በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ ስምምነትን የክልሎቹ መሪዎች ተፈራርመዋል።በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰላም እና የጋራ የልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል።ጽ/ቤቱ በሁለቱ ክልሎች 12 አዋሳኝ ዞኖችች ላይ ሰላምን በማስፈን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ጥናቶችን ይፋ አድርጓል።በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተዋቀረው የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ በቀጣይ በደቡብ፣ በጋምቤላ እና በቤቢሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለመተግበር ማቀዱን ነው የኦሮሚያ ክልል ያስታወቀው።የኦሮሞ እና ሱማሌ ሕዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት የተሳሰሩ እና ከ 1 ሺህ 872 ኪ.ሜ በላይ ወሰን የሚጋሩ … [Read more...] about የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
News
ዜና
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በሰፊው ታስቦ እንደሚውል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል።125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።በዓሉ ሲከበር በወረዳዎች በመሰረተ ልማት ቦታዎች ላይ የጀግኖች ስም የሚሰየም እንደሚሆንና የመደመር የኪነጥበብ ትርኢቶች እደሚዘጋጁ የምሁራንና የህዝብ የውይይት መድረኮችም እንደሚካሄዱአድዋን ለአባይ በሚል መሪ ሀሳብም የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳልም ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሰው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ወቅት ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት አከባበር መለያ አርማ (Logo) ይፋ አድርጓል፡፡የአርማው መግለጫ፦- ጋሻ ጎራዴና ጦር፦ አባቶቻችን ጠላትን የተዋጉባቸው የጦር መሳሪያዎች፤- … [Read more...] about 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
በመቀሌ ከተማ ከ350 ሚሊዮን በላይ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ክምችት እንዳለ የፌደራል መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ። በትግራይ ክልል የመድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ወደ ጤና ተቋማት ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ተነግሯል። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከሆነ በትግራይ ክልል ለ47 ጤና ተቋማት 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ ወደ ክልሉ በመድረስ የማሰራጨት አገልግሎት ማከናወኑን አስታውቋል። ቅርንጫፉ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 የጤና ተቋማት ግብዓቶቹን በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን በተለይም በመቀሌ ለሚገኙ 4 ሆስፒታሎች ለዉቅሮ፣ ሀውዜን፣ አዲግራት፣ አክሱም ቅድሰት ማርያም፣ ኮረምና ሌሎች ሆስፒታሎች መድሃኒቶችን አሰራጭቻለሁ ብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን እና በምዕራብ አንዲሁም በማዕከል በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች የመደበኛ እና የጤና … [Read more...] about በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
ዊንጉ አፍሪካ የተባለው በምስራቅ አፍሪካ በመረጃ ማዕከልነት ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው ድርጅት አዲስ አበባ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ውስጥ 15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያለው የመረጃ ማዕከል (ዳታ ሴንተር - Ethiopia’s first-ever Carrier-Neutral Hyperscale Data Center Park) ሊገነባ ነው።ዊንጉ አፍሪካ በተሰኘ ድርጅት የሚገነባው ማዕከሉ በቀጣይም ድርጅቱ ሁለተኛ ፕሮጀክቱን ከአዳማ ከተማ በ96 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ለመገንባት ዕቅድ እንዳለውም ተነግሯል፡፡የመረጃ ማዕከላቱ ግንባታ በፓን አፍሪካ ፕሮጀክት ስር የታቀፈው ዕቅድ አንዱ አካል ነው የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል በጂቡቲ እና በናይሮቢ ከተማዎች በተመሳሳይ ስራ ላይ ተሰማርቶ ስራዎችን የሰራ ቆይቷል ተብሏል። (Extensia- ENA) … [Read more...] about ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ድሮኖችን ለማምረት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ (ምንጭ Tikvah) … [Read more...] about ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ
የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመሥራች አባላት ጉዳይን አስመልክቶ ፓርቲው ያቀረበው የመሥራች አባላት ዝርዝር ላይ ቦርዱ 50 የሚሆን ናሙና በመውሰድ ያደረገው ማጣራት ስለ ትክክለኛነቱ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባው በመሆኑ፤ ቦርዱ ጉዳዩን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልኮት እንደነበር ይታወሳል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ባደረገው የማጣራት ሥራ ከሶማሌ ክልል 1145 መሥራች አባላት፣ ከአፋር ክልል 72 መሥራች አባላት፣ ከኦሮሚያ ክልል 23 መሥራች አባላት፣ ከአ.አ. ከተማ አስተዳደር 58 መሥራች አባላት በጠቅላላው የ1298 መሥራች አባላት በተጠቀሱት አድራሻ ያለመኖራቸውን ማረጋገጡን የሚያስረዳ መግለጫ በመስጠቱ የቦርዱም ሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ የማጣራት ሥራ የሚያሣየው ፓርቲው እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው በቃለመኃላ በተረጋገጠ ሰነድ ያቀረበው የመሥራች አባላት ሥም ዝርዝር … [Read more...] about የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ
ህወሓት ተሠረዘ!!!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህግ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ፥ ቁጥጥር እና ክትትል ነው። በመሆኑም በምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ፓርቲዎች የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሰረት ቀደም ብሎ መስፈርት አሟልተው ምዝገባቸው የተጠናቀቀ እና በሂደት ላይ ያሉ ፓርቲዎች ዝርዝርን ማሳወቁ ይታወሳል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም ውሳኔ ያልሰጠባቸው እንዲሁም የተጠየቁትን ማብራሪያዎች ያቀረቡ ፓርቲዎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል። 1. ቦርዱ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ወይ የሚለውን ሁኔታ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችን እና በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሃቆችን በማቅረብ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር … [Read more...] about ህወሓት ተሠረዘ!!!
ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው
ቦርዱ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሶስት ፓርቲዎችን ላይ በቦርዱ የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቀረቡ መረጃዎች እና ሌሎች ጥቆማዎች መሰረት ተጨማሪ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ስለእንቅስቃሴያቸው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል። ትእዛዝ የተሰጣቸው ፓርቲዎችም የሚከተሉት ናቸው። ሀ. “ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ዓዴፓ/”- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያሉ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በተካሄደ ህገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸው ለ. “ብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ /ባይቶና/” - በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያሉ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በተካሄደ ህገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸው እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች በአመጻ ተግባር በመሳተፋቸው ለቦርዱ መረጃ በመድረሱ ሐ. “ሳልሳይ ወያነ … [Read more...] about ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው
ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ
ትላንት የተደገደሉትን የህወሓት ቡድን አመራሮች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው መውሰድ እንደሚችሉ ብ/ጄ ተስፋዬ አያሌው በቪኦኤ ቀርበው ተናገረዋል። አመራሮቹ የተገደሉበት ቦታ ሩቅ እና በረሃ በመሆኑ መከላከያ የሁሉንም አስክሬን መልቀም እንደማይችልም አሳውቀዋል። ሰራዊቱም በእግሩ እየተጓዘ መሆኑ ገልፀዋል። በዚህ ተገቢ ባልሆነ ጦርነት ህይወታቸው እያለፈ የሚገኘውን አካላት ገበሬዎች እየቀበሯቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ብ/ጄ ተስፋዬ ፥ "የአመራሮችን አስክሬን ብንችል ብናመጣው ደስ ይለን ነበር" ብለዋል። በተጨማሪ ፥ ትላንት የተገደሉት አመራሮች ፎቶና ቪድዮ እንደሚደርሳቸው ገልፀው ካስፈለገ ይህን መስጠት ፣ በሚዲያ ማስተላለፍ ይቻላል ነገርግን በሚዲያ ሰው ገደልን ብሎ ማሳየት ከኢትዮጵያ ባህል አንፃር የማይሄድ እና የእርስ በእርስም ስለሆነ ይህን ማድረጉ ተቀባይነት … [Read more...] about ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ
ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው
“ስብሃትን “አቦይ” አልላቸውም … እንዲህ ዓይነት አባት አልመኝም” ጄኔራል ባጫ የጁንታው ፈጣሪና መሪ ስብሃት ነጋ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል። በርካቶችም ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር። ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል። ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግሥቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት” የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ … [Read more...] about ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው










