ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የተገንጣዮች ጥርቅም፤ አዲስ የተመሠረተውን ብልጽግና ፓርቲ አልቀላቀልም ብሎ ካፈነገጠ ወዲህ ሁኔታዎች መስመር እየለቀቁበት ነው። ላሁኑ አጥር ላይ መንጠልጠሉን አማራጭ አድርጓል። እስካሁን በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው ትህነግ/ህወሓት መሪ የነበረው መለስ በሥልጣን በቆየበት ዘመን ሲዘልፋቸው የኖረውን ተቃዋሚዎች ባንድ ወቅት እንዲህ ብሏቸው ነበር፤ አጥር ላይ መሆንና አንድ እግር ከግቢ ውስጥ ሌላኛውን ከውጭ ማድረግ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ህወሓት ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ የመለስን አጽም ካላበት ቦታ እንዲላወስ ያደረገ ሆኗል። አንድ እግሯ መቀሌ፤ ሌላው እግሯ አዲስ አበባ … [Read more...] about ህወሓት/ትህነግ በአጥር ላይ
meles zenawi
መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ … [Read more...] about መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለውን የህወሓት ትዕዛዝ ተፈጻሚ ያደረገው ኦሞት ኦባንግ ሞቷል
በወንበዴው የህወሓት ቡድን ትዕዛዝ 424 አኙዋኮችን የጨፈጨፈው ኦሞት ኡባንግ ኡሎም ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ መሞቱ ታውቋል። ከመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በመቀበል ለ424 የአኙዋክ ተወላጆች የግፍ ዕልቂት ተጠያቂ የነበረው ኦሞት ኦባንግ በስደት በሚገኝበት ፊሊፒንስ ሞቷል። የሞቱ ምክንያት ኤችአይቪ ኤድስ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። ኦሞት ኦባንግ የዛሬ 15 ዓመት አካባቢ በታኅሳስ ወር ከህወሓት ሹሞች ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል ጭፍጨፋውን በፈጸመበት ወቅት የክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊ ነበር። ለዚህም ኢሰብዓዊ ድርጊቱ ሽልማት ይሆን ዘንድ የወንበዴው ህወሓት መሪዎች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾመውታል። ጋምቤላን እንደፈለገ ሲፈነጭባት የኖረው ኦሞት ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓም ጀምሮ ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ዜናዊ በላከው አስገምጋሚዎች ለሳምንት … [Read more...] about “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለውን የህወሓት ትዕዛዝ ተፈጻሚ ያደረገው ኦሞት ኦባንግ ሞቷል
መለስ በቆፈረው ጉድጓድ ሲዘከር
ይህ ቃለ ምልልስ “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ May 20, 2013 አትመነው ነበር። የኢትዮጵያን የውድቀት ጉድጓድ ሲቆፍሩ የነበሩትና በአገዛዝ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ጉድጓዱን በጥልቀት ሲቆፍሩ የነበሩት መለስ ከኢትዮጵያ ቀድመው ጥልቁ ጉድጓድ ገብተዋል። ዛሬ በሙት መንፈስ የሚመሩት “ተዝካራቸውን” የሚያወጡበት ቀን ነው። ለዝክሩ ይህንን ደግመን አቅርበነዋል። ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ … [Read more...] about መለስ በቆፈረው ጉድጓድ ሲዘከር