አገሪቱን ከሁሉም አቅጣጫዎች ለዓመታት ሲያናውጥ የቆየው ሕዝባዊ ዓመጽ ከHR 128 ጋር ተዳምሮበት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባው ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እያለ በግፍ ያሰራቸውን እየፈታ ነው። የተፈቱት ተመልሰው ላለመታሰራቸው ምንም ዋስትና የለም ተብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚዳንትነቱን መንበር ከተረከቡ ጊዜ ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) የተባለው አሸባሪ የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን ስሉሱ እንደዞረበት አስተውሎ የራሱን ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። በጣም ይተማመንባቸው የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎች” ህወሓት መናፈቅ የጀመረው ኦባማ የሥልጣን መንበሩን በሚያስረክቡበት የመጨረሻ ዓመት መገባደጃ ላይ ነበር።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ October 3, 2017 ባቀረበው የዜና ዘገባ ላይ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይህንን ማለቱ ይታወሳል፤
ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በመንበሩ ላይ የተሰየሙት ዶናልድ ጄ ትራምፕ አስተዳደራቸው በአፍሪካ ላይ የተለየ አቋም የሚይዝ መሆኑ የተነገረው ገና ከጅምሩ ነበር። የትራምፕ የሽግግር ቡድን አፍሪካን በተመለከተ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ መ/ቤቶች ያቀረበው ባለ አራት ገጽ ጥያቄዎችን ያዘለ መረጃ ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቦበት ነበር። ከበርካታዎቹ ጥያቄዎች ጥቂቶቹ፤ “በአፍሪካ ይህንን ያህል ሙስና ተንሰራፍቶ እያለ ለአፍሪካ ከምንሰጠው ዕርዳታ ምን ያህሉ ይሰረቃል? እዚህ አሜሪካ ውስጥ በስንቱ ጉዳይ እየተሰቃየን ይህንን ይህል ገንዘብ አፍሪካ ላይ የምናፈሰው ለምንድነው? …” የሚሉ ነበሩበት።
ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም “አልሻባብን ለአስር ዓመት ያህል ስንዋጋ ቆይተን ለምንድነው እስካሁን ያላሸነፍነው?” የሚለው ጥያቄ በራሱ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሳና ለብዙዎቹም መልስ የሚሆን ተደርጎ የተወሰደ ነበር።
አዳዲሶቹ የትራምፕ ሹማምንት በአልሻባብም ጉዳይ ወደ አፍሪካ ጉብኝት ሲያደርጉም ሆነ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ሲያስቡ እንደተለመደው ህወሓት/ኢህአዴግ ታሳቢ በማድረግ ሳይሆን መቅረቱ በህወሓት ዘንድ ጭንቀት ሲፈጥር ቆይቷል። በተለይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ማቲስ ጅቡቲን ጎብኝተውና በአልሻባብ ጉዳይ ላይ መክረው ሲመለሱ ህወሓት በስብሰባው ላይ እንዳይገኝ ተደርጓል። ሚስተር ማቲስም ከጅቡቲ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ጉብኝት ሳያደርጉ ተመልሰዋል፤ ይህ ብቻ አይደለም የብሩ ቋትም መጉደል ከጀመረ ሰነባብቷል። በኦባማ አስተዳደር ዘመን ኢትዮጵያ የአሜሪካ “ስትራቴጂካዊ አጋር” የሚለው አነጋገር በትራምፕ ዘመን ሲነገር እስካሁን አለመሰማቱ ብቻ ሳይሆን ህወሓት የሚቆምርበት የአልሻባብን ጉዳይ አሜሪካ በራሷ የምትወጣው ጉዳይ አድርጋ መውሰዷ አቅጣጫዎች በገሃድ መቀየራቸውን ያመላከተ ሆኖ ታይቷል።
የትራምፕ አስተዳደር በአፍሪካ ላይ የተለየ አቋም የመያዙን ሁኔታ ተከትሎ በተለይ ከሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች አስመልክቶ የተቀናበረው HR 128 የህወሓት ሹሞችንና ቤተሰቦቻቸውን ያስጨነቀ መሆኑን ጎልጉል ዘግቦ ነበር። በዚህ ሁሉ መካከል የህወሓት ታዳጊ ሆነው ብቅ ያሉት የኦክላሆማው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ናቸው።
የHR 128 አክሻፊው ሴናተር ኢንሆፍ ፊትአውራሪ ሆነው ራሳቸውን ከሾሙ በኋላ ኢትዮጵያ ድረስ በመሄድ ከHR 128 ጋር የተገናኙ ተግባራትን እንደፈጸሙ ጉዳዩን የሚከታተሉ የሚስማሙበት ነው። ከዚህም ሌላ “ይህንን ረቂቅ ህግ ገና ከጅምሩ የፈራው ህወሃት ለወትዋቾች (ሎቢይስቶች) በጀት መድቦ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በዋሽንግቶን ዲሲ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ተጠሪ የሆነው ግርማ ብሩ SGR Government Relations ከተባለ የወትዋቾች ድርጅት ጋር በተፈራረመው ሰነድ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ለዚህ የውትወታ ሥራ ድርጅቱ (SGR) በወር 150ሺህ ዶላር፤ በጥቅሉ 1.8 ሚሊዮን ዶላር ይከፈለዋል። በርካታ የተቃዋሚ ድርጅቶችና ቡድኖች (በተለይ በዳያስፖራ ያሉቱ) ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ቀሩ እንጂ ሁኔታዎች እንዳላማሩለት የተረዳው ህወሓት የቤት ሥራውን መሥራት የጀመረው አስቀድሞ ነበር”።
ከወራት በፊት በሞቃዲሾ በደረሰውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖችን ህይወት በቀጠፈው የአሸባሪዎች ፍንዳታ ውስጥ የህወሓት አሻራ አለበት የሚሉ ወገኖች አሉ። ለዚህም አስረጅ አድርገው የሚያቀርቡት “እኛ ከሶማሊያ ከወጣን የሚሆነውን እዩት” የሚል ለአሜሪካ የቀረበ “ማስፈራሪያ” ነው ይላሉ። (ጎልጉል በዚህ ርዕስ ላይ ያቀረበውን ዘገባ እዚህ ላይ ይመልከቱ)
“ሁሉንም ፈንቅል HR 128ን አምክን” በሚለው አስተሳሰብ ሲንቀሳቀስ የቆየው ህወሓት ከዚህ ሁሉ ተደጋጋሚ ሙከራና ጥቃት በኋላ HR 128 በአሜሪካ የእንደራሴዎች ሸንጎ ለውሳኔ እንዳይቀርብ ለማቀዛቀዝ ቻለ። የHR 128 ጉዳይም ቀስ እያለ ላይነሳ የሞተ መሰለ።
ሆኖም በአገር ውስጥ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ፣ በዳያስፖራ ያሉቱ የሰላማዊ ትግል ተሟጋቾች ውትወታ እና በአሜሪካ የእንደራሴዎች ምክርቤት የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደራሴዎች ትጋት ከጥቂት ሳምንታት በፊት HR 128 ነፍስ መዝራት ጀምሮ ነበር። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ስብሰባዎችና ውይይቶች ሲጀመሩ ህወሓት ዕንቅልፍ ማጣት ጀመረ። እንደራሴዎችን በቀጥታና በእጅ አዙር መለማመጡን ቀጠለ። በርካታ ተስፋዎችን መግባት ጀመረ፤ ከነዚህም መካከል ክስ አቋርጣለሁ፤ እስረኞችን እፈታለሁ የሚለው እንደሚገኝበት ጎልጉል ከእንደራሴዎች ምክርቤት አካባቢ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ በፊት ከተረቀቀው HR 2003 በተለየ መልኩ HR 128 በርካታ ጉዳዮችንና ማነቆዎችን ያካተተ ነው። ረቂቅ ሕጉን ገና ከአወጣጡ ጀምሮ ሲከታተሉና ግብዓት ሲሰጡ የቆዩ ወገኖች እንደሚሉት ይህ ያሁኑ ረቂቅ ሕግ የህወሓት ሰዎች አንገት ላይ ገመዱን ያስገባ ነው። ኢትዮጵያውያንን በመግደል፥ በማሰቃየትና በማንኛውም መልኩ የሰብዓዊ መብቶቻቸውን በመርገጥ ስማቸው የሚገኝ የህወሓት ሹሞችና ተባባሪዎቻቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ከገንዘብ ሚ/ር መ/ቤት ጋር በመተባበር በዓለምአቀፍ ሕግጋት በተደነገገው መሠረት ዕቀባ እንዲያደርጉባቸው ረቂቅ ሕጉ ያዛል። ይህ ማለት በሌላ አነጋገር ህወሓት/ኢህአዴግ ለዚህ በHR 128 ላይ ለሰፈረው የአሜሪካ የለውጥ ዕቅድ የማይገዛ ከሆነ የህወሓት ሹሞችና ቤተሰቦቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ማዕቀብ ይጣልባቸዋል፥ ሃብታቸው እንዳይነቃነቅ ይደረጋል። የአሜሪካንን ፈለግ የሚከተለውና ከህወሓት ጋር የጸና ወዳጅነት የሌለው የአውሮጳ ኅብረትም ተመሳሳይ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል።
የህወሓት ወንበዴዎች ዋና መሪ የነበረው መለስ የ1997 ምርጫ ወቅት ሥልጣኑን ሊያጣ አፋፍ ላይ በነበረበት ጊዜ በቅንጅት ተጠርቶ የነበረውን የሥራ ማቆም አድማ እንዲቆምለት “ከፀሐይ በታች በማንኛውም ነገር ላይ እደራደራለሁ” ማለቱ የሚታወስ ነው። በምዕራባዊ የኤምባሲ ሰዎች (ነጭ ወያኔዎች) ድጋፍ የሥራ ማቆም አድማው ከተሠረዘ በኋላ ድርድሩን ትቶ የቅንጅት መሪዎችን እየለቀመ ቃሊት ማሰሩን ተያያዘው።
ከዚህ እና ከሌሎች ተመሳሳይ ተሞክሮዎች የሚነሱ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት የHR 128 ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ህወሓት አሁን እየፈታ ያለውን እስረኞች መልሶ የማያስርበት ምንም ማስተማመኛ የለም። በአስመሳይ ተሃድሶ ረቂቅ ሕጉ ጸድቆ እንዳይወጣ ካሰናከለ በኋላ ያቋረጠውን ክስ እንደገና የማይጀምርበት፤ የሚቃወሙትን ሁሉ “አሸባሪ” እያለ በአዲስ ክስ የማያስርበት ምንም ዓይነት የሞራል ልዕልና የለውም። በመሆኑም HR 128 ሕግ ሆኖ እንዲጸድቅ በተለይ በዳያስፖራው በኩል የሚካሄደው የውትወታ ዘመቻ (ሎቢ) በርትቶ መቀጠል አለበት፤ ለአሜሪካ እንደራሴዎችም የህወሓትን ባህርይ በማስረዳት በቃሉ የማይታመን ድርጅት መሆኑን ደጋግሞ ማስረዳት ያስፈልጋል ይላሉ። አንድ የሃይማኖት አባት ለጎልጉል በላኩት አስተያየት እንዳሉት “ህወሓት እንደ ሠይጣን ወዳጅ የለውም፤ ወዳጅም አያውቅም”።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Mulugeta Andargie says
ዩጉራጌ ሕዝብ ጡንቻ ነው ያስፈታቸው!! ግድ የለም!! ውነት ለሃገር ተቆርቋሪ መሆናቸውን ወደፊት ይለያል!!! እዚህ ብርሃኑ ነጋ ቦንገር እኮ ይደነፋል!! ልማታችን ላይ ተሳታፊ ካልሆናችሁ፣ የትም ኣታመልጡንም!! ስትወራጩ እንይዛችኋለን!!
cute-ehapa says
back again – phots without what they show and credit? if one writes pages how long doe it take to label photos?
Editor says
Welcome back, cute-ehapa,
It is a screenshot taken from a Youtube video showing a TPLF thug, which is also known as “federal police”, brutally beating an Ethiopian at Mesqel Square. What is superimposed on the picture – HR 128 – is added added by Golgul.
የመጀመሪያው፤ አንዲት እናት በኦሮሚያ ዱላ ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው (ምንጩ ያልታወቀ – ምናልባትም ማኅበራዊ ሚዲያ)
ሁለተኛው፤ ህወሓት ያሰማራችው ታጣቂዎች ተማሪዎችን ሲደበድቡ። አንደኛው በጫማው ተማሪውን ሲመታ ይታያል፤ ተማሪዎቹ ሰላማዊና ታዛዥ ሆነው ቁጭ ብለው ይታያሉ። ቦታው ኦሮሚያ፤ ምንጩ ከማኅበራዊ ሚዲያ።
ሶስተኛው፤ ጎንደር በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሰላፊዎቹ “በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው!!” የሚል በቀይ የተጻፈ እንዲሁም “የህዝብን ጥያቄ መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም!!” የሚል በጥቁር ወይም በሰማያዊ የተጻፈ መፈክር ይዘው። (ምንጩ ያልታወቀ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ)
የመጨረሻው፤ በሎንዶን የተደረገ የተቃውሞ ትዕይንተ ሕዝብ ምንጩ ያልታወቀ፤ ምናልባትም ማኅበራዊ ሚዲያ
Hope this explains.
Editor