በኔዘርላንድ በሚደረግ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ለመገኘት ተጋብዞ የነበረው እስክንድር ነጋ ሐሙስ ሌሊት ለአርብ ጠዋት ቦሌ ላይ ከአገር እንዳወጣ ታግቷል። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት ጉዳዩ ህወሓትን ትልቅ ቅርቃር ውስጥ ከቶታል።
ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት ይህ ፈጽሞ መከሰት ያልነበረበት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚ/ር አብይ በጉዳዩ ላይ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል።
ሌላው ለጉዳዩ ቅርበት ያለውና ክስተቱ እንደተፈጸመ አጭር ዘገባ ያሰራጨው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ “ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም” ብሏል።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከቦሌ አካባቢ ባገኘው መረጃ መሠረት እስክንድርን እንዳይወጣ ፓስፖርቱንና የጉዞ ሰነዱን የነጠቀችው የትግራይ ተወላጅ የሆነች የኤርፖርቱ ደኅንነት ሠራተኛ መሆኗ ታውቋል። ሆኖም ክስተቱ እንደተፈጸመ እና እስክንድርም በአየር ማረፊያው እንዲታገድ ከተደረገ በኋላ በምዕራቡ ዓለም ለሚገኙና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መረጃው እንዲደርስ ተደርጓል። የእስክንድርን መታገድ አስመልክቶ ማን ትዕዛዝ እንደሰጠ በወቅቱ የተደረገ ክትትል በቦታው የሚገኙት እርስበርሳቸው ሲወነጃጀሉና ራሳቸውን ከጥፋተኝነት ለማግለል ሲሞክሩ ተሰምተዋል።
እንደ ጎልጉል መረጃ ከሆነ ከእስክንድር ፓስፖርት መነጠቅ ጋር በተያያዘ በተከሰተው የህወሓት የአፈና ተግባር በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ የህወሓት ድርጎ ሰፋሪዎች ዘንድ መረጃው ደርሶ ህወሓት በሚገባው ቋንቋ እንደሚነግሩት ለማወቅ ተችሏል። እየሻከረ የመጣው የህወሓትና የምዕራቡ ግንኙነት ላይም ትልቅ ነጥብ የሚጥል መሆኑን አብሮን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። “ይህንን በፍጹም ማድረግ አልነበረባቸውም” የሚል ተጠያቂ የሚያደርግ ንግግር እና “የግመሏን ወገብ የሚሰብረው የመጨረሻው ገለባ ነው” የሚለው የእንግሊዝኛ ብሒል አብሮ ተሰምቷል።
እስክንድር በኢትዮጵያ አቆጣጠር አርብ ሲሆን የሚፈታ መሆኑን በተቻለው ሁሉ ለአምነስቲ ፕሮግራም ለመድረስ የሚችልበት ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሞከር ለማወቅ ችለናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍቃሪ ህወሓት የትግራይ ተወላጆች የተሞላ መሆኑንና እዚያም የሚገኙ ሠራተኞች እንደ መንግሥት ራሳቸውን በመቁጠር የፈለጉትን የሚያደርጉበት አሠራር መቆም ያለበት መሆኑን ዛሬ ከእስክንድር መታገት በኋላ በአጽንዖት በአየርመንገዱ አካባቢ የነበሩ ያሰሙት አቤቱታ ነው። ጠ/ሚ/ር አብይ ከሚያጸዱት መ/ቤት መካከል ቀዳሚው አየር መንገዱ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል።
አርብ ወደ ጎንደር የሚጓዙት ዶ/ር አብይ አህመድ፤ እስክንድር ነጋ ወደ አምስተርዳም እንደሚበር ሳያረጋግጡ ጉዟቸውን ወደ ጎንደር ማቅናት የለባቸውም ሲሉ ከአዲስ አበባ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰው ለጎልጉል ተናግረዋል።
ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ያቀናበaረው ዜና ከዚህ በታች ይነበባል፤
እስክንድር ነጋ -ፓስፖርቱን ነጥቀው ቦሌ ላይ አገቱት
የዲሞክራሲ ጥማት የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተመልክቻለሁ – እስክንድር ነጋ
ክንፉ አሰፋ — አምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር ለክብር እንግድነት በሆላንድ የጠራው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሊወጣ ሲል በህወሃት ታግቷል።
ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም። እስክንድር ነጋ ሃሳቡን በነጻ በመግለጹ ምክንያት የመጨረሻውን ሳንደምረው ለ8 ጊዜ ታስሯል። እ. ኤ. አ. በ2013 በሽብርተኝነት ተከሶ 18 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር።
እስክንድር ነጋ የካቲት 14 ቀን 2018 ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጋር ቢለቀቅም እንደገና ለ 9ኛ ጊዜ ታሰሮ ነበር።
እስክንድር ከዘጠኝ በላይ የክብር ሽልማቶች ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው።
1. በ 2011 PEN America (NY)
2. በ 2012 Barbara Goldsmith Freedom to Write Award
3. በ 2014 World Association of Newspapers’ Golden Pen of Freedom Award
4. በ 2015 PEN Canada Freedom of Expression Award
5. በ 2017 International Press Institute World Press Freedom Hero
6. በ 2018 Oxfam Novib/PEN Award for Freedom of Expression (60 laureates)
7. ሂዩመን ራይት ዋች የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና አምነስቲ የኢንተርናሽናል የክብር ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ነው።
ዶ/ር አብይ አህመድ ለውጥ ሊያመጣ ቃል በገባ ሳምንታት ቢቆጠሩም የህወሃት አፈና እና ግድያ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የአለም መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ዛሬ በእስክንደር ነጋ ላይ የተፈጸመው የተለመደ የህወሃት በደል በዶ/ር አብይ ፈንጥቆ የነበረውን ተስፋ የሚያጨልም ነው። የህግ ሳይሆን የህወሃት የበላይነት እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ለውጥ አይታሰብም።
ሕወሃት አይታደስም። አይጠገንምም። ህወሃት ከምድሪቱ ላይ መጥፋት ነው ያለበት። ይህ ደግሞ በሕዝባዊ አመጹ እውን ይሆናል።
እስክንድር ነጋ በሆላንድ ሃገር ከተዘጋጀለት የአምነስቲ ዝግጅት በኋላ ልጁን እና ባለቤቱን ለማየት ወደ አሜሪካ ሊያመራ እንደነበር ይታወቃል።
የሆላንድ ንጉስ ዊለም አሌክሳንደር የሚገኙበት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ከብረ-በዓል በእስክንድር ያለመገኘት የተነሳ መልካም የነበረ ድባቡ እንዲጠፋ መደረጉን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተወካይ ገልጸውልናል።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ
ተጨማሪ፤ ከአዲስ አበባ ባገኘነው መረጃ መሠረት እስክንድር ብዙም ሳይቆይ ተፈቷል። ፓስፖርቱና የጉዞ ሰነዱ ተመልሶለታል። በአምነስቲ ላይ የመገኘቱ ተስፋ አምልጧል። (April 20, 2018 @7:14PST)
አለም says
ያሠሩት በማን ትዛዝ እንደሆነ ተጣርቶ ከኃላፊነታቸው መነሳት አለባቸው።
የዋህ ነሽ says
በማስምሰል እንኮእን በቅጣት መልክ አድራጊውን ቢያነሱ ያው የነሱ የሆነውን የትግሪ ጊንጥ ነው የሚተኩት።