ዊንጉ አፍሪካ የተባለው በምስራቅ አፍሪካ በመረጃ ማዕከልነት ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው ድርጅት አዲስ አበባ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ውስጥ 15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያለው የመረጃ ማዕከል (ዳታ ሴንተር – Ethiopia’s first-ever Carrier-Neutral Hyperscale Data Center Park) ሊገነባ ነው።
ዊንጉ አፍሪካ በተሰኘ ድርጅት የሚገነባው ማዕከሉ በቀጣይም ድርጅቱ ሁለተኛ ፕሮጀክቱን ከአዳማ ከተማ በ96 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ለመገንባት ዕቅድ እንዳለውም ተነግሯል፡፡
የመረጃ ማዕከላቱ ግንባታ በፓን አፍሪካ ፕሮጀክት ስር የታቀፈው ዕቅድ አንዱ አካል ነው የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል በጂቡቲ እና በናይሮቢ ከተማዎች በተመሳሳይ ስራ ላይ ተሰማርቶ ስራዎችን የሰራ ቆይቷል ተብሏል። (Extensia- ENA)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply