• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከአንድ አማራ ንቅናቄ የዶ/ር አብይ አህመድ መመረጥን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

April 1, 2018 06:27 am by Editor Leave a Comment

የአንድ አማራ ንቅናቄ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውሃገራች ን መስቀለኛ መንገድ ላይ በደረሰችበት በዚህ ወቅት ላይ በመመረጥዎ ሃላፊነትዎን ከመቼውም ግዜ በላይ ወሳኝና ታሪካዊ ያደርገዋል ብለን እናምናለን።

የአማራው ሕዝባችን የእርሶን መመረጥ አስመልክቶ የብሄር ፤ የቋንቋና ፤ የማንነትድንበር ሳያግደው ለእርሶ ያሳየው ድጋፍና እምነት በግልጽ የሚታይ ሃቅ ነው:: አማራው ትላንትም ዛሬም ሆነ ወደፊት በሃሳብ ጥራት በስልጡንና ጨዋ የፖለቲካ ባህል ለሚያምን : ሃገራዊና ህዝባዊ አመለካከት ያላቸውን መሪዎች የሚከተልና የሚያከብር በመሆኑ እርስዎ ከዚህ ቀደም በአደባባይ ካቀረቡት ወገናዊና ስነምግባራዊ አቀራረብ መነሻ በማድረግ ድጋፉን ያለማንገራገር
እየገለጸ ይገኛል።

ሃገራችን ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት አደጋና ከገባችበት ከፍተኛ የፖለቲካ አጣብቂኝለመላቀቅ ስር ነቀል የፖለቲካ መፍትሄ በሚያስፈልግበት በዚህ ቀውጢ ጊዜ እንደቀደሙት ጠቅላይ ሚንስትር የሕወሃትን የዘረፋና የጭቆና አገዛዝ ለማስቀጠል በታለመ መልኩ የመሪነት ስልጣኑን ይቀበላሉ ብለን የማናምን በመሆኑ የሃላፊነት ግዜዎን በተስፋና በበጎ ምኞት የምንመለከተው መሆኑን እንገልጻለን።

ዘረኛውና ዘራፊው የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን ከተነሳበት አደገኛ ሕዝባዊ ተቃውሞና ተቀባይነት የማጣት አደጋ ብቸኛው መውጫ መፍትሄው አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመቀየር ለውጥ ይመጣል ብለን አናምንም። ነገር ግን የሃገራችን ኢትዮጵያን ስም በመልካምና በክብር አንደበት በመጥራት ላሳዩን ክብር ከጽንፈኛና ዘራፊ የትግራይ እብሪተኞች የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ በማለት እንገምታለን።

ምንም እንኳን አማራውን በይፋ የወከለ፥ እውነተኛ ወኪል በግልጽ ያልተሳተፈበትምርጫ  ፍትሃዊና ሁሉን ያካተተ ነው ባይባልም: በተጨማሪም የብአዴን አመራር አካላት አማራውን ይወክላሉ ብለን ባናምንም እርስዎ ለመመረጥዎ ሙሉ የብአዴን አባላት ድምጻቸውን መስጠታቸው ለማሸነፍዎ ትልቅ ሚና እንዳላው ጠንቅቀው ተረድተዋል ብለን እናምናለን።

ሃገራችን ከገባችበት ችግር አንጻር ዶክተር አብይ አህመድን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በመመረጥዎ ሁኔታውን አጢነን ከታች የሚመለከተውን የምኞትና የተግባር መግለጫ ሰጥተናል።

1. ዘረኛውና ዘራፊው የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን በአማራነታቸው ብቻ ያለምክንያት የታሰሩትን እና ሌሎችንም ኢትዮጵያውያን የፖለቲከኛ እስረኞችን ባስቸኳይ መፍታት

2. ያለ ሕግ አግባብና በኢሰብአዊ አያያዝ በባርነት ጥላ ስር ውለው ያሉ ወገኖቻችንን እና በማንአለብኝ እብሪት በትግራይ ግፈኞች የተወሰደውን የአማራ መሬት የሆነውን የወልቃይት ጠገዴ: ሁመራ: አላማጣና: ኮረም ወደ ቀደመ ባለቤታቸው የአማራ ይዞታ ከተገቢው ካስ ጋር እንዲመለሱ ማድረግ

3. በሃገራችንና በህዝባችን ላይ የተጣለውን የህገ አራዊት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማንሳት:

4. በትግራዪች የበላይነት የሚዘወረው የኢኮኖሚ ፤ ወታደራዊና ፤ የደህንነት መዋቅር ሁሉንም የሃገሪቷን ሕዝቦች ሊወክል በሚችል ደረጃ ተከልሶ እንዲዋቀር ተጨባጭ እርምጃን መውሰድ

5. ሁሉንም የተቃዋሚ ፓርቲወች የሚሳተፉበት ህዝባዊ ውይይት እና መግባባትን መፍጠር ሕዝባችን በጽናትና በቁርጠኝነት ልጆቹን እየገበረ ሲያካሂድ የቆየውን የለውጥ የሰላምና የዲሞክራሲ ትግል በጥገናዊ ለውጥና በተስፋ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሳይዛናጋ የሚካሄደውን የለውጥ ሂደት በንቃት በመከታተል በትግሉ እየተቀዳጀ ያለውን ድል እንዳይነጠቅ በተጠንቀቅ ከመቼውም ግዜ በላይ ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል።

አዲሱም የሃገሪቷ መሪ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር አብይ አህመድ ከአገዛዙ በተቃራኒ ሲያራምዱ የቆዩትን ሕዝባዊነት በበለጠ አጎልብተው በተስፋና በድጋፍ ከጎናቸው የቆመውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሚያሳዝንና የሃገሪቱን ሰላማዊ የለውጥ ተስፋ ከሚያጨልም ድርጊት ተቆጥበው ከሕዝብ ጎን እንዲቆሙ እና በመጭው የስልጣን ጊዜዎት መሰረታዊ ለውጦችን በአፋጣኛ እንዲፈጽሙ እናሳስባለን።

ድል ለሕዝባችን!!!
እውነተኛ አማራ እንኳን ተነጋግሮ ተያይቶ መግባባት አለበት !!!
አንድ አማራ ንቅናቄ

Oneamhara1@gmail.com
www.oneamhara.org


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: one amhara, Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule