የመንጋ ፖለቲካ እና የመንጋ ፍትሕ የትም ሃገር ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። ተከስቶም ያውቃል። የዘርፉ ባለሙያዎች ዋነኛ ምክንያቱ "በተቋማት እና በመንግሥት የተቆጣ ሕዝብ፣ ከምሬት እና ከቁጭት የተነሳ ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ በሥሜት የሚወስደው በቀል አዘል "የፍትሕ ጥያቄ" ነው" ይሉታል። በዚያ መልኩ ስንረዳው መፍትሔው ቀላል ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንጋ ፖለቲካውን እና የመንጋ ፍትሕን በዋነኛነት በሕዝብን ይሁኝታ (ለመልካም እሴት በመገዛት) እና የጸጥታ ኃይሉ በሚወስደው እርምጃ ብቻ ለመቆጣጠር ማሰባቸው ግን ሙሉ አይመስለኝም። ነፃነትል መሸከም አለመቻል አድርጎ መሳላቸውም አልተመቸኝም። ብዙ ትክክለኛ ጥያቄዎች "በመንጋው" ተነስተዋልና። ይልቁንስ ሕዝቡ በለውጡ ላይ ከፍተኛ ተስፋን በመጣሉ ዝቅተኛው ካድሬ እና የአስተዳደር አካል ሕዝቡ የሚፈልገውን ለማድረግ አለመቻሉ ነው። … [Read more...] about የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ
Left Column
“እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት
ትውስታችሁን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ ካሁን በፊት እኔ የጻፍኳቸው፤ ጃዋር የተናገራቸውን ነጥቦች ላስታውሳችሁ። “ኦሮሞዎች ወደ ግንጣላ የሚመራቸው የመጀመሪያው ጉዞ አገባድደውታል” ጌታቸው ረዳ (3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ- 2015) “በማሃይም አዝማሪዎች እና በደደብ ምሁራን ጭንቅላት እየተመራችሁ የምታሽቃብጡ ኢትዮጵያውያን ሁላ የኦነግ እና የሻዕቢያ ባንዴራ ይዛችሁ መዝለል እና ማሽቃበጣችሁን ተው” (ጌታቸው ረዳ “የግንቦት 7 ጀሌዎች የኦነግና የሻዕያ ባንዴራ ማውለብልብ ብርቅ ሆኖባቸዋል- 2015) አሁን ደግሞ ጃዋርን ላስታውሳችሁ፡ “ኦሮሚያ በአፍሪካ ውስጥ እንደ ኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ብሔሮች የሚኖሩባት አካባቢ የለም። ምናልባት ጆሃንስ በርግ በስተቀር። ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ‘ብሔር’ ‘ብሄረሰብ’ የለም።ባሁኑ ወቅት … [Read more...] about “እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት
An afternoon with a quiet revolutionary
I spent a Saturday afternoon in Los Angeles attending a “Thank You” tour by my hero Andargachew Tsige upon his release from TPLF Woyane Gulag. To remind you how he became a prisoner - he was abducted in broad daylight from an International airport by Woyane security in collaboration with Yemen. It is a brazen act that broke many laws and conventions and it can only be carried by a regime that believes it was answerable to no one. It took its lawlessness into the international arena. It is not … [Read more...] about An afternoon with a quiet revolutionary
ታላቋ ኢትዮጵያ በተግባር
ባለፈው ቅዳሜ በባሌ ዞን ግንድር ወረዳ፣ ዳሎ ሰብሮ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ቤተ ክርስቲያን እያስመረቁ በነበሩበት ወቅት ሙስሊም ወንድሞቻቸዉ የኦሮሞን ህዝብ የባህል ምግቦች በመያዝ ቤተ ክርስቲያኒቷ ድረስ በመውሰድ አብረው በአንድነትና በፍቅር አስመርቀዋል። ከዚህ ሌላ 11,500ብር በመሰብሰብም ገቢ አድርገዋል። ታላቋ ኢትዮጵያ ማለት ይህች ናት፤ ኢትዮጵያዊነት በተግባር ሲገለጽ እንደዚህ ፍቅር ነው። (ምንጭ፤ Mereja.com የፌስቡክ ገጽ) … [Read more...] about ታላቋ ኢትዮጵያ በተግባር
አንዳርጋቸው ሳይሆን ኢ.ኤን.ኤን ኦሮማይ ሆነ
እ.ኤ.አ. በ2014፣ አንዳርጋቸው ጽጌ በህወሓት መንግሥት ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዮጵያ መወሰዱ በጣም ካስደሰታቸው አንዱ የኢ.ኤን.ኤኑ ብንያም ነበር። የበዓሉ ግርማን ኦሮማይ መጽሐፍ ርእስ ወስዶ “ኦሮማይ! ፀሓፊ፦ አዘነጋሽ ቦጋለ - ከሽሮሜዳ” የሚባል ትረካ ተረከበት። ከግንቦት ሰባት ፖለቲካዊ አቋም በተቃራኒ የተሰለፉ ፖለቲከኞች፣ አብዛኛው ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር፤ የህወሓት መንግሥትን የማፍያ ዓይነት ርካሽ ጠለፋ ሌት ተቀን ሲያወግዙ፤ ብንያም ጠላፊ አለቆቹን ለማስደሰት “እኔም ማረፍ አማረኝ” እና “በቃሉ የጸናው አንዳርጋቸው ጽጌ” እያለ በሌሎች ተከታታይ ትረካዎች ቀለደበት። በኋላም፣ የህወሓት መንግሥትን ማጅራት ጨምድደው ከግራ ቀኝ የሚያላትሙትን ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅቶች ዱካ እየተከተለ መሳደብን የሙሉ ጊዜ ሥራው አደረገው። ሻእብያን ለማጣጣል፣ ትግራይ ውስጥ … [Read more...] about አንዳርጋቸው ሳይሆን ኢ.ኤን.ኤን ኦሮማይ ሆነ
አብይ ምናችን ነው?
ለመነሻ፤ ሀ፦ “አሁንም…ኢትዮጵያ አንድ አብዮት ያስፈልጋታል። ልጆቿን የማይበላ አብዮት! ራሱን የማይውጥ አብዮት! ሳይንቲፊክ ሪቮሉሽን። በሳይንስና ቴክኒዮሎጂ የታገዘ አብዮት። ለውጥን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ የለም። ለውጡ ሆዳቸውን ከሚያጎልባቸው ጥቂቶች በቀር።” ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ በዴርቶጋዳ መፅሀፍ ላይ በ2001 ዓ/ም እንደፃፈው ወይም በራዕዩ እንዳስቀመጠው። እነሆ በሃያዎቹ መጀመሪያ ዕድሜው ላይ ይገኝ የነበረው ወጣቱ ባለራዕይ ደራሲ እንደታየው ሳይንሳዊው አብዮት፤ ልጆቹን የማይበላው አብዮት፤ ራሱን ውጦ የማያሳብጥና የማይፈነዳ አብዮት፤ በሳይንስና ቴክኒዮሎጂ ላይ የታገዘ/የሚታገዘው አብዮት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም የኢትዮጵያን መንበር ከህወሃት መዳፍ በይፋ ፈልቅቆ በወሰደው ሌላኛው ወጣት/ጎልማሳ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ በርግጠኝነት ተጀምሯል ማለት እንችል … [Read more...] about አብይ ምናችን ነው?
The way forward: challenges and opportunities for Ethiopia; truth and reconciliation
The ascendancy of Dr Abiy to the premiership in Ethiopia brings unprecedented, and to many fellow Ethiopians, unexpected hope and excitement to the possible formation of a democratic system in the country. The central galvanising messages are unity, forgiveness, love, inclusiveness (medemir) and a robust Ethiopian nationalism sentiment. There are some indications that various committees are working on a number of initiatives including the revision of the existing laws such as the terrorism and … [Read more...] about The way forward: challenges and opportunities for Ethiopia; truth and reconciliation
ይቅርታ! ከዜሮ በታች ከሆኑ ሰዎች ጋር አብረን አንደመርም !!
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ይቅርታ! ከዜሮ በታች ከሆኑ ሰዎች ጋር አብረን አንደመርም !!
ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
ቀደም ሲል በሃዋሳ፣ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተቀነባበረ ሁኔታ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ፣ በቤኒሻንጉል በተለያዩ ቦታዎችና በተለይም በአሶሳ የደረሰንና እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥራት ጭፍጨፋ፣ ሕዝብ ወደ ምሬት እንዲሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ በጥሞና ለምትከታተሉ ሁሉ፤ በባህር ዳር ለጠቅከላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ቀና ተግባርና የለውጥ ሩጫ እውቅና ለመስጠት የተጠራውን ሰልፍ ለማወክ ከወዲሁ ቦንብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለሰማችሁ፣ የደኅንነት ኃይሉን ትብትብ በወጉ ለምትረዱና ለምትገነዘቡ፤ በተለያዩ የአገሪቱ የልማት ተቋማት ላይ የሚፈጸመውን የኢኮኖሚ አሻጥር በውል ለምትከታተሉ፤ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚሸረቡ ተንኮሎችን ለምታጤኑ፤ ለውጡ እንዲኮላሽና አገሪቱ ወደ ትርምስ ውስጥ እንድትገባ በተሸናፊነት ውስጥ ሆነው ለጥፋት የሚመደበውን በጀት ለምትሰሙ … [Read more...] about ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
አሸባሪው ህወሃት
“ዘረኛ ከሆንክ የዓለማችን ርካሽ ሰው አንተ ነህ” ሠኔ 16 ቀን (ዕለተ ትንሣኤ) 2010 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድንና የባልደረቦቹን የለውጥ እርምጃ ለማመስገንና ለመደገፍ በሚሊዮን የሚቆጠረው ህዝብ በመስቀል አደባባይ ይዞ ከወጣቸው መልዕክቶች መካከል አንዱ። “…መግደል መሸነፍ ነው። መግደል መዋረድ ነው። በደስታ አንድ ሆኖ ሀገሬን የሚልን ህዝብ በራሱ ዜጋ ሠዎች አቅዶ አስቦ እንዲጨነግፍ መሥራት ትንሽነት ነው። ኢትዮጵያውያን ግን ትንሽ አይደለንም። ትልቅ ህዝቦች ነን። ከትንንሾች ጋር ወርደን ትንሽ አንሆንም። ይህንን ቀን ደስታችንን ለማጨለም፤ ፍቅራችንን ለማጨለም፤ አንድነታችንን ለማደፍረስ ያሰባችሁ ሃይሎች አልተሳካላችሁም።…ትላንት አልተሳካላችሁም። ዛሬ አልተሳካላችሁም። ነገም አይሳካላችሁም…” ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ሠኔ 16/2010 ዓ/ም በእርሱና … [Read more...] about አሸባሪው ህወሃት










