ታዲያ ሁላችሁም ለምን ከሥልጣን አትወርዱም?
“ለአመጽ የግብረ መልስ የሚሰጥ አመራር እንጂ ለችግሮች ቀድሞ መፍትሄ የሚሰጥ አመራር አይደለም”፤ “አመራሩ ህዝቡ ከሚጠብቀው በታች ነው”፤ “አመራሩ ከሽፏል”፤ የማሸማቀቅና የማስፈራራት ተግባር ነው በፓርቲው ውስጥ ያለው፤ ተመሳሳይ ዓይነት ነገር ወደ ሕዝቡ ሰርጾዋል፤ ወዘተ በማለት “በድፍረት” የተናገረው የኦህዴዱ ለማ መገርሳ እንደዚህ ብቃት የሌለውን አመራር ቢያንስ “ሥልጣኑን መልቀቅ ይገባዋል” ሳይል ወይም ራሱ ሁኔታው የማይስተካከል ከሆነ ሥልጣኑን እንደሚለቅ ምንም ፍንጭ ሳይሰጥ ንግግሩን አብቅቷል።
ህወሓት/ኢህ አዴግ እንደ ድርጅት ከሽፏል! ይህ የተመሰከረው ደግሞ በራሱ በአመራሩ ነው። እስካሁን በሥልጣን ለምን እንደቆዩ እና ወደፊትም ለመቆየት ለምን እንዳሰቡ ግልጽ ቢያደርጉ የተሻለ ነው።
መለስም “እስከ እንጥላችን ገምተናል” እያለ ነበር ሞት እስኪነቅለው ሥልጣኑን የሙጥኝ ብሎ የቀጠለው። የለማን ንግግር ለማዳመጥ ከታች ያለውን ምስል ይጫኑ
ጎልጉል
(ፎቶ: የሶማሊ ክልል የህወሓት ተጠሪ አብዲ፤ ካሣ ተክለብርሃን እና ለማ)
Lemma says
Eyasebachihu new yemititsifut?
ለጥይበሉ says
የለማ መልስ እንደሚመስለኝ፡- “ለማን ተትቶ ይኬዳል? ዘላቂ መፍትሄ እስከሚገኝ ድረስ ውስጣቸው ሆኖ የከፋ ችግር እንዳያደርሱ መገደብ የተሻለ አይመስልህም። ስልጣኔን ብለቅ ወያኔ ማንን የሚተካ ይመስልሃል?“
እንደኔ እንደኔ ወያኔ በዛገ ቢለዋ ከሚገዘግዘን እንደለማ አይነቱ ከውስጥ ሆኖ በመጠኑ ቢሞርዱት ይሻላል። መታረዳችን ካልቀረ።