ሁላችንም ካለንበት አጣብቂኝ ውስጥ መውጫ መንገድ አጥተን ተፋጠን ሰንብተናል። ስንነካከስ እንዳንጠፋፋ በሚያስፈራበት መልኩ ሁላችንም ግብ ግብ ስንገጥም እዚህ ደረስን። መንግስት በጉልበቱ ሲገፋበት፥ ሕዝብ በአመፁ ሲዘልቅበት፥ አማራጭ ኃይል በሁሉ አቀፍ ትግሉ ሲዘምትበት፥ አካሄዱ ሁሉ ሲያስፈራ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ያሰኝ ነበር። ሕዝቡ ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ ወደ አምላኩ ከመጮህ አልተቆጠበም። በአራቱም አቅጣጫ አንድነቷን እና ብልጽግናዋን በማይወዱ የተከበበች ሀገር ሆና ሳለ፥ ከውስጥ ደግሞ በነውጥ ስትናጥ ተስፋዋ እየመነመነ ጫፍ ደርሶ ነበር። ምን አልባት ታዲያ የማታ ማታ ፈጣሪዋ ኢትዮጵያን ከምጥ ሊገላግላት፣ ውጥረቷን አርግቦ ሰላምን ሊሰጣት አስቦ ይሆን ዶ/ር አብይ እርስዎን ወደ አመራር ያመጣዎት? ካለንበት አጣብቂኝ ለመውጣት ረዥም መንገድ መሄድ እንዳለብን እሙን ነው። ዶ/ር … [Read more...] about ዘብ ቆመናል ክቡር የኢትዮጵያ ልጅ ዶ/ር አብይ አህመድ
Archives for April 2018
ከአንድ አማራ ንቅናቄ የዶ/ር አብይ አህመድ መመረጥን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የአንድ አማራ ንቅናቄ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውሃገራች ን መስቀለኛ መንገድ ላይ በደረሰችበት በዚህ ወቅት ላይ በመመረጥዎ ሃላፊነትዎን ከመቼውም ግዜ በላይ ወሳኝና ታሪካዊ ያደርገዋል ብለን እናምናለን። የአማራው ሕዝባችን የእርሶን መመረጥ አስመልክቶ የብሄር ፤ የቋንቋና ፤ የማንነትድንበር ሳያግደው ለእርሶ ያሳየው ድጋፍና እምነት በግልጽ የሚታይ ሃቅ ነው:: አማራው ትላንትም ዛሬም ሆነ ወደፊት በሃሳብ ጥራት በስልጡንና ጨዋ የፖለቲካ ባህል ለሚያምን : ሃገራዊና ህዝባዊ አመለካከት ያላቸውን መሪዎች የሚከተልና የሚያከብር በመሆኑ እርስዎ ከዚህ ቀደም በአደባባይ ካቀረቡት ወገናዊና ስነምግባራዊ አቀራረብ መነሻ በማድረግ ድጋፉን ያለማንገራገር እየገለጸ ይገኛል። ሃገራችን ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት አደጋና ከገባችበት ከፍተኛ የፖለቲካ አጣብቂኝለመላቀቅ ስር ነቀል … [Read more...] about ከአንድ አማራ ንቅናቄ የዶ/ር አብይ አህመድ መመረጥን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ