• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከዶ/ር አብይ ንግግር ትኩረት የሳቡ ነጥቦች

April 2, 2018 03:03 pm by Editor Leave a Comment

በዶ/ር አብይ የሹመት ንግግር ውስጥ፤ ይቅርታ፣ እርቅ፣ ካሳ፣ ዲያስፖራ፣ ኤርትራ፣ ሙስና፣ ተቀናቃኝ ሃይሎች፣ የባከነ እድል፣ ስለ ዘረኝነት በሽታ እና የኢትዮጵያ ታላቅነት ተነስተዋል።

“በቅጡ ሳይቧርቁ ሕይወታቸው ለተቀጠፈ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ለስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ሲሉ ጀመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ።

በተለያየ ግዜያት መስዋዕትነትን ለከፈሉ፤ የመብት ተከራካሪዎች እና የፖለቲካ ስዎች ለደረሰው ጉዳት፣ ለፈሰሰው ደም እና ለጠፋው ህይወት፤ ይቅርታ ብቻ ብለው አላለፉም። ለተፈጠረው ችግር እልባት፤ ለተበደለ ወገን ደግሞ ካሳ እንደሚከፍሉም ተናግረዋል። “ከስህተታችን ተምረን ሃገራችንን የምንክስበት ወቅት ነው!” ማለታቸው ራሱ ንግግራቸውን በተግባር ለመተርጎም ያላቸውን ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳየናል። የመርህ እና የእምነት ሰው ናቸውና፣ ይህንን ለማድረግ እንጂ ለማለት ብቻ አልተናገሩትም።

ከየት ጫፍ ተነስተው የት ጫፍ ላይ እንደደረሱ ለተመለከቷቸው ሁሉ፤ ከአንደበታቸው የወጣው ይህ ቃል ምን ያህል በተግባር ሊመነዘር እንደሚችል ይገምታሉ።

ሃገሪቷን ሸብቦ የያዛት የዘረኝነትን በሽታ እናጥፋ ብለዋል። “ማንነታችን የተሳሰረ፣ የተጋመደ እና የተዋሃደ ነው” ይላሉ። ይህችን አባቶቻችን በደማቸው የቆዩዋት ኃያል ሃገር ወደ ቀድሞዋ ታላቅነትዋ እንመልሳት፤ በርካታ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ታሪክ አለን ብለው ሲናገሩ ለሚሰማ ሰው እውነትም ይህ ሰው ሊመራኝ ይገባል ማለቱ እንግዳ አይሆንም። ይህ በእኛ ዘመን አልተለመደማ!

ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ ስርዓት ለመገንባት የህዝብ ፍላጎት እና ይሁንታ ያለው መንግስት መመስረት እንደሚገባው በአጽንኦት ተናግረዋል። ተቀናቃኝ ያሉዋቸውን የተቃዋሚ ሃይሎችም ጥሪ አቅርበዋር። ለሃገሪቱ ባይተዋር ሳይሆኑ የለውጡ አካል እንዲሆኑ ጋብዘዋል።

የሰው ልጆች ነጻነት ከመንግስት የሚቸር ስጦታ ሳይሆን የሰው ልጅ በተፈጥሮ ያገኘው ጸጋ እንደሆነ መናገራቸው ስለ ፕሬስ ነጻነት መቆማቸን ይጠቁመናል።

ከዲያስፖራ ጋር ያለው የሻከረ ግንኙነት ጠፍቶ ዲያስፖራውም በሂደቱ እንዲሳተፍ ተማጽነዋል። ያለፈውን ምዕራፍ ዘግተን በአዲስ ምዕራፍ እንጓዝ ሲሉ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ጠርተዋል። ጽንፈኛ ብሎ የሚሳደብ እንጂ፤ ይቅር እንባባል የሚል ልብ የሚነካ ጥሪ ከየትኛውም መሪ አልሰማንም። ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ ብሎ የተናገረ መሪ እስካሁንም አላየንም። ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች ብሎስ የተናገረ የኢህአዴግ ሰው መች ተሰምቶ ይታወቃል።

ከኤርትራ መንግስት ጋር ስለሚኖረው እርቅ እና ሰላም እቅድም ጥቅሰዋል። ሁለቱ ሃገር ህዝቦች በደም የተሳሰረ መሆናቸው እና ለክልሉ እድገት ወሳኝ በመሆኑ ለኤርትራ መንግስትም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ የለውጥ እድል እንደነበራት እና በአመራር ድክመት ሳብያ እነዚህ እድሎችዋን ሳትጠቀም መቅረትዋን ብቻ አልነበረም የተናገሩት፤ እሳቸውን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያመጣውን ይህንን እድልም ይጠቅሳሉ። የንግግራቸው ቁልፍ ይህ ይመስላል። ይህ እድል እንዳያመልጥ የሚል ይመስላል። ብሄራዊ መግባባትን ፈጥሮ ሁሉን ያቀፈ ፍትሃዊ ስርዓትን መመስረት።

የዶ/ር አብይ ንግግር፣ በመለስ ራዕይ ጀምሮ በመለስ ራዕይ ካበቃው ከኃይለማርያም ደሳለኝ አሰልቺ ንግግር ጋር የሰማይ እና የምድር አይነት ርቀት አለው።

ከኃይለማርያም የተረከቡት ይህ የስልጣን ሽግግር ከጊዜው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታዎች ጋር እኩል የሚጓዝና በህዝብ ፍላጎት የሚገዛ፤ ህዝብን አለቃው አድርጎ የሚያገለግል ስርዓት እየገነባን መሆኑን አብስሮናል።

የዶ/ር አብይ ንግግር ፓርላማው ለመጥራት እንኳ ይቀፍፈው በነበረው ኢትዮጵያዊነት ጀምሮ በዚያው ነው የጨረሰው። “ኢትዮጵያ የሁላችን ቤት ናት። ልዩነት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው” ከሚለው የመቀነስ ሳይሆን የድምር ፖለቲካ እሳቤ – ከሳጥን ውስጥ የወጣ አዲስ እሳቤ ነው።

በርግጥ ይህ የስልጣን ሽግግር ብዙ የተከፈለበት የህዝብ ትግል ውጤት መሆኑ ባይዘነጋም፣ መላው ሕዝብ በእኝህ መሪ ደስተኛ መሆኑ ከፈጣሪ የመጣ ተዓምር ነው ያሰኛል።

አለም በስጋት እና በጉጉት እየጠበቀው ያለው ይህ የለውጥ ሽግግር በተግባር ሲተረጎም ፈተናዎች ሊገጥሙት ይችላል። የሁሉም ድጋፍ ሲታከልበት የተሳካ ለውጥ እንደሚመጣ እርግጥ ነው። የቀድሞው ወዳጃቸው፣ ኸርማን ኮኸን በትዊተር ለዶክተር አብይ በላኩት መልዕክት “አይዞህ ስራህን በድፍረት ስራ፤ አለም አቀፉ ህብረተሰብ ካንተ ጋር ነው” ብለዋል።

የሹመት ንግግር በተናጋሪው መጻኢ ዘመን ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የኦባማ ንግግር በተግባር ባይተረጎምም ብዙዎችን ልብ ገዝቶ ነበር። ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬነዲ በቀዝቃዛው ጦርነት ሰሞን ምዕራብ በርሊን ተሰብስቦ ለነበረ ህዝብ Ich bin ein Berliner በርሊናዊ ነኝ፤ ሲሉ በመናገር የመላ ጀርመንን ልብ ሰልበው እንደነበርም ታሪክ ያወሳል። ይህን ያሉት ኮምኒዝምን ለመምታት እንጂ ለሕዝበኝነት አልነበረም።

የዶ/ር አብይ ንግግር የሕዝብን ልብ ለመግዛት የሚደረግ ቢሆንም ይህ ክፋት የለውም። የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል እንዲሉ … በቃሉ የሚኖር ሰው ከአነሳሱ ያስታውቃል። ስልጣን … የማንም ስልጣን ገደል ይግባ! ከሀገር በላይ አይደለም:: ከማናችንም ስልጣናችን፣ ክብራችን፣ ከሀገር በታች ነው!” ብለውን ነበር ኦቦ ለማ መገርሳ።

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: abiy, eprdf, Left Column, prime minister, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule