• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፎቶና ታሪኩ – እስረኞች [የህወሓት ግፍ ሰለባ ስለሆኑት ወገኖቻችን ሲባል ሊነበብ የሚገባው]

January 7, 2018 04:43 pm by Editor 3 Comments

{ፈላስፋ በወህኒ ቤት በራፍ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ አነበብኩ አለ፤ ይህች ቦታ የመከራና የጭንቅ ናት፤ ያልሞቱ (በሕይወት ያሉ) ሰዎች የሚቀበሩባት መቃብርም ናት። የወዳጆች መፈተኛ፤ የጠላቶች መደሰቻ የሆነች ቦታ ናትና።} አንጋረ ፈላስፋ (የፈላስፎች አነጋገር)፤ በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ በ1953 ዓ/ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተተረጎመ።
*************************************************************
በወያኔ አገዛዝ፤ በወያኔ ቀንበር
የካቴናው ስርስር የኮረንቲው ንዝር
የመቀመቅ ፍዳው የጨለማው እስር
የሰቆቃው ንረት የአውሬዎቹ ምንዝር
እንዴት እንደ ሆነ እንዴት እንደነበር
ፍትህ በሌለበት ለዳኛ ከመንገር
ጠበቃ ከማቆም ዕማኝ ከመደርደር
ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር።
ፎቶ፤ ሴፕቴምበር 14 2011 (እአአ)

የወያኔ ፀጥታ ሀይሎች አዲስ አበባ ላይ አንዱዓለም አራጌን በቁጥጥር ስር ሲያውሉ። እነሆ ከዚህ ቀን ጀምሮ ወጣቱ ትንታግ የሠላማዊ ትግል አራማጅ ፖለቲከኛ በወህኒ ቤት ይገኛል። ህግና ዳኛ ወያኔንና አገዛዙን ለመጠበቅ በቆሙባት ኢትዮጵያ ለህዝብ መብት፤ ነፃነት ፍትህና እኩልነት ተሟጋቹ አንዱዓለም አራጌ በሽብርተኝነት ህገ መንግሥቱን በሀይል ለመናድ በሚል በተመሰረተበት ክስ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በር ተዘግቶበታል። ዘረኞችና ዘራፊዎች ‘መንግሥት’ በሆኑባት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነትና ፍትህ ጠያቂነት ‘ሽብርተኝነት’ ሆኗል። ዳኞች እነሱ አቃቤ ህግ እነሱ ህጉም ለእነርሱ።

እነሆ በ2002 ዓ/ም (2010) ምርጫ ወቅት በህወሃት/ኢህአዴግ ገዢ ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተካሄደው ውይይት አንዱዓለም አራጌ ‘መድረክ’ን ወክሎ እንዲህ አለ፤ “ኢህአዴግ አንድም ቀን ስሜታዊ እንጂ ምክንያታዊ ውይይት አድርጎ አያውቅም። በመሰረቱ ኢህአዴግ አምባገነናዊ መንግሥት ነው። በግልፅ መነጋገር አለብን። የአምባገነንነቱ መሰረት ደግሞ ፍርሃት ነው። በሀገራችን ‘የፈሪ ዱላው አስራ ሁለት ነው’ ይባላል። ኢህአዴግ ፈሪ ስለሆነ የተለያዩ የፍርሃት ህጎችን እያወጣ የኢትዮጵያን ህዝብ ቀይዶ፤ ጫንቃው ላይ ተጭኖ ለመግዛት እየሞከረ ነው ያለው። ለምሳሌ በደርግ ጊዜ አንድ አዋጅ ወጥቶ ነበር፤ አዋጅ 767 የሚባል። ያነበበ ያስነበበ አሽሙር የተናገረ 15 ዓመት ይፈረድበታል ይላል። ዛሬ ኢህአዴግ የሚያወጣው የፀረ ሽብር ህግ ፤ የፓርቲዎች ሥነ ምግባር አዋጅ የኢትዮጵያን ህዝብ ለጉሞ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ህግ ነው። ኢህአዴግ ከ’97 ዓመተ ምህረት በሁዋላ የተማርኩት ነገር አለ ይላል። የተማረው አንድ ነገር ነው። በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግን እንደማይመርጠው ያውቃል። ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ሜዳውን ሁሉ ዘጋግቶ ለብቻው መሮጥ ይፈልጋል።

[የህወሓት ግፍ ሰለባ ስለሆኑት ወገኖቻችን ሲባል ሊነበብ የሚገባው]

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: eprdf, Ethiopia, Full Width Top, meles, Middle Column, political prisoners, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    January 10, 2018 02:48 am at 2:48 am

    በውነቱ መነጋገር ካስፈለገ: አንተማመንም እንጂ: ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሲሸፍት ያታሰሩ የጉራጌ ብሄረ ሰብ ወጣቶች ናቸው!! ለምሳሌ ያህል እስክንድር ነጋ: ዓንዱ አለም አራጌን ይጠቅሷል!!ከውጭ ማለትም ከሰሜን አሜሪካም ተደራጅተው ሙሉ ድጋፍ እያደረጉ ልማቱን ለማደናቀፍ የሚያደርጉት እነዚሁ ቡድኖች ናቸው:: ኢህአድግን ለማሳሰብ የምንፈልገው : ሁሉንም እስረኛ ባንዴ ወይም በጅምላ ከመልቀቅ እየተጠናና እየታየ ቢለቀቁ ለቅቆ ከማሳደድ ያግደናል::

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    January 10, 2018 03:10 am at 3:10 am

    ኢህአድግ!!! ሰድዶ ማሳደድ ካማረህ: ዶሮህን በቆቅ ለውጣት!!! ደጋግሞ ይታሰብበት!!!

    Reply
  3. Tesfa says

    February 4, 2018 06:57 pm at 6:57 pm

    አቶ ሙሉጌታ – በዘር የተቃመስክ ተውሳክ በመሆነህ እይታህ ሁሉ በዘር ዙሪያ ነው። ጉራጌዎች ሃገር አይሸጡም። ጉራጌዎች ሃገራቸውን፤ ህዝባቸውን የሚወድ በሃገራችን ውስጥ ጠንካራ ሰራተኛ እንደሆኑ የሚመሰከርላቸው ናቸው። ሰርተው ነው የሚከብሩት። እንደ ወያኔ በስርቆትና በዝርፊያ አይደለም። ግን እንዳንተ ያለ ጅል ይህ ሁሉ ነገር አይገባውም። የምትተነፍሰውና የምታስበው ወያኔ በገጠመልህ ሳንባና ጭንቅላት ነው።
    ከላይ የጠቀስካቸው በወያኔ ኢ-ፍትሃዊ ግፍ ሃበሳቸውን የሚቆጥሩት ስዎች በዘርና በጎሳ ቢሰለፉ ኑሮ ወያኔ አይነካቸውም ነበር። የሃገርን አንድነት፤ የወገንን መረገጥ በአደባባይ ወያኔን ተቃውመው ድምጻቸውን በማሰማታቸው ሰቆቃ ውስጥ ወያኔ ከተታቸው። ማሳደድ አንተን የመሰሉ የህዝባችን ተባዮች ነው እንጂ ከቆቅ ጋር ጥል ያለው ወይም ደሮውን በቆቅ የሚለውጥ ጅላ ጅል የለም። ገና ወያኔ ውሸቱን ሁሉን ፈትቼ እስርቤቱን ወደ መዝናኛ ቦታና የመጎብኛ መአከል አደርጋለሁ በማለቱ ይህን አምነህ ሰው እንዳይፈታ ምቀኛ መሆንህ ምንኛ ያሳዝናል። ልማት አደናቃፊው ወያኔ እንጂ ሌላ ሃይል አይደለም። ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ በማለት ሌላውን የሃገራችን ክፍል ራቁቱን ያስቀረ አጥፊ ድርጅት ነው። እንዲሁ በየድህረ ገጽ እየገባህ ነገር ታማታለህ። ግን ተነቅቶብሃል። ማንም አይሰማህም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule