ላለፉት በርካታ ዓመታት በየአደባባዩ "በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም" ሲል የነበረው ህወሓት/ኢህአዴግ ዛሬ በኃይለማርያም አማካኝነት "እስረኞችን እፈታለሁ፥ ማዕከላዊን እዘጋለሁ" ብሏል። ባለፉት ዓመታት በግፍ የታሰሩት በሙሉ የተከሰሱት በአሸባሪነት መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህ መግለጫ በራሱ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲዋሽ እንደነበር የሚያሳይ ነው ወይም ይቺ ጊዜ መግዣ የህወሓት ጨዋታ ነች። ለሁሉም በመቆየት የሚታይ ነው። የእኛ አቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ አመለካከቱ መታሰር የለበትም፥ በግፍ የታሰሩት ሁሉም የፖለቲካ እና የኅሊና እሥረኞች ህወሓት/ኢህአዴግ ይቅርታ እየጠየቀ ካሣ ከፍሎ በነጻ ይልቀቃቸው ነው። ጎልጉል! … [Read more...] about ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እስረኞችን እፈታለሁ አለ
Archives for January 2018
ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከወር በላይ ስብሰባ በማድረግ የደቆሰውና የፈጨውን በተስፈኞቹ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ በመድፋት በድንፋታ ኢህአዴግ የሚለውን የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁ ከራሱ ከአገዛዙ የሚዲያ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
መፍትሄው በብሄራዊ መግባባት የሽግግር ሂደትን እውን ማድረግ እንጂ ለ27 ዓመት የተደረገውን መድገም አይደለም
ህወሓት-መራሹ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 17 ቀናት የወሰደ ስብሰባውን እንዳጠናቀቀ በማመልከት መግለጫ አውጥቷል። ስብሰባው ከመጠናቀቁ በፊት ትልቅና አዲስ ነገር አመላካች የሆነ ውሳኔ እንደሚያሰተላልፍ በተለያየ መልክ ሲጠቁም ቢከርምም፣ የመጨረሻው መግለጫ እንደሚያመለክተው ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካለፉት ጊዜያት የተለየ ተስፋ ሰጭ ነገር ይዞ አልመጣም። ይህ ደግሞ ሀገራችን ባለችበት ሁኔታና ሕዝባችን ለመብቱ መከበር እያሳየ ከሚገኘው ቆራጥነት አንፃር ሲታይ ገዥው ህወሓት-መራሹ ኢህአዴግ አሁንም ለሕዝባችን ብሶት፣ ለሀገር ደህንነትና ለአካባቢውም መረጋጋት ደንታ እንደሌለው፤ ከዚያም አልፎ ሥልጣኑን ይዞ ለመቆየት ደግሞ አፈናውን፣ ረገጣውን፣ ከፋፋይነቱን ባጠቃላይም ከፍተኛ ወንጀልን ከመፈጸም እንደማይመለስ አመላክቷል። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ … [Read more...] about መፍትሄው በብሄራዊ መግባባት የሽግግር ሂደትን እውን ማድረግ እንጂ ለ27 ዓመት የተደረገውን መድገም አይደለም