በታሪክ አጋጣሚ ከክልሉ ውጭ በሰፋትና በብዛት በኢትዮጵያ ተበትኖ የሚኖረው የዐምሐራ ሕዝብ ነው። ዛሬ የወለጋ ዐምሐራ፣ የኢሉአባቦር ዐምሐራ፣ የጋሞጎፋ ዐምሐራ፣ የከፋ ዐምሐራ፣ የሲዳሞ ዐምሐራ፣ የሸዋ ዐምሐራ፣ የአርሲ ዐምሐራ፣ የባሌ ዐምሐራ፣ የሐረር ዐምሐራ፣ የሶማሌ ዐምሐራ፣ የጋምቤላ ዐምሐራ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዐምሐራ፣ የአዲስ አበባ ዐምሐራና የድሬዳዋ ዐምሐራ ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል። ከዐምሐራ ክልል ውጭ የሚኖረው ዐምሐራ ሕዝብ ለዘመናት በሚኖርበት ቦታ ሁሉ ከአከባቢው ሕዝብ ጋራ ሰምና ፈትል ሆኖ ተጋብቶ፣ ተዋልዶ፣ በሥጋና በደም ተዋህዶ ኖሮአል። በቋንቋ፣ በባህል፣ በወግ፣ በሥርዓት እና በሀይማኖት ተስማምቶ ከሺህ ዓመታት በላይ በቤተሰብነት ክፉውንም ደጉንም በማሳለፉ በቀላሉ የማይፈርስ የወል ማንነት ገንብቷል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ … [Read more...] about ከዐምሐራ ክልል ውጭ ያለው የሰፊው ዐምሐራ ሕዝብ
Left Column
ከሠርቶ አደር ወደ ሰርቆ አደር፤ ነገስ
ወያኔዎች አገራችን ኢትዮጵያን ለ27 ዓመታት ሲያስርቡን ቆይተው፤ ጠ/ምኒስትር አብይ አህመዴና ኦቦ ለማ መገርሳ የአገራችን አትዮጵያን ስም ደጋግመው በመጥራት በመጠኑም ቢሆን ከርሃባችን ስላስታገሱን ምስጋና ቢገባቸውም፤ የዘርና የጎሳ ፖለቲካ ያመጣብንን ውርደትና ክስረት እያወቁ፤ ዘርና ጎሳን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ ስብስብ ማስቀረት ሲችሉ፤ በዚያው ለኢትዮጵያ ህልውና አስጊና፤ አጥፊ በሆነ ጎዳና እንዲቀጥል መፍቀዳቸው፤ (መፈለጋቸው) አንድም ተራው የ'ኛ ነው በሚል እሳቤ፤ ሁለትም ህወሃት እንዳይቀየማቸው ፈርተው ይሆን?! (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት … [Read more...] about ከሠርቶ አደር ወደ ሰርቆ አደር፤ ነገስ
THE WAY FORWARD: LET’S START TALKING TO EACH OTHER
Good Afternoon! “እንደምንአመሻችሁ”. I would like to thanks the president of Bahir Dar University, vice president, Dean of College of Social Science and the Humanities and other members of the staff. It is an honor to be at the Bahir Dar University, one of the great universities of Ethiopia, located in one of the most beautiful city and the capital of the Amhara National Regional State in Ethiopia. My speech today will consisted of both good and bad news. I will start with the bad news. We Ethiopians … [Read more...] about THE WAY FORWARD: LET’S START TALKING TO EACH OTHER
የዜጎች የፍትሕ ጥያቄ በሸገር – መቀሌ የፖለቲካ ጡዘት እንዳይጠለፍ!
የጠቅላይ ሚንስትሩ ጥረት ወንጀል ፈጽመው የተደበቁትን ብቻ ሳይሆን ወንጀል ፈጽመው በአደባባይ የሚንጎማለሉትንም ሆነ ወንጀለኞችን የሸሸጉትን መጨመር አለበት። ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት አሥርት አመታት የሰብአዊ መብቶች የተፈጸመው እና ሰዎች በግፍና አስከፊ በሆነ ሁኔታ እንዲሰቃዩ የተደረጉት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ነው። አድራጊዎቹም በሁሉም ድረጃ የሚገኙ ሹማምንት እና የጸጥታ ሰራተኞች ናቸው። የተለየ ቀለም፣ ዘር፣ ኃይማኖት ወይም ሌላ የማንነት መገለጫ የላቸውም። እንደተበዳዩ ስብጥር ሁሉ በደል አድራሾቹም የተሰባጠሩ ናቸው። በማዕከላዊ እስር ቤት ከተፈጸመው ባልተናነሰ መልኩ ከጋንቤላ እስከ ዑጋዴን፣ ከጎንደር እስከ ሞያሌ፣ ከአፋር እስከ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ከትግራይ እስከ ኮንሶ ባሉት የአገሪቱ ግዛቶች ሁሉ ግፍ በገፍ ተፈጽሟል። ይህን ሰፊ እና ውስብስብ ችግር … [Read more...] about የዜጎች የፍትሕ ጥያቄ በሸገር – መቀሌ የፖለቲካ ጡዘት እንዳይጠለፍ!
An Obstruction of Justice charge has yet to be filed against the TPLF’s Executive Committee Members
Author’s Note: This critic has nothing but love for the Tigrayan people; as such the writer doesn’t intend to diminish the Tigrayan people – who are one of Ethiopia’s umbilical cords – for the crimes the TPLF’s butchers committed against Ethiopians over the last forty years. In the author’s view, the TPLF’s elites and their interrogators inhuman acts don’t represent the Tigrayan peopleeven though the elites and their interrogators masquerade as Tigrayan-pride; instead they are a disgrace to the … [Read more...] about An Obstruction of Justice charge has yet to be filed against the TPLF’s Executive Committee Members
በቅርቡ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ይኖራሉ – የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የሥራ ኃላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር 102.1 እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል። የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል። ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ … [Read more...] about በቅርቡ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ይኖራሉ – የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
THE WAY FORWARD: CAN THE RIGHT CHANGE BE SUSTAINED IN ETHIOPIA?
Mr. Obang Metho, Executive Director, Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) will be a Guest Lecturer at The University of Gondar Lecture Title and Description: THE WAY FORWARD: CAN THE RIGHT CHANGE BE SUSTAINED IN ETHIOPIA? Ethiopia is in a state of great change. Many regard it as a miracle, a door that few believed could be opened, a glimmer of light that has resurrected hope for change that seemed impossible less than a year ago. This momentum for change has led to new freedoms and … [Read more...] about THE WAY FORWARD: CAN THE RIGHT CHANGE BE SUSTAINED IN ETHIOPIA?
የሰባት አመቷ ህፃን በፀሎት ብርሃኑ – ተሰርቃ፣ ተደፍራ በግፍ የተገደለች‼
ከጥቂት ቀናት በፊት በደሴ ከተማ አንድ የሰባት አመት ታዳጊ ለቀናት ከጠፋች በኋላ፤ ተገድላ መገኘቷን ተከትሎ የተቆጡ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር። በወቅቱ ታዳጊዋ ከመገደሏ በፊት መደፈሯን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተያያዘ ታዳጊዋን አስገድዶ በመድፈር የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል። አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ። በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል። የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ … [Read more...] about የሰባት አመቷ ህፃን በፀሎት ብርሃኑ – ተሰርቃ፣ ተደፍራ በግፍ የተገደለች‼
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሹመት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት ነገ ጠዋት 1:30 አዲስ አበባ ~ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ይደርሳሉ። ተወልደው ባደጉበት አዲስ አበባ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ሠፈር ለብርቱካን ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። ሪፖርተር በዘገበው መሠረት ብርቱካን “በመንግሥት ጥሪ ወደ አገር ቤት ጠቅልለው ከተመለሱ ምናልባትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር፣ ወይም የፌዴራል የመጀመርያ ወይም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተደርገው ሊሾሙ እንደሚችሉ ከወዲሁ ትንበያዎች እየተሰሙ ነው” ብሏል። ወ/ሪት ብርቱካን ወደ አዲስ አበባ ከመብረራቸው በፊት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በሰጡት አስተያየት “አገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ለመርዳት ማንም ሰው የሚችለውን ነገር ለማድረግ ወደ ኋላ የሚልበት ጊዜ አለመሆኑን በመረዳት እኔም በበኩሌ … [Read more...] about ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሹመት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ
ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ
ተጠናቀቀ በተባለው የጋምቤላ ክልል ግምገማ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ለመሾም የገንዘብ ኃይል ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑ ተሰማ። ግምገማውን እንዲመሩ የተመደቡት ግለሰቦች የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ምደባ በተመለከተ ከሌሎች ጋር በመሆን በገንዘብ ኃይል የሚፈልጉትን ለመሾም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ማለታቸውን ጠቅሶ በክልሉ የተንሰራፋውን ግፍና ሙስና (ሌብነት) በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ ካወጣ በኋላ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ለመሾም በታቀደው ድብቅ አጀንዳ ላይ ችግር መፈጠሩ ተሰምቷል። ለአሥር ቀናት የተካሄደውን ግምገማ የመሩትን በተመለከተ ጎልጉል ዘገባውን ሲያቀርብ “ግምገማውን እንዲመሩ ከፌዴራል መንግሥት የተወከሉት ፈቃዱ ተሰማ እና ተፈራ … [Read more...] about ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ