ ከሶማሌ ቢወጡ እኛ አንሞትም። እኛ ግን እጃችንን ብናነሳ እነሱ ህይወታቸው አይኖርም፣ ሥልጣናቸውም በቀናት ውስጥ ታሪክ ይሆናል” ሲሉ የአሜሪካን ትዕግስት ወደ መገባደጃው መድረሱን የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ጉዳዩ የሸክላ ድስት ከብረት ድስት ጋር ያደረገውን አይነት ጸብ ተደርጎ ተወስዷል።

አንድ የመለስ የቅርብ ወዳጅ የሆኑ ከፍተኛ ዲፕሎማት “መለስ ይታዘዘና፤ መለስ አድርግ የተባለውን ያደርጋል፤ መለስ አያስቸግርም፤ መለስ ይሰማናል፤ እነዚህ አይሰሙም፤ ማድረግ ያለባቸውንም አያውቁም” ሲሉ ተማርረው ሲናገሩም ተደምጠዋል። እነዚህኞቹም ሆነ መለስ ተላላኪ ስለመሆናቸው ጥያቄ ባይነሳም፣ በመላላክ አንዳቸው ከሌላቸው የሚለዩበት ነገር ባይኖርም አሁን መካረሩ የመጣው “ልቀቁ” እስከማለት በመደረሱ እንደሆነ ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።  ሌላ አንድ ጡረተኛ፣ ነገር ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዲፕሎማት “የወያኔ ነገር አሜሪካኖች ጉንጭ ውስጥ እየጎመዘዘ ሄዷል” ሲሉ ተደምጠዋል። እኚሁ ሰው በቅርቡ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳይ በተመለከተ ለአሜሪካ ምክርቤት የቀረበው ጠንካራ ረቂቅ ሕግ (H.Res.861) የሚጽድቅበት ጊዜም ሩቅ እንደማይሆን አመልክተዋል።

አሜሪካኖቹ ስራቸውን የሚሰራሉላቸው ሌሎች አካላት እንዳሉ መግለጻቸውን ተከትሎ ሃይለማርያም አሜሪካ መጥተዋል። ፋና የሚሰኘው የስርዓቱ አንደበት መስከረም 11 ቀን 2009 ግርማ ብሩን ጠቅሶ እንዳለው “ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድና ኧንደር ሴክሬተሪ ሻነን ስሚዝ ጋር መወያየታቸው” ይፋ አድርጓል።

smith3እንደ ፋና ወሬ የውይይቱ አንኳር ጉዳይ በምስራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር በሚቻልበትና የኢትዮጵያ ሚና በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መሆኑን፣ በውይይቱ  በተለይ በሶማሊያም ሆነ በደቡብ ሱዳን አገሮች ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ በኢህአዴግ ስም ሃይለማርያም ቃል ገብተዋል። “ጦራችንን ከሶማሊያ እናስወጣለን፣ ከሰላም ማስከበሩ ስራ ራሳችንን እናገላለን” ብለው በፎከሩ በቀናት ልዩነት ጌቶቻቸው ደጅ ደርሰው መሃላ መፈጸማቸው ከላይ የተባለውን ዜና የሚያጠናክር ሆኗል።

“በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት” በማለት አሁን ሰላም እንዳለ በማስመሰል የፕሮፓጋንዳ ዜና የዘገበው ፋና፣ ችግሩን ለመፍታት እየተደረገ ስላለው ጥረትና የግጭቱን መንስኤ በመለየት የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ስለመብራራቱ ችግሩን የእግረመንገድ አስመስሎ አቅርቦታል።

የጎልጉል የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ግን ሃይለማርያም ደሳለኝ ታጋይ ጀኔራልና የህወሃት ሰዎች እየመሯቸው ወደ አሜሪካ ባስቸኳይ የመጡት እንደተባለው ለተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ብቻ ሳይሆን እንዲመጡም ታዝዘው ነው። ዋናው ጉዳይ “ከፓርላማው ፉከራ” ማግስት ቀደም ሲል በደብዳቤ የተገለጸላቸውን ጉዳይ እንዲቀበሉ ሲሆን በተደረገውም ውይይት አድርጉ የተባሉትን እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው የግድ ይሆናል።

meles isayasህወሃትን የመሰለ የወንበዴ ቡድን እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት አገር እንዲመራ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈውና አበባ ጎዝጉዘው ከሥልጣን መንበር ላይ ያስቀመጡት ምዕራባውያን በተለየም አሜሪካኖች ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ከሕዝብ ጋር እንደወገኑ በማስመሰል ህወሃትን የማይሰማ፤ የማይታዘዝ እያሉት ይገኛል፡፡ እንደ ክሪስ ስሚዝ ዓይነት ጥቂት የአሜሪካ ፖለቲከኞች በስተቀር አብዛኛዎቹ በሹመት የመንግሥት ባለሥልጣናት የሆኑቱ የኢትዮጵያን ጉዳይ ለህወሃት ሙሉ በሙሉ አሳልፈው የሰጡ ናቸው፡፡ የአዛዥና ታዛዥ ግንኙነቱም ከበረሃ የጀመረ መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደር የእግር እሳት ሆኖ ያለፈውን የ1997 ምርጫ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከመለስ ጋር በርካታ ዲፕሎማቶችና የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ተነጋግረዋል። ከእነዚህ አንዱ አሁን ረቂቅ ሕግ (H.Res.861) በመጻፍ ቀዳሚ የሆኑት ከኒውጀርሲ ጠቅላይግዛት የአሜሪካ ም/ቤት ተወካይ ክሪስ ስሚዝ ናቸው። የዛሬ ሦስት ዓመት “ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል የተዘጋጀ የምክክር ሸንጎ በመሪነት ሲከፍቱ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው …” በማለት ነበር የገለጹዋቸው። የርሳቸው ገለጻ ታዲያ ከ25 ዓመታት በፊት ኢህአዴግ እንዲነግስ ሲወሰን ከቃል በላይ እሳት እየተፉ ንግግር ያደረጉትን ኢትዮጵያዊ ያስታወሰ ነበር – የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!

goshu“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ዕቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላትን አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው የኢትዮጵያን ተላልፎ መሰጠት የተናገሩት ታሪካዊ ንግግር ልዩ ሰነድ ሆኖ የተቀመጠላቸው ነው።

ከ25 ዓመታት በኋላ ብዙ ለውጦች ተካሂደዋል፡፡ በቢል ክሊንተን “የህዳሴ መሪዎች” ተብለው የተሞገሱት የምስራቅ አፍሪካ “ቆንጆዎች” ምርጥ አምባገነኖች ሆነዋል። መለስ ሞቷል፤ ኢሣያስ ነትቧል፤ ካጋሜና ሙሴቪኒ ቀናቸው ተቆጥሯል፡፡ የዛሬ 25ዓመት የነበረው ሙዚቃ “ሬዢም ቼንጅ” ነበር፡፡ ቅጂው ግን በካሴት ነበር፡፡ ዛሬም ሙዚቃው ያው ይመስላል፤ ያሁኑ ቅጂ ግን ዲጂታል ይሆናል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. tesfai habte says

    September 22, 2016 04:36 pm at 4:36 pm

    ኢሰያስ ነትቧል?—የኣመሪካ ተላካኪዎች፡ የዶላር ቅጥረኛች፡ ትምክህተኞች፡ የሌላ ትእዛዝ እየተቀበሉ የአፍሪቃ ቀንድ ያናጣጠሉ፡ የጨፈጨፉ፡ ወደሃላ ቀር የመለሱ፡ የስልጣን ስሶኞች፡ ሃይሌስላሴ፡ መውንጉስቱ፡ መለስ፦— የገደለ ኢሰያስ!—–የወንድ ወንድ!—የማይፈራ ተጋይ፥ ከቃል ግብርን የሚያሳይ፡ እዩን የወሰነው እንጂ የተላካኪነት ብህርይ የሌለው ቆራጥ መሪ ነው። እጥፍ ተኪና፡ ተዋጊ፡ ከትውልድ ወደ ትውልዲ የሚያስተላልፍ ታሪክ የሰራ የመሰረት፡ ብህዝብ ሃይል እንጂ ብጉጠኝነት የማያምን ትግህ፡ እኔ የማይል፡ ተታሪ ነው። ፈጣሪ ለኤትርትራ የነብዩ ኢሰያስ የሰጣት!—–በሃይማኖቱና በእምነቱ ጽኑዕ፡ እንደ መለስ፡ ጋጋመ፡ ሙሴበኒ የግብረሰዶም የማይቀበል፡ ኣስመሳይ ኣይደለም!—-እንደ ኣንተ እንትም ት#$ የማይል ነፍጠኛ ኣይደለም!—-የዶላር ተላላኪ ቅጥረኛ!—ሰላም የማይምኙ ዘውትር ጦረኛ!

    Reply
  2. ወንድሙ መኰንን says

    September 23, 2016 10:54 am at 10:54 am

    ጎልጉል – እናመሰግናለን። እንደ አፋችሁ ያድርግልን። ግን ከኔ በፊታስተያየት የሰጡት ግለሰብ ምን እያሉ ነው?

    Reply
  3. Negash Abdurahman says

    September 24, 2016 06:13 am at 6:13 am

    Dear Goolgule,

    I read your articles frequently and usually appreciate what you write. Unfortunately, this particular piece with alleged leaks from US officials has the smell of a disinformation campaign.

    Where is the disinformation? Ethiopians have rightly and increasingly become angry at US coddling of the TPLF ethnic dictatorship. This article craftily attempts to cast US policy in a positive light. The selective leaks from US officials are self-serving and meant to soften the attitude of Ethiopians. I suspect the disinformation is being channeled through someone of Ethiopian origin on the payroll of the US government.

    Please prove me wrong.

    Reply
    • Editor says

      September 24, 2016 08:38 am at 8:38 am

      Dear Negash Abdurahman,

      Many thanks for being a regular reader of our online newspaper. Greatly appreciate your kind words as well.

      Rightly said that the US is coddling the TPLF ever since they were “የበረሃ ወንበዴዎች” – Paul Henze is one to mention. However, as the TPLF is becoming a trouble child for the US and the West at large, with the anger of our people back at home and in the diaspora, it is up to us to become a viable alternative and strike it while the iron is hot. This is what the article is trying to magnify. Hence, it is more informative, we presume.

      The article doesn’t “craftily attempts to cast US policy in a positive light” because it has clearly stated this:

      “ህወሃትን የመሰለ የወንበዴ ቡድን እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት አገር እንዲመራ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈውና አበባ ጎዝጉዘው ከሥልጣን መንበር ላይ ያስቀመጡት ምዕራባውያን በተለየም አሜሪካኖች ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ከሕዝብ ጋር እንደወገኑ በማስመሰል ህወሃትን የማይሰማ፤ የማይታዘዝ እያሉት ይገኛል፡፡ እንደ ክሪስ ስሚዝ ዓይነት ጥቂት የአሜሪካ ፖለቲከኞች በስተቀር አብዛኛዎቹ በሹመት የመንግሥት ባለሥልጣናት የሆኑቱ የኢትዮጵያን ጉዳይ ለህወሃት ሙሉ በሙሉ አሳልፈው የሰጡ ናቸው፡፡ የአዛዥና ታዛዥ ግንኙነቱም ከበረሃ የጀመረ መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡”

      Besides, the silence of the US to Colonel Goshu’s serious concern is another point to mention that the article is not trying to “cast US policy in a positive light” – from the get-go it was corrupted. We also never forget Obama’s “democratically elected …” discourse.

      In fact, the information in the article should be taken with a grain of salt, not to say that the information is inaccurate. But due to lack of clarity and commonality of our political, #protest, #resistance … agenda and other intrinsic factors apart from the TPLF, these kinds of talks in the diplomatic corridors, unless they are materialized into tangible policies, can change anytime.

      Regardless of what the TPLF is saying all the time, this article is adding another proof, from the horse’s mouth, about the real life support of TPLF.

      Finally, with all due respect we beg to differ to your statement “I suspect the disinformation is being channeled through someone of Ethiopian origin on the payroll of the US government.” In fact it is to the contrary.

      Again, we are thankful for your candid comment and speaking your mind.

      Editor

      Reply
  4. Angile says

    September 24, 2016 04:30 pm at 4:30 pm

    የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule