ከጥቂት ቀናት በፊት በደሴ ከተማ አንድ የሰባት አመት ታዳጊ ለቀናት ከጠፋች በኋላ፤ ተገድላ መገኘቷን ተከትሎ የተቆጡ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር። በወቅቱ ታዳጊዋ ከመገደሏ በፊት መደፈሯን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተያያዘ ታዳጊዋን አስገድዶ በመድፈር የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል። አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ። በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል። የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ … [Read more...] about የሰባት አመቷ ህፃን በፀሎት ብርሃኑ – ተሰርቃ፣ ተደፍራ በግፍ የተገደለች‼