• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሹመት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ

November 7, 2018 12:29 pm by Editor 1 Comment

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት ነገ ጠዋት 1:30 አዲስ አበባ ~ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ይደርሳሉ። ተወልደው ባደጉበት አዲስ አበባ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ሠፈር ለብርቱካን ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።

ሪፖርተር በዘገበው መሠረት ብርቱካን “በመንግሥት ጥሪ ወደ አገር ቤት ጠቅልለው ከተመለሱ ምናልባትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር፣ ወይም የፌዴራል የመጀመርያ ወይም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተደርገው ሊሾሙ እንደሚችሉ ከወዲሁ ትንበያዎች እየተሰሙ ነው” ብሏል።

ወ/ሪት ብርቱካን ወደ አዲስ አበባ ከመብረራቸው በፊት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በሰጡት አስተያየት “አገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ለመርዳት ማንም ሰው የሚችለውን ነገር ለማድረግ ወደ ኋላ የሚልበት ጊዜ አለመሆኑን በመረዳት እኔም በበኩሌ ባለኝ አቅም፣ በሞያዬ፣ በልምድና በዕውቀቴ የምችለውን ለማዋጣት እና ያም ምን እንደሚሆን ለመወያየት ነው የምሄደው። በጣም ጥሩ ቀን ነው ለእኔ” ብለዋል።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የፌዴራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬ “ወደ አገራቸው ተመልሰው በሕግም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ለአገሪቱም ለሕዝቡም ባላቸው ዕውቀትና ልምድ አስተዋጾ ማበርከት ፈልገው መምጣታቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። … በአገሪቱ በሚካሄደው እንቅስቃሴ እንዲያግዙ እንፈልጋለን። አብረናቸው ለመስራትም ዝግጁ ነን” ብለዋል። እኛም አብረናቸው ለመስራት ዝግጁ ነን።”

ጎልጉል ያነጋገራቸው የዐቃቤ ሕግ መ/ቤት ባለሙያ ደግሞ ብርቱካን ለቪኦኤ ከሰጡት መግለጫ እና ከሌሎች ባለን መረጃ መሠረት የምርጫ ቦርድን ወይም የሰብዓዊ መብቶችን ኮሚሽንን ይመሩ ይሆናል የሚል ከፍተኛ ግምት አለ። የጠቅላይ ፍርቤት ፕሬዚዳንቷ ሴት በመሆናቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤትም በከፍተኛ ኃላፊነት ሌላ ሴት ለመሾም የሚያስችል ክፍተት ቢኖርም ወ/ሪት ብርቱካን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሕግ ካለመሥራታቸው ጋር ተያይዞ ከሕግ ሥራ ለ13 ዓመታት ተለይተው በመቆየታቸው በፍርድ ቤት አካባቢ የመሾማቸውን ዕድል ያጠበዋል ይላሉ።

ሪፖርተር እንደ ዘገበው፤ “ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1988 ዓ.ም. በሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ወ/ሪት ብርቱካን፣ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆንም ከ1989 ዓ.ም. እስከ 1990ዎቹ አጋማሽ ድረስ ከመሥራታቸውም በተጨማሪ፣ ለእስር እስከተዳረጉበት ጥቅምት ወር 1998 ዓ.ም. ድረስ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሆነው ሠርተዋል። … ወ/ሪት ብርቱካን ከእስር እንደተፈቱ ወደ አሜሪካ ሄደው ላለፉት ሰባት ዓመታት ቆይተዋል። በቆይታቸውም በታዋቂው ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ማግኘታቸው ታውቋል”።

(ፎቶዎቹ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ናቸው)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News Tagged With: birtukan, Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. gi Haile says

    November 8, 2018 03:10 am at 3:10 am

    መልካም ዜና ለወ/ሮ ብርቱካን እንኳንም ደስ ኣሎት። አገራችን ጠንካራ መሪዎች የምትፈልግበት ጊዜ ነው። በጠማማ ትውልድ ውስጥ መልካም ሥነምግባርና መልካም መሪዎች አስተማሪዎች የሚያስፈልጉበት ጊዜ ነው። የዘረፋና በለቤት ኣልባ የነበረችውን ኢትዮጵያ በንፁህ ታታሪና ታማኝ ልጆችዋ ተመልሳ በመልካም መሠረት ላይ ትታነፃለች። ሌቦችና ወንበዴዎች የአገራችን ጣላት ሆነው ሲዘርፉና ሲያዘርፉ ቆይተው ተመልሰው ወደ ጫካ ተመልሰዋል ። ዛሬ የአገር አድን ጥሪ መመለስ የሚችሉት የመከራውን ገፈት የቀመሱት ለፍትህ ሲሉ ዋጋ የከፈሉት ዛሬ ሊካሱና የተገደሉለት ፍትህ በእግሩ እንዲሄድና ለምድራችን ተሰፋ እነዲሆን ታላቅ ምኞታችን ነው። የሰላም ፣ የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የእኩልነት ድምፅ አሁንም ፍትህ ሙሉ በሙሉ እስኪሰፍን ድረስ ትግሉን በአገርና በውጭ ይቀጥላል ። ፍትህ ለመላው የኢትዮጵያና ለሰው ልጆች በሙሉ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule