... “ያሰብኩት ተሳካ ያለምኩት ደረሰ፣ ሃሳቤም ተሟላ መንፈሴም ታደሰ፤...” ለዛሬዋ ጽሁፌ መግቢያነት የመረጥኳት ግጥም፣ በእውቁ ድምጻዊ በጥላሁን ገሠሠ ከተቀነቀኑት አያሌ የማኅበራዊ ዘርፍ ዘፈኖች አንዱ የሆነው ዘፈን አዝማች ናት(በሃሳባችሁ ዜማውን እያስታወሳችሁ ተከተሉኝ፤ በተለይ ከአጃቢ የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ጎልታ የምትሰማዋን፣ የአየለ ማሞን የማንዶሊን ዜማ እያዳመጣችሁ)። ... ከዛሬ አንድ ዓመት በፊት “አማኒ ኢብራሂም — ’ያልታወቀው‘የጥበብ ሰው” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ቢጤ በኢትዮጵያውያኑ ድረ-ገጾች (በኢትዮ-ሚድያ፣ በኢኤምኤፍ፣ በቋጠሮ፣ በጎልጉል...) ላይ ለንባብ አብቅቼ ነበር። ጽሑፉ እንደወጣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ ከሰላሣ ዓመታት በላይ የትና እንዴት እንዳለ ያላወኩትን፣ በሙዚቃ ሙያ በእጅጉ የተካነውን፣ ሁሌም ብዙዎች በአርዓያነት የሚጠቅሱትንና … [Read more...] about ዳግም ተገናኘን!
Archives for January 2018
“አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ታዲያ ሁላችሁም ለምን ከሥልጣን አትወርዱም? "ለአመጽ የግብረ መልስ የሚሰጥ አመራር እንጂ ለችግሮች ቀድሞ መፍትሄ የሚሰጥ አመራር አይደለም"፤ "አመራሩ ህዝቡ ከሚጠብቀው በታች ነው"፤ "አመራሩ ከሽፏል"፤ የማሸማቀቅና የማስፈራራት ተግባር ነው በፓርቲው ውስጥ ያለው፤ ተመሳሳይ ዓይነት ነገር ወደ ሕዝቡ ሰርጾዋል፤ ወዘተ በማለት "በድፍረት" የተናገረው የኦህዴዱ ለማ መገርሳ እንደዚህ ብቃት የሌለውን አመራር ቢያንስ "ሥልጣኑን መልቀቅ ይገባዋል" ሳይል ወይም ራሱ ሁኔታው የማይስተካከል ከሆነ ሥልጣኑን እንደሚለቅ ምንም ፍንጭ ሳይሰጥ ንግግሩን አብቅቷል። ህወሓት/ኢህ አዴግ እንደ ድርጅት ከሽፏል! ይህ የተመሰከረው ደግሞ በራሱ በአመራሩ ነው። እስካሁን በሥልጣን ለምን እንደቆዩ እና ወደፊትም ለመቆየት ለምን እንዳሰቡ ግልጽ ቢያደርጉ የተሻለ ነው። መለስም "እስከ እንጥላችን ገምተናል" እያለ … [Read more...] about “አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ፎቶና ታሪኩ – እስረኞች [የህወሓት ግፍ ሰለባ ስለሆኑት ወገኖቻችን ሲባል ሊነበብ የሚገባው]
{ፈላስፋ በወህኒ ቤት በራፍ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ አነበብኩ አለ፤ ይህች ቦታ የመከራና የጭንቅ ናት፤ ያልሞቱ (በሕይወት ያሉ) ሰዎች የሚቀበሩባት መቃብርም ናት። የወዳጆች መፈተኛ፤ የጠላቶች መደሰቻ የሆነች ቦታ ናትና።} አንጋረ ፈላስፋ (የፈላስፎች አነጋገር)፤ በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ በ1953 ዓ/ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተተረጎመ። ************************************************************* በወያኔ አገዛዝ፤ በወያኔ ቀንበር የካቴናው ስርስር የኮረንቲው ንዝር የመቀመቅ ፍዳው የጨለማው እስር የሰቆቃው ንረት የአውሬዎቹ ምንዝር እንዴት እንደ ሆነ እንዴት እንደነበር ፍትህ በሌለበት ለዳኛ ከመንገር ጠበቃ ከማቆም ዕማኝ ከመደርደር ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር። ፎቶ፤ ሴፕቴምበር 14 2011 (እአአ) የወያኔ ፀጥታ … [Read more...] about ፎቶና ታሪኩ – እስረኞች [የህወሓት ግፍ ሰለባ ስለሆኑት ወገኖቻችን ሲባል ሊነበብ የሚገባው]
የወያኔ “መርህ-አልባ” ክስ ስረ-መሰረትና አፀያፊ “ውነትነት”
ሰሞነኛ መነጋገሪያ የሆነው "ለፖለቲካ እስረኞች ይቅርታ ልሰጥ ነው?” የሚለው ድንገተኛየወያኔ ዛባር (ቅዠት) መሰል ወግ ከመንገዳችን እንዳያወጣን መነጋገሩ አስፈላጊ ሆኖ ስለተሰማኝ የዚህ ጽሁፍ ማጠንጠኛ ላደርገው ፈቀድኩ። “የእስረኛ መልቀቅ” ጩኸት ከአፋኞቹ አፍ አምልጦ እንዲወጣ ያስገደደው ዋነኛ ሀቅ የህዝብ እምቢተኛነትና አልገዛም ባይነት አመጽ ለመሆኑ አንዳች ብዥታ እንደሌለን እየታወቀ ወያኔ “ምህረትና-ይቅርታ” በሚሉ ቃላቶች ዙሪያ፤ በማፈራረቅ ሲዋዥቅ አውቆም ሆነ ሳያውቅ በፈጠረልን “አጀንዳ” የተነጠቀውን ኳስ አስመልሶ ዋናውን የነጻነት ጥያቄበብርሃን ፍጥነት ወደ እስረኛ የማስፈታት ባህሪ እንዳይወርደው ልብ ማለት የተገባ ነው። ለመሆኑ አሁንም አሁንም አጥፍቻለሁ፤ በስብሻለሁ፤ ተግማምቸ -አግምቻችኋለሁ እያለ ሲወሻከት የነበረው የወሮበላ ቡድን “ይቅርታ አስጠይቄ … [Read more...] about የወያኔ “መርህ-አልባ” ክስ ስረ-መሰረትና አፀያፊ “ውነትነት”
ጀንፎና ጅና!!
ዓመት ጠብቀው፤ ዐውደ ዓመትን ዙረው ከሚመጡት በዓላት አንዱ የገና (ልደት) በዓል ነው። ይህ በዓል በሀገራችን በያመቱ ታኅሣሥ 29 ቀን "ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም" (ዛሬ የዓለም ቤዛ ተወለደ) እያሉ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያኖች በደማቅ ሥነ ሥርዓት በዓሉን ያከብራሉ። ለገና በዓል በቀረበ ግዜ በሀገራችን ከሚዘወተሩና ከሚወደዱ ክንዉኖች መካከል የገና ጨዋታ ዋናዉ ነዉ። የበአሉን መድረስ ተከትሎ ጎበዛዝት መጫወቻዋን ጥንግ የሚያሾሩበት የክትክታ ዱላ በመቁረጥ በደንብ እንዲጠነክር ቅቤ እያጠጡ ሲወለዉሉት ይከርሙና የገና በዓል ደረስኩ ደረስኩ ሲል ሰፈሩ ሲደምቅ ጨዋታዉ ሲደራ የክትክታዉ መታያ ቀን ይሆንና ለገና ጨዋታ የጎበዝ ጥሩር መለጊያ በትርነት ይዉላል። ታድያ ይህ በትር እልህና ጉልበት በተቀላቀለበት ጎዝ እጅ የገባ ለት ጉልበቱ በደንብ ይታያል ሆኖም የምትለጋዋ ጥሩር … [Read more...] about ጀንፎና ጅና!!
መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
የተከበራችሁ አንባቢያን፤ ይህችን መጣጥፍ ለመከተብ የተነሳሁት የዶ/ር በያን አሶባን (የኦሮሞ ዴሞክራሲ ግንባር ቃል አቀባይ) ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩ በኋላ ነው፤ አመለካከታቸው ብዙ መልካም አስተሳሰቦችን በውስጡ ያካትታል፤ መልካም የምላቸው አመለካክቶች የኢትዮጵያ ችግር መፈታት ያለበት እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ፤ መሰረታዊ ለውጥ ማስፈለጉ፣ በሙሉ እከሌ ከእከሌ ሳይባል የፖለቲካ እስረኞች የመፈታትን ሃሳብ፣ የውጭው ትግል አጋዥነት እንጂ መሪ ቦታ መያዝ እንደማይገባው፤ የሚሉትን ሲሆን ትልቁ ተቃውሞዬ ወያኔን የሽግግሩ አካል ማድረጉ ላይ ነው፤ (በሰላምና እርቅ ሰበብ) ፍራቻቸው ወያኔ አጓጉል አወዳደቅ ከወደቀ አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ትገባለች ነው፤ {አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ከገባች ሰንብታለች}። ወደ በያን አሶባ ማንነት ስመለስ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በመለሱት ደብዳቤ … [Read more...] about መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
IS THE EPRDF OFFER FOR REAL?
IS THE RELEASE OF POLITICAL PRISONERS AN HONEST FIRST STEP TO PRODUCTIVE DIALOGUE LEADING TO RECONCILIATION, MEANINGFUL REFORMS AND RESTORATIVE JUSTICE OR IS IT A MANIPULATIVE SURVIVAL TECHNIQUE FOR THE EPRDF? Washington, DC-- On January 3, 2018, Prime Minister Hailemariam Desalegn publicly declared the EPRDF’S (Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front) decision to release all political prisoners and to close down the infamous Maekelawi detention center as a confidence-building measure … [Read more...] about IS THE EPRDF OFFER FOR REAL?
ዐማራን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ዐማራ ከመጥፋቱ በፊት ይጠፋሉ!
የተለያዩ ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት የሆኑ ሁሉ፣ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ማጥፋት የሚቻለው፣ዐማራውን ቀድሞ በማጥፋ ነው ብለው ያምናሉ። ለዚህ አባባል ዋቢውም፣ የፋሽስቱ ሞሶሎኒን ወረራን በዓይኑ የተመከለተውና በግብር ያየው፣ አዶልፍ ፓርለሳክ የተባለው ፀሐፊ የጻፈውና በተጫኔ ጆብሬ መኮንን፣ «የሃበሻ ጀብዱ» ሲል ወደ አማርኛ የተተረጎመው መጽሐፍ በግልጽ ያስረዳናል። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ … [Read more...] about ዐማራን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ዐማራ ከመጥፋቱ በፊት ይጠፋሉ!
The TPLF Should Face an Immediate, Complete & Independent Investigations
Amnesty International, Human Rights Watch,concerned US politicians like Rep. Chris Smith, Rep. Mike Coffman, Ethiopian activists and others who care about human rights in Ethiopia have been exposing tortures, killings and massacres committed by the TPLF (Tigrayan People’s Liberation Front) regime for more than twenty-five years. Most of these crimes are still being committed against many Ethiopians for their political views and ethnicities. Former prisoners, like Habtamu Ayalew, who were lucky … [Read more...] about The TPLF Should Face an Immediate, Complete & Independent Investigations
ጥያቄው አሁንም ግልጽ ነው!
ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ምርጫ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በማለት የሰየመ የአሸባሪ ወንበዴዎች ቡድን አሁንም የውንብድና ተግባሩን እየፈጸመ ይገኛል። ይህ በዓለምአቀፋዊ የአሸባሪዎች መረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት የተመዘገበ ድርጅት በነጻ አውጪ ስም ሕዝብ ሲጨፈጭፍ፣ ሲያዋርድ፣ ሲያስር፣ ከአገር ሲባርር፣ ሲያፈናቅል፣ … የኖረ ድርጅት አሁንም በዚሁ ተግባሩ ቀጥሏል። ዓላማ ብሎ የተነሣለትን አገር ማፍረስ የተቃወሙ፣ ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ የገለጹ በሙሉ አሸባሪ፣ ጸረ ልማት፣ ጸረ ህዝብ፣ … በማለት ሲገድልና ሲያሰቃይ ኖሮ አሁን ደግም “አላሰርኩም” ሲላቸው የነበረውን እስረኞች “እፈታለሁ” ብሏል። ይህ በህወሓት/ኢህአዴግ ስለተነገረው መግለጫ ጥቂት ነጥቦች ብቻ እናንሳ፤ በመጀመሪያ ኃይለማርያምና ጓደኞቹ በኢትዮጵያ ስም እና ስለ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ጥያቄው አሁንም ግልጽ ነው!