እ.ኤ.አ. በ2014፣ አንዳርጋቸው ጽጌ በህወሓት መንግሥት ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዮጵያ መወሰዱ በጣም ካስደሰታቸው አንዱ የኢ.ኤን.ኤኑ ብንያም ነበር። የበዓሉ ግርማን ኦሮማይ መጽሐፍ ርእስ ወስዶ “ኦሮማይ! ፀሓፊ፦ አዘነጋሽ ቦጋለ - ከሽሮሜዳ” የሚባል ትረካ ተረከበት። ከግንቦት ሰባት ፖለቲካዊ አቋም በተቃራኒ የተሰለፉ ፖለቲከኞች፣ አብዛኛው ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር፤ የህወሓት መንግሥትን የማፍያ ዓይነት ርካሽ ጠለፋ ሌት ተቀን ሲያወግዙ፤ ብንያም ጠላፊ አለቆቹን ለማስደሰት “እኔም ማረፍ አማረኝ” እና “በቃሉ የጸናው አንዳርጋቸው ጽጌ” እያለ በሌሎች ተከታታይ ትረካዎች ቀለደበት። በኋላም፣ የህወሓት መንግሥትን ማጅራት ጨምድደው ከግራ ቀኝ የሚያላትሙትን ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅቶች ዱካ እየተከተለ መሳደብን የሙሉ ጊዜ ሥራው አደረገው። ሻእብያን ለማጣጣል፣ ትግራይ ውስጥ … [Read more...] about አንዳርጋቸው ሳይሆን ኢ.ኤን.ኤን ኦሮማይ ሆነ