የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን ዓቀፍ መንግሥት በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ለማስቻል በአሜሪካ የእንደራሴዎች ምክርቤት የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ያለአንዳች ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ኤፕሪል 10፤2018ዓም ጸድቋል። ህወሓት እጅግ ከፍተኛ የውትወታ ገንዘብ ያፈሰሰበትና በርካታ የፖለቲካ ሥራ የሠራበት ረቂቅ በምክርቤቱ በሚገኙ 108 እንደራሴዎች ስፖንሰር ያደረጉት ሲሆን የሁለቱም ማለትም የዴሞክራትና የሪፑብሊካን እንደራሴዎች በጣምራነት የደገፉት ረቂቅ ነበር። በዋሽንግቶን ዲሲ በ“አምባሳደርነት” ሹመት የኢህአዴግ ተወካይ ሆኖ የተቀመጠው ካሣ ተክለብርሃን ለምክርቤቱ ረቂቅ ሕጉ እንዳይፀድቅ ደብዳቤ ልኮ እንደነበር H.R. 128 ለኢትዮጵያ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባተመው የደብዳቤው ፎቶ አስታውቋል። በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ያደረጉት እንቅስቃሴ አንዱ የድሉ አካል እንደሆነ … [Read more...] about H.R. 128 ያለ ተቃውሞ አልፏል!
Archives for April 2018
A charismatic young leader tries to calm ethnic tension in Ethiopia
"The price of power may have been private assurances that aspects of the security establishment would be left untouched" Intelligence Expert at Georgetown University. IN ITS three decades of existence, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) has gone through only two leaders. Neither came to power through a competitive vote. So it was with a sense of novelty that Ethiopians awaited the outcome of a secret ballot held on March 27th to determine the new chairman of … [Read more...] about A charismatic young leader tries to calm ethnic tension in Ethiopia
ልጄ ሆይ፤ ሰው ሁን!
እነሆ ሰንበት ነበረ። ምዕመኑ በሚኖርበት ከተማ በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድሰት ቤተ ክርስቲያን እንዳለፉት አያሌ ሰንበቶች ሁሉ ባለፈው ሰንበትም ተገኝቷል። ቃሉን ሊሰማ፤ ስለ ቃሉም ለመኖር ብርታትን ሊያገኝ፤ ስለራሱና ስለቤተሰቦቹ፤ ስለ ህዝቦቹና ስለ ሀገሩም ሊፀልይ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ አንስቶ ሊለምን። ማረን ለማለት። እግዚኦታም ለማቅረብ። ከትጉሁና ትሁቱ ካህንም ቃለ ህይወት ሊሰማ። ቃለ ህይወትንም ሊማር። እነሆም ካህኑ ቅዳሴውንና ፀሎቱን ይመራሉ። ድምፃቸውም በመንፈሳዊ ቅላፄ በመቅደሱ ይሞላል። ዲያቆናቱም ይቀበላሉ። ምዕመናኑም ይደግማሉ። ወይ ተንበርክከውና አንገታቸውን ከመሬት ደፍተው፤ ወይ ቀጥ ብለው በመቆም እጆቻቸውን ወደ ፈጣሪ ዘርግተው። የካህኑ ድምፅ በፀሎትና በቅዳሴ ዜማ እንዲህ ይላል - አምላካችን ክርስቶስ ሆይ፤ የተጨነቀችይቱን ነፍስ ሁሉ አሳርፍ፤ … [Read more...] about ልጄ ሆይ፤ ሰው ሁን!
የጠቅላይ ሚንስትሩ ተስፋ ሰጪ ንግግርና የኛ ሚና!
በትናንትናው ዕለት በሕይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ የፖሊቲካ ታሪክ ውስጥ ሥልጣን ካንዱ ጠ/ሚንስትር ወደ ሌላው ሲሸጋገር በአደባባይ በማየቴ ለማመን እየተቸገርኩኝ ነው። በጠ/ሚንስትሩ ንግግር ውስጥም ላለፉት አርባ ዓመታት የለመድናቸው “ጠላት” “ጸረ ሰላም ኃይሎች” “እናሸንፋለን” የመሳሰሉ ካድሬያዊ አነጋገሮች ለመጀመርያ ጊዜ በመሪያችን አፍ አለመነገሩን፣ ተፎካካሪ እንጂ ተቃዋሚ እንደሌለ መስማት፣ የተለየ አስተሳሰብ ስላስተናገዱ ብቻ የተገደሉትን የፖሊቲካ መሪዎችና በጨቅላነታቸው የተቀጩትን አስታውሶ ይቅርታ መጠየቅ፣ ከልብ ይቅር ተባብሎ ያለፈውን ምዕራፍ ዘግቶ ወደ ፊት ለመራመድ መጋበዝ፣ ከኤርትራ ጋር በሰላም ለመኖር ከማሰብ አንጻር ንግግር ለመጀመር ዝግጁ መሆን፣ ከሁሉም በላይ ለዘመናት እንደ “ገበና” ተቆጥሮ የማይነገረውን የግልን ህይወት ለአደባባይ ፍጆታ ቀርበው ስናዳምጣቸው … [Read more...] about የጠቅላይ ሚንስትሩ ተስፋ ሰጪ ንግግርና የኛ ሚና!
“መጪው ጊዜ በኢትዮጵያችን የፍቅርና የይቅርታ ጊዜ ነው” ጠ/ሚ/ር ዓብይ አህመድ
"መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው፤" እየተባለ ጆሮዋችን ሲደነቁርባት በነበረ አገር አዲሱ ጠቅላይ ሚ/ር ዓብይ አህመድ “መጪው ጊዜ በኢትዮጵያችን የፍቅርና የይቅርታ ጊዜ ነው” በማለት ለኢትዮጵያ የሚመጥን ንግግር ኣድርገዋል። ይህንን አስመልክቶ ሪፖርተር ያጠናቀረው ዘገባ አንዲህ ይነበባል። "ኢትዮጵያውያን ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ ነን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር፣ በሕዝብ ዘንድ ትኩረትን ከሳቡት ጉዳዮች መካከል የቤተሰብ ጉዳይ አንዱ ነው። የሰባት ዓመት ልጅ እያሉ ሩቅ፣ ጥልቅና ረቂቅ ራዕይ በውስጣቸው የተከሉትን፣ ያሳደጓቸውንና ለፍሬ ያበቋቸውን ወላጅ እናት ለማመሥገን እንዲፈቀድላቸው ሲጠይቁ ብዙዎች ልባቸው ተነክቷል። እናታቸው … [Read more...] about “መጪው ጊዜ በኢትዮጵያችን የፍቅርና የይቅርታ ጊዜ ነው” ጠ/ሚ/ር ዓብይ አህመድ
ስማኝ ሰማእቱ!
ከባርነት ሞትን የመረጥከው ወንዱ፣ አፉን ክፍት አርጎ የዋጠህ መቃብሩ፣ የማዋይህ አለኝ ስማኝ ሰማእቱ፡፡ የፈሰሰው ደምህ በህልሜ እየታየኝ፣ አጥንትህ ከመቃብር እየጎራበጠኝ፣ እሾህ ቀጋ ሆኖ አላስተኛህ አለኝ፡፡ ለፍትህ ስትጮህ የቀረኸው ባጭር፣ ጎንደር ደብረታቦር ወልድያ ባህርዳር፣ ቡሬና ዳንግላ ማጀቴና አቸፈር፣ ዛሬም ወንድሞችህ ታስረዋል ግዮን ዳር፡፡ በስናይፐር የፈጁህ ህሊና ቢሶቹ፣ ለውጥ አመጣን ብለው ያንኑ ደገሙ፣ አንድ አስገዳይ ነቅለው ሌላውን ተከሉ፡፡ አጥንትህን ከአምቦ ከእሬቻ ለቃቅሞ፣ መሰላል አረገው ከለማ ጋር ሰርቶ፡፡ በስንት በጎች ደም እንደተነከረ፣ እጁን ሳይታጠብ አቢይ ቀደሰ፡፡ ኢያሱና ሙሴን ተከተሉ እያሉ፣ ስንቱን ዘልዛላ እንከፍ ከጀርባ አሰለፉ፡፡ ተመራጩ አስገዳይ መራጩም ገዳይ ነው፣ የሌላው ማሽቃበጥ ምን … [Read more...] about ስማኝ ሰማእቱ!
QUE SERA SERA!
Whatever will be, will be! Ethiopia has a new Prime Minister. Actually we never had Prime Ministers so far, for the last almost 27 years but Prime Miseries. None of them talked before, about Ethiopia. Dr Abiy Ahmed Ali talked about Ethiopia. That does sound like the Prime Minister of Ethiopia. Does it? Time will tell. Que sera sera! I have never called the Woyyane House of Cards, the EPRDF, by its fake name. For me, EPRDF was just a cover coat. The real body inside was the TPLF, or the … [Read more...] about QUE SERA SERA!
“(ዓብይ) ብዙ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች ፈጽሟል”
ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት እኩለ ሌሊት እየተቃረበ እያለ የተሰማው ሰበር ዜና በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ያነጋገረ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ ተተኪያቸው ማን ይሆን የሚለው በመላ አገሪቱ ዋነኛ መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተለይ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተተኪውን የግንባሩን ሊቀመንበር ለመምረጥ ስብሰባ የተቀመጠው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ለአንድ ሳምንት በመቆየቱ፣ በርካቶች በመላ ምቶችና በሴራ ንድፈ ሐሳቦች እንዲጨናነቁ አድርጓቸዋል፡፡ የአገሪቱ ፖለቲካ ለትንተና እስከሚያስቸግር ድረስ የተለያዩ መረጃዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመሰማታቸው፣ የተተኪው ማንነት ብዙዎችን ቢያሳስብ አይገርምም … [Read more...] about “(ዓብይ) ብዙ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች ፈጽሟል”
ህዝባዊ ትግል መቀጠሉ ነው ዋስትናው
የተደራጀ ኃይል ወደተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓስት ያደርሰኛል ብሎ ብዙ የጠበቀውና መስዋዕት ሲከፍል የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ በራሱ አመፅ የትግሉ ባለቤት ሆኗል። በኦሮምያ፣ በአማራ፣ በደቡብና በተለያዩ ቦታዎች በአምባገነኖች ጥይት ግንባራቸው እየተመታ የወደቁት፣ በእስር የሚማቅቁት፣ ተፈናቅለው የተሰደዱት ሁሉ የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባላት አይደሉም። በተቃውሞ ሰልፍ፣ በመንገድ መዝጋት፣ቤት ውስጥ በመቀመጥ፣ የነዳጅ ትራንስፖርት በማገድ፣ ሱቅ በመዝጋት፣ ግብር ባለመክፈል፣ ትጥቅ ላለመፍታት ገድሎ በመሞት፣ በኳስ ሜዳዎችና በህዝባዊ ስብሰባዎች ዘራፊ አምባገነኖችን በማጋለጥ፣ በመደበኛና በሶሻል ሚድያ ቅስቀሳ በማድረግ ስርዓቱን የሚይዘውና የሚጨብጠው ያሳጣው በዚህ ወይንም በዚያ ድርጅት አመራር የሚንቀሳቀስ አካል ብቻ አይደለም። የዘመናት ብሶት ያደቀቀው በቃኝ ብሎ ለተመሳሳይ ዓላማ … [Read more...] about ህዝባዊ ትግል መቀጠሉ ነው ዋስትናው
ከዶ/ር አብይ ንግግር ትኩረት የሳቡ ነጥቦች
በዶ/ር አብይ የሹመት ንግግር ውስጥ፤ ይቅርታ፣ እርቅ፣ ካሳ፣ ዲያስፖራ፣ ኤርትራ፣ ሙስና፣ ተቀናቃኝ ሃይሎች፣ የባከነ እድል፣ ስለ ዘረኝነት በሽታ እና የኢትዮጵያ ታላቅነት ተነስተዋል። “በቅጡ ሳይቧርቁ ሕይወታቸው ለተቀጠፈ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ለስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ሲሉ ጀመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ። በተለያየ ግዜያት መስዋዕትነትን ለከፈሉ፤ የመብት ተከራካሪዎች እና የፖለቲካ ስዎች ለደረሰው ጉዳት፣ ለፈሰሰው ደም እና ለጠፋው ህይወት፤ ይቅርታ ብቻ ብለው አላለፉም። ለተፈጠረው ችግር እልባት፤ ለተበደለ ወገን ደግሞ ካሳ እንደሚከፍሉም ተናግረዋል። “ከስህተታችን ተምረን ሃገራችንን የምንክስበት ወቅት ነው!” ማለታቸው ራሱ ንግግራቸውን በተግባር ለመተርጎም ያላቸውን ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳየናል። የመርህ … [Read more...] about ከዶ/ር አብይ ንግግር ትኩረት የሳቡ ነጥቦች