ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ምርጫ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በማለት የሰየመ የአሸባሪ ወንበዴዎች ቡድን አሁንም የውንብድና ተግባሩን እየፈጸመ ይገኛል። ይህ በዓለምአቀፋዊ የአሸባሪዎች መረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት የተመዘገበ ድርጅት በነጻ አውጪ ስም ሕዝብ ሲጨፈጭፍ፣ ሲያዋርድ፣ ሲያስር፣ ከአገር ሲባርር፣ ሲያፈናቅል፣ … የኖረ ድርጅት አሁንም በዚሁ ተግባሩ ቀጥሏል።
ዓላማ ብሎ የተነሣለትን አገር ማፍረስ የተቃወሙ፣ ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ የገለጹ በሙሉ አሸባሪ፣ ጸረ ልማት፣ ጸረ ህዝብ፣ … በማለት ሲገድልና ሲያሰቃይ ኖሮ አሁን ደግም “አላሰርኩም” ሲላቸው የነበረውን እስረኞች “እፈታለሁ” ብሏል። ይህ በህወሓት/ኢህአዴግ ስለተነገረው መግለጫ ጥቂት ነጥቦች ብቻ እናንሳ፤
በመጀመሪያ ኃይለማርያምና ጓደኞቹ በኢትዮጵያ ስም እና ስለ ኢትዮጵያ እየተናገሩ ኢትዮጵያን የሚወክል ሳይሆን የራሳቸውን “ጨርቃ ጨርቅ” ከኋላቸው አሰልፈው የወጡት ኅሊናቢሶች ናቸው። “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” የሚሉትን “ባለ ሰማያዊ ኮከቡን ባንዲራ” መድረኩ ላይም ይሁን ከኋላቸው ያለማድረጋቸው ንግግራቸው ስለኢትዮጵያ ሳይሆን ስለፈጠራቸው ህወሓት እንደሆነ በጉልህ የመሰከሩበት ነው።
ለዓመታት በመንግሥት ስም ሆነው ሲገድሉና ሲያስሩ፤ ከሟቹ መለስ ጀምሮ እስከ ኃይለማርያም ድረስ በአገር ውስጥና በውጪ “በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም” ሲሉ ቆይተው ዛሬ ከየት ያሰሯቸውን “የፖለቲካ እስረኞች” አምጥተው እንደሆነ ባታወቅም “እንፈታለን” ማለታቸው እስካሁን ያሰሩት በሙሉ የፖለቲካና የኅሊና እስረኛ መሆኑን በራሳቸው አፍ ያመኑበት ማስረጃ ነው።
ሲቀጥል እነዚህኑ “እንፈታቸዋለን” ያሉትን እስረኞች እንፈታለን ያሉት እንደ “መንግሥት” በመሆን ወይም የመንግሥት ሥራአስፈጻሚ አካል በመሆን ሳይሆን ኢህአዴግ በሚሉት ድርጅታቸው ስምና ውክልና ነው። አገሪቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚባል ጠቅላይ ሚኒስትር አላት ሲሉ የኖሩትን ያህል እርሱ እንደ መንግሥት ወኪልነቱ በአገሪቱ አስተዳደር ስም ሆኖ አለኝ በሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ መናገር ሲገባው መግለጫው የተሰጠው በድርጅት ስምና ዓርማ ነው።
ይህንን ሁሉ ሕዝብ ሲያስሩ የኖሩት “ሕገመንግሥቱን ለመናድ በማሰብ” እና “ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ ሲንቀሳቀሱ” ያገኘኋቸው “አሸባሪዎች ናቸው” በማለት ነበር። ስለዚህ ክሱ ሁሉ የተፈጸመው “በተከሳሹ”ና በ“መንግሥት” መካከል ነበር ለማለት ይቻላል፤ የበርካታ ክሶች ማስረጃ የሚመላክተው ይህንኑ ነው። ስለዚህ አሣሪው “መንግሥት” (ሥራ አስፈጻሚው) ነበር ቢባል ሐሰት አይሆንም። አሁን ግን “እፈታለሁ” የሚለው ያሰራቸው “መንግሥት” ሳይሆን ህወሓት/ኢህአዴግ ነው። በሌላ አነጋገር የታሰሩትም ሆነ ታስረው የተፈቱት፣ የሞቱት፣ የተሰደዱት፣ ወዘተ ወገኖቻችን በሙሉ ይህ ሁሉ መከራ የደረሰባቸውና የሚደርስባቸው ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር ስሙም መሆን ስላልቻሉ ነው ወደሚለው ድምዳሜ በቀላሉ መድረስ ይቻላል። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ ራሱ ህወሓት/ኢህአዴግና መግለጫው ነው!
ይህ በድርጅት ስም በገሃድ የተነገረ መግለጫ ግልጽ ሆኖ ሳለ የምዕራብ ሚዲያ ተቋማት በሙሉ ኃይለማርያም እንደመንግሥት ወኪልነቱ እስረኞችን እፈታለሁ አለ በሚል ዜናውን መሥራታቸው ትዝብት ላይ የሚጥል ብቻ ሳይሆን የሙያ ስነምግባር የጎደለው ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህ ድርጊት የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮኖች መሳተፋቸው እርምት ሊወስዱበትና ይቅርታ ሊጠይቁበት የሚገባ ነው እንላለን።
ይህ በአደባባይ የተሰጠ መግለጫ “እስካሁን ድረስ በአገራችን ላይ ለደረሰው ግፍ ማነው ተጠያቂ?” ለሚለው በጥሩ ማስረጃነት መቅረብ የሚችል ነው። ከዚህም ሌላ አራቱ ስዎች በአንገታቸው ላይ የመታነቂያ ገመድ እያስገቡበት እንደሆነ ራሳቸው ተረድተውታል ለማለት እንጠራጠራለን። የተናገሩትን በአጭሩ ለማስቀመጥ፤ “የተቃወሙንን፣ ከእኛ ጋር የማይስማሙትን፣ የፖለቲካ አመለካከታቸው ከእኛ የተለየውን በሙሉ ስንገድል፣ ስናስር፣ ስናሰቃይ፣ ከአገር ስናባርር፣ ወዘተ የነበረው እንደ መንግሥት የአገሪቱን ኅልውና አደጋ ላይ የጣሉ አሸባሪዎች በመሆናቸው ሳይሆን ለህወሓት/ኢህአዴግ አሜን ብለው እጅ እየነሱ መገዛት ያልፈለጉትን ሁሉ ነው። ስለዚህ የጸረ ሽብር ሕግ የሚል በማውጣት የቻልነውን ያህል ገድለናል፤ አስረናል፤ አዋርደናል፤ ከአገር አባርረናል፤ ይህንንም እንደ መንግሥት ፈጽመናል፤ ለዚህ ማስረጃ እንደ መንግሥት ያሰርናቸውን እንደ ድርጅት ለመፍታት መወሰናችን ብቻ ሳይሆን ይህንንም በአደባባይ በማስረጃ እንዲደረግ መወሰናችን ውስጣዊ ዴሞክራሲያዊ አሠራር መጀመራችንን ያሳያል። ሌላው መታወቅ የሚገባው ጉዳይ ባስፈለገ ጊዜ በየትኛውም ቦታ ነፍሰበላ አሳሪዎች መሆናችንን እንዲመሰከርብን የሚያስችል ማስረጃ እየሰጠን ነው። መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ጥቅጥቅ ጨለማ ነው”።
ህወሓት/ኢህአዴግ የቱንም ያህል ባህታዊ መስሎ ቢቀርብም ቀበሮነቱን ግን ሊክደው የማይችል ተፈጥሮአዊ ባህርዩ መሆኑን ራሱ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ ጠንቅቆ ያወቀው ጉዳይ ነው። ከ26 ዓመት ውሸትና ማጭበርበር በኋላ አሁንም “ኑ ላታልላችሁ” ማለት በረሃ ተወልዶ ያደገ “አራዳነት” ካልሆነ እብደት ነው የሚሆነው። ህወሓት/ኢህአዴግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በቃህ ብሎታል። በኢሬቻ በዓል ላይ “down down woyanne” እንዳለው ወጣት ህወሓት መውደም ነው ያለበት።
ጥያቄው አሁንም ግልጽ ነው! የሕዝብ ጥያቄ “የህወሓት የበላይነት ይቁም” የሚል ነው!!
ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።
Dawn Wejane says
It is about time these shit heads got to go!!!!
Mulugeta Andargie says
ጎልጉሎች!!! መቼም የዴሞክራሲ ጉዳይ ነውና:ካወያያችሁን በተገቢው መንገድ ለኛም ዕድል ስጡንና ሃሳባችንን እንግለጽ: ያገር ጉዳይ ነዋ!! ያለበለዚያ የአድሎ ሚዛናችሁ እየደፋ ሲሄድ እኛም ሆንን ታዛቢዎች ቋታችሁን ለመጠራረግ ሙሬ ፍለጋ መሯሯጥ እንዳይሆን:: ሽሙጥ:ቄንጥ:ሂስ:ማጣጣል ወዘተ ለተዋናይ አይነግሩም:: ከላይ የተጻፈውን ሃሳብ በሚገባ ለመተቸት እድሉ ስለተነፈገን ፍርዳችሁን ያለአድሎ እንትዳኙን እንጠይቃለን:: እኛም ሆንን እናንተ ለህዝብ መብት ታጋይ ነን ብለን ብዕር አንስተናል:: ያለፈውን ዝም ብለን እንለፈው::ጽሁፌን ሁሉ እንደ አለቃ ወይም እንደ የኔታ በየራስጌችሁ አትወችቁት:: መማማር ይኑር!! መማማር ካለ መሻሻል ይፈጠራል:: የሰብዓዊ መብት ጉዳይ እስከ ሰው ጓዳ ያስገባል::
Editor says
ምስጋና ቢስ ነህንጂ (ዱሮም ከካድሬ ከዚህ በላይ አይጠበቅም) ያንተን ያህል አስተያየት የተለጠፈለት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ምትናገረው ካለህ አሁንም ሥርዓት ይዘህ ጻፍ – መስመር ካለፍክ ግን ባትጽፈው ይሻልሃል። ታውቀዋለህና አንነግርህም። ያውም ፈጣሪ በሰጠው ጭንቅላት ሳይሆን በታፋው ከሚያስብ አእምሮ ቢስ ካድሬ ምንም ፋይዳ ያለው ነገር ባይጠበቅም።
ለማንኛውም ከእኛ የምትጠብቀውን “የመናገር ነጻነት” ያንተ ጌቶች ከ100 ሚሊዮን ሕዝብ ሲነፍጉና ለመንፈጋቸው ደግሞ እርግጠኛ ሆነው ሲናገሩ እኛም አንተም ሰምተናል። የሚገርመው ግን በሚኒሊክ ጊዜ የደነቆረ እንደሚባለው አንተና መሰል ካድሬዎች “ዘይት” እስኪቀየርላችሁ ድረስ ንግግራችሁ መልሶ መልሶ ነው። ቀጥልና አደንቁረን።
አርታኢ
Mulugeta Andargie says
እኔ መቼም ቢሆን ማጅራት መቺ ሆኜ አላውቅም!! ሃገር ቤት የለመዳችሁትን ባህሪ በተለምዶ ይዛችሁ ተጉዛችሁ እህቶቻችሁን ሚስቶቻችሁን ሳይቀር ለቅሌት ትጋብዙ ነበር!! ከዚህ የበለጠ ቅሌት የለም!! ሰውየው ከማይታወቅ ሃገር ሄዶ ዲስኩር ይደሰኩራል! ሰሚ አጣ!! ለካ እንደ ጅራት የተከተለው ስው ነበር!! ተዋረደ!! ቀለለ!! የዋሸው ሁሉ መሬትን አረጠበ!! አይገርምም?? በስርቆት አልተሰማራንም!!ሪኮርድ የለብንም!!! ኣንታማም!! ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት!! ብመለስ እኖራለሁ!! ካድሬነት ለውጥ ፈላጊነትን ያሳያል!! ኣንመነትፍም!!
Mulugeta Andargie says
ጎልጉሎች!! ለላይኛው ንግግር መልስ የሰጠሁትን የመልስ መልስ እየጠበቅሁ ነው:: ቀየው ሰላም ከሆነ ማራገቢያዬን ላንሳ!!
Mulugeta Andargie says
ጎልጉሎች!! እስከ አሁን የመልስ ምቱን ጠብቄ ነበር:ዳግም ስለ አለፈው ዘገባ ኣልመለስበትም::አፈጮ ሌውና ዘንካታው ነገሩን ተቀብሎታልና ነው:: ከእንግዲህ ቢቀባጥርም ወደ ኣረሙ ማሳ ኣልመለስበትም:: ግን እስቲ ስለሚጠላው ካድሬ ስራ ላንሳው!!ካድሬነት ሌብነትን:የከተማ ቅሚያን: ኪስ አውላቂነትን:ዝርፊያን ማጭበርበርን: ያለጥቅሙ በጩሀት የሌላውን ጥቅም ዘራፊ:የኮሚኒቲ አባወራነት:ባጠቃላይ በፊት የተነሳውን ቆርቁሮት ነጣቂ የስራ ውጤት አይደለም:: በተገኘው ለውጥ ተጠቅሞ ገስጋሽ መሆንን ይከጅላል:: በፊት በዳዩን ክፍል ስለሚያውቅ የእምነት ተቋማትን መጠለያው አያደርግም:: ስለ ባህል ለውጥና መሻሻል ያተኩራል::እኩልነትን ይሰብካል!! ተስፋን ያበስራል! መደጋገፍን ያስቃኛል:: በአስመራ ቀይ ሽብር አልተካሄደም(በምሳሌነት) ካድሬዎች ናቸው የተከላከሉት!!ካድሬ ወገናዊነቱ ለተጠቃሚው ነው!!
ወደ ጉዳያችን እንመለስ!!ከላይ የተጻፈውን ርእስ ለመተቸት ፈልጌ በዳሰሳ ብቻ እዘለዋለሁ!! ምክንይቱም ጸሃፊው ሊል የፈለገው ብያለሁና ነው!!ሴትዮዋ እንቅርቷን ታመመች ባሰባትና አይኗም ተደገመ!!የቱን ትታ የቱን ትታከም?? ዓይንም ዓይን ነው ጉሮሮም ጉሮሮ ሆነ!! ወይ ዓይኔ ትልጀመር!! ጉሮሮ አይብስ ብለሽ?? ታዛቢ ጣል አደረገባት!!
ግለሰቦች ዓይናውጣነትን ከተያያዙት ውለው አድራዋል!! ለነሱ ይሀ ጽሁፍ ፌዝ ነው!! የሚጽፉትም ባወጣው ያውጣው እንጂ ተቆርቋሪነት ገፋፍቷቸው አይደለም!! ጎልጉሎች!! ትዝብትን ሰንቁልን!! እንደ አዘጋጅም ይዳዳዋል!! የቦርድ አባልነው ልበል??ከጎሻሸመኝ ሰነባበተ!!በዘርም በእምነትም:በቀበሌም:በስራም:ጭራሽ ውር አንባባልም!! ፈሪ ፈራና ሆኖብኝ ጎልሎችን ተማጥኜ ዓይኔን እያሸሁ የሞት ሞቴን በወንጭፍ መልክ ሩሯን ወረወርኩ!! ወንድ!!በወንጭፍ!!!
In other way, he is trying to propagate as if he is tuoched or concerned to his community!! The slogan he showed us was imported by others!! He attracted with colorful but with a single person standing as if so many protestors were showed up!! Just a single man!! The flag could be from one the African countries!!
In his prose, he tried to blame the current government’s duties. Whenever you elaborate the sentences, you get no fruit or seed at all. As if he needed compensation from Golgul, and asking what he needed for, just insulting or abusing or degrading or undermining or discouraging the work of individuals with manner less way.
Looking or getting the sentences of his critics; in general, absolutely painless!!
Mulugeta Andargie says
ተዘግቼ መጥቼ ነበር ተከላከላችሁኝ!! ትቼላችኋለሁ!!የተሰባባረውን እንግሊዘኛዬንም አንብቡት!!ሻጥር በየፈርጁ ሆነብኝ!! ዳግም እድታነክስ አደርግህ ነበር!!!