ከዚህ በፊት በአሜሪካ ምክርቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በረቂቅ ሕግነት ከቀረቡት መካከል ህወሓት/ኢህአዴግ HR 128 እጅግ ፈርቶታል። ይህንን ረቂቅ ሕግ ለማክሸፍም የውትወታ (ሎቢ) ሥራ ከመሥራት ጀምሮ የአሜሪካ ባለሥልጣናትንና የፖለቲካ መሪዎችን በ“አልሻባብ ምስራቅ አፍሪካን ይወራል” ድራማ ለማስፈራራት ተደጋጋሚ በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም። ላለፉት በርካታ ወራትም (በቅርቡ ወደ አሜሪካ የመጡትን እነ ወርቅነህን ጨምሮ) ሊያሳምኑ ይችላሉ የሚላቸውን ሹሞቹን በመላክ ረቂቅ ሕጉ በተግባር እንዳይውል የአሜሪካ ባለሥልጣናትንን - ጊዜ ስጡን፣ ሁሉን እናስተካክላለን፣ … የመሳሰሉ ተማጽንዖዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በግምባር ቀደምትነትም የህወሓት ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ ኢትዮጵያ ድረስ እስኪሄዱ ያደረሰ የውትወታ ሥራ ተካሄዷል። ይህንን ረቂቅ … [Read more...] about ህወሓት፡ የHR 128 ፍርሃቻ እና የማግኒትስኪ ሕግ