• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ

August 20, 2018 05:25 am by Editor Leave a Comment

የመንጋ ፖለቲካ እና የመንጋ ፍትሕ የትም ሃገር ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። ተከስቶም ያውቃል።  የዘርፉ ባለሙያዎች ዋነኛ ምክንያቱ “በተቋማት እና በመንግሥት የተቆጣ ሕዝብ፣ ከምሬት እና ከቁጭት የተነሳ ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ በሥሜት የሚወስደው በቀል አዘል “የፍትሕ ጥያቄ” ነው” ይሉታል።
በዚያ መልኩ ስንረዳው መፍትሔው ቀላል ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንጋ ፖለቲካውን እና የመንጋ ፍትሕን በዋነኛነት በሕዝብን ይሁኝታ (ለመልካም እሴት በመገዛት) እና የጸጥታ ኃይሉ በሚወስደው እርምጃ ብቻ ለመቆጣጠር ማሰባቸው ግን ሙሉ አይመስለኝም። 

ነፃነትል መሸከም አለመቻል አድርጎ መሳላቸውም አልተመቸኝም። ብዙ ትክክለኛ ጥያቄዎች “በመንጋው” ተነስተዋልና። ይልቁንስ ሕዝቡ በለውጡ ላይ ከፍተኛ ተስፋን በመጣሉ ዝቅተኛው ካድሬ እና የአስተዳደር አካል ሕዝቡ የሚፈልገውን ለማድረግ አለመቻሉ ነው። በዚህ ረገድም የፍትሕ ሥርዓቱ መሉ በሙሉ የፍትሕ ሥራን ሠርቶ ሕዝብን አገልግሏል ለማለት አያስደፍረም።

የመንጋ ፍትሕ ሌላ ምክንያቱ የዳሸቀ የፍትሕ አካላት ቅቡልነት እና ተዓማኒነት እንደሆነ ይገለፃል። (ሌላ ምክንያት ሊኖረው እንደሚችል ቢታወቅም)

ለረጅም አመታት የፖለቲካ ድርጅት ጠበቃ የነበረው የፍትሕ ዘርፉ አሁንም አንድም የተጠያቂነት አሠራርን ሳያሰፍን (ቢያንስ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ ሳይፈታ፣ የማጎሪያ ቤት አሰቃይ የነበሩ ባለሥልጣናት ላይ ምንም ምርምራ ሳያደርግ) እንዴት ቅቡል እና ተዓማኒ ይሆናል፤ ሕዝቡስ እንዴት “የኔ ፍትሕ ሰጪ” ብሎ ይወሰደው?

Securitization and appealing to unbridled and unprincipled “forgiveness” will be inadequate. Appropriately recognizeing popular demand and making more delivery accordingly is a necessity. 

በሌላ በኩል የመንጋ ፍትሕ ተጨባጭ ምንክያት ዝቅተኛው ካድሬ አለመታደሱ (“አለመደመር”) ነው። ሙሰኛ ዞን እየቀተቀየረለት መሾሙ ነው። ከፍተኛው የሙስና አባቶችም “አለመደመር” ነው። ….…መደመር ማለቴ መቀነስ።

በሌላ በኩል ግን ጥሩ መልዕክት ነው…ሁለት ነጥቦችን ልጨምር.

፩. የጥንት የመልካም እሴቶች እና ሥነ መንግሥት እንደነበሩን ገልጸው ነበር። እጅግ በጣም ጥሩ ነው። ግን እነዚህ እሴቶች እና ሃገር በቀል የሆኑ የመንግሥት ሥርዓቶችን አንኮታኩተው ያደከሙት እና አንዴ ፊውዳል ሌላ ጊዜ ኮሚዩኒኒዝም፣ ሶሻሊዝም እና ካፒታሊዝም (ዴሞክራቲክ ዴቬሎፕመንታል ስቴት LOL) እያሉ ሀገሩን ወደ “STATE” ማሳደግ እንኳን ያቃታቸው ይዚሁ ሃገር ፖለቲከኞች ናቸው (ኢሕአዴግን ጨምሮ)።

፪. “አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚንማኅበረሰብን መፍጠር” ያሉትን ሰማሁት። ይህ ሐረግ በሕገ መንግሥቱ መቅድም ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የቡድን እና የግል መብት ተከብረውላቸው፣ የጋራ ጥቅም ተከብረውላቸው፣ ሠላም እና ዴሞክራሲ የሠፈነበት ሀገርን በጋራ መመሥረትን እንዲህ ብሎ ይገልፃል
” .….መጪው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል…. ”
የሕገ መንግሥት ባለሙያ ስላልሆንኩ ብዙም አስተያየት ባልችልም ግን ባለፉት 27 ዓመታት በዚህ ረገድ ምንል እንዳልተሠራ ለመናገር አሁን ያለንበት እርስበርስ ያለን ጥላቻ፣ መነቋቆር፣ መገዳደል ማየቱ በቂ ነው።

ምን ለማለት ፈልጌ ነው?

“አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ”…ወይም በቀላሉ STATE ለመገንባት ብዙ ርቀት ይቀረናል…የጠቅላይ ሚኒስትሩም ትልቅ ፈተና እንደሚሆን አስባለሁ። 

Tactical Alliances (ካለ LOL)  ወደ strategic integration ይደጉ፤ እንትግሬሽንም አቃፊ ይሁን፣ ኢኮኖሚው ይነቃቃ፣ የሥራ ዕድል ይፈጠር፣ ያኔ መንጋ በሥራ ይጠመዳል (የፌስቡክ መንጋንም ጨምሮ)።
ግን ግን ቆይ የሕዝባዊ አመጹ ዋነኛ ጥያቄ ምን ነበር?

(እኔ ራሴው እንዳልረሳው ለማስታወስ ያህል ነው እንጅ እርስዎ “ጊዜ” ብለዋል)።

ከምንም በላይ ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ  ኢሕአዴግን ማስተዳደር፣ መለወጥ ይቅናዎት። ካልሆነም እሱ ግትር ሆኖ አልቃና ብሎ ሲሰበር ኢትዮጵያን አደራ።

መንግሥቱ አሰፋ ነኝ

መልካም ቆይታ

(ፎቶ፤ የመንጋ ፍትሕ በታንዛኒያ ለማሳያ የቀረበ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule