• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ

November 2, 2018 07:24 pm by Editor 3 Comments

ተጠናቀቀ በተባለው የጋምቤላ ክልል ግምገማ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ለመሾም የገንዘብ ኃይል ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑ ተሰማ። ግምገማውን እንዲመሩ የተመደቡት ግለሰቦች የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ምደባ በተመለከተ ከሌሎች ጋር በመሆን በገንዘብ ኃይል የሚፈልጉትን ለመሾም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ማለታቸውን ጠቅሶ በክልሉ የተንሰራፋውን ግፍና ሙስና (ሌብነት) በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ ካወጣ በኋላ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ለመሾም በታቀደው ድብቅ አጀንዳ ላይ ችግር መፈጠሩ ተሰምቷል።

ለአሥር ቀናት የተካሄደውን ግምገማ የመሩትን በተመለከተ ጎልጉል ዘገባውን ሲያቀርብ “ግምገማውን እንዲመሩ ከፌዴራል መንግሥት የተወከሉት ፈቃዱ ተሰማ እና ተፈራ ድሪቦ ግምገማው ከመጠናቀቁ በፊት በጋትሉዋክና በሰናይ ምትክ ዑመድ ኡጁሉ የጋህአዴን ሊቀመንበር፤ ታንኩዌይ ጆክ ምክትል አድርገው አስመርጠዋል። ሆኖም ሁለቱ ከፌዴራል የተወከሉትን የግምገማ መሪዎች በርካታ የተዓማኒነት ጥያቄዎች የሚቀርብባቸው ብቻ ሳይሆኑ ምናልባትም የጋትሉዋክን ዓላማ በማሳካት ሰፊ ሚና የተጫወቱ ናቸው ተብለው በአንዳንዶች ዘንድ ይወቀሳሉ” ብሎ ነበር።

ግምገማው ከመጠናቀቁ በፊት የግምገማው መሪዎች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሹመት መወሰን አለበት በሚል ያቀረቡት አጀንዳ በስብሰባው ላይ ከፍተኛ አለመግባባትን ፈጥሮ እንደነበር ጎልጉል ከተሰብሳቢዎቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፈቃዱ ተሰማ እና ተፈራ ድሪቦ የተባሉት የግምገማው መሪዎች የጋትሉዋክ ሚስት ወንድምና የፓርቲው (ጋሕአዴን) ምክትል ሊቀመንበር እንዲሆኑ የተመረጡትን ታንኩዌይ ጆክ ሮምን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፤ የፓርቲውን ሊቀመንበር ዑመድ ዑጁሉን ደግሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆኑ ሃሳብ ያቀርባሉ።

ይህንን ከአሠራር ውጪ የሆነ ሃሳብ ከሊቀመንበሩ ሌላ የስብሰባው ተሳታፊዎች አጥብቀው ይቃወማሉ። ያቀረቡትም መከራከሪያ በኢህአዴግ ድርጅታዊ አሠራር መሠረት የፓርቲው ሊቀመንበር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሆናል፤ ሆኖም ሊቀመንበሩ በፌዴራል ደረጃ ከፍተኛ ሥልጣን ካለውና ክልሉን ማስተዳደር የማይችል ከሆነ ብቻ ነው ምክትሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚሆነው፤ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሶማሊ ክልሎች የተደረገው ይኸው ነው፤ ከዚህ ውጪ የሆነ ምደባ በጋምቤላ ማድረግ ሕዝቡን መናቅ ብቻ ሳይሆን ክልሉን ለከፍተኛ ብጥብጥ የሚዳርግ ነው፤ ሕዝቡ የሚፈልገው መሪ ሊሾምለት ይገባል የሚል ነበር።

በዚህ ወቅት የግምገማው መሪዎች ወደ ክልላችሁ ሄዳችሁ ከሕዝባችሁ ጋር ተነጋግራችሁ ጉዳዩን ፍቱት በማለት ለግምገማ የተጠራውን ስብሰባ ያጠናቅቃሉ። ከግምገማው መጠናቀቅ በኋላ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አዳዲሶቹ የፓርቲው አመራሮች ሂስና ግለሂስ ማድረጋቸውን ገለጾ “በዚህ መሠረት ሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እስከሚቀጥለው ጉባዔ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሲያግድ አንድ የሥራ አስፈፃሚ አባልን ደግሞ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲወርድ” መወሰኑን አስታወቀ።

የድርጅቱ መግለጫ ይፋ ከሆነ በኋላ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ከድርጅቱ የታገዱትና እርምጃ የተወሰደባቸው አባላት እንደተባለው በሂስና ግለሂስ ምክንያት ሳይሆን ኢፍትሓዊ የሆነውን የርዕሰ መስተዳድር አመዳደብ የተቃወሙ ነበሩ። ከህወሓትና ከሌሎች በርካታ በጥቅም ከተሳሰሩ ጋር የተወሳሰበውን የጋትሉዋክን አመራር በሌላ መልኩ ለማስቀጠል የተቀነባበረ ሤራ አንዱ አካል እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። እነዚህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አጠራር “ሌቦች” የሚባሉትና “የሌብነት” ሥራቸው እንዳይጋለጥ የሚፈልጉ በአገር ውስጥና በውጪ የሚገኙ ኃይሎች፤ በጋምቤላ የሚፈለገው ለውጥ እንዳይመጣና አሁንም በግፍና በሌብነት የተሳሰረው ሠንሠለት እንዳይበጠስ እስከ 10 ሚሊዮን ብር እንደመደቡ ይህንንም ለአስፈጻሚዎቹ እንዳስረከቡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።

የጋሕአዴንን ምክትል ሊቀመንበር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለማድረግ የታቀደው ሤራ ከከሸፈ በኋላ አዲሶቹ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንደሚፈለጉና ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ጥሪ ይደርሳቸዋል። ጥሪው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ዕውቅና ውጪ የተደረገ መሆኑን ሊቀመንበሩ ዑመድ ኡጁሉ ያውቁት አዲስ አበባ ሲደርሱና የስብሰባው ገምጋሚዎች ከሌሎች ወታደራዊና የደኅንነት አባላት ጋር ጠርተው ሲያነጋግሯቸው ነው።

ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉት አመራሮች በተለይ ሊቀመንበሩ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ይህም ዋንኛ ምክንያት ምክትል ሊቀመንበርና የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትን ታንኩዌይ ጆክ ሮምን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆኑ እንዲቀበሉ ሲሆን ሊቀመንበሩ ግን በአቋማቸው ፀንተዋል። ከሕዝባቸውና ከፓርቲው አሠራር ውጪ የሚደረገውን ምደባ እንደማይቀበሉ ለተናገሩት ሊቀመንበር ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ተሰጥቷቸው ቅዳሜ ጥቅምት 24፤ 2011 ለሌላ ስብሰባ እንዲመጡ ተነግሯቸው ከስብሰባው ወጥተዋል።

ይህንን በጋምቤላ ሕዝብ ላይ ያለፍላጎቱ ለማስቀጠል የሚደረገው የህወሓትና የለውጡ ተቃዋሚዎች ሤራ በፌዴራል መንግሥቱ ቀጥተኛ ጣልቃገብነት ካልተቀለበሰ በክልሉ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትል ጎልጉል ያነጋገራቸው የክልሉ የቀድሞ አመራር ሥጋታቸውን ይገልጻሉ። በሌሎች ክልሎች በተለይ በሶማሊ ክልል ከተደረገው ያነሰ በጋምቤላ እንዲሆን መፍቀድ ለዓመታት መሬቱን እየተነጠቀ፣ ግፍ እየተፈጸመበት የኖረውን የጋምቤላ ሕዝብ ወገብ የሚሰብር ብቻ ሳይሆን ግፍ የመረረውን የክልሉን ወጣት ላልተፈለገ አመጽ መጋበዝ ነው ሲሉ እኚሁ ሰው ይናገራሉ። ከደቡብ ሱዳን ጋር የተቆራኘው የጋምቤላ ጉዳይ የክልሉን ሕዝብ ፍላጎት በሚያረካ መልኩ ካልተጠናቀቀ አሁንም በግፍ፣ በጉቦ፣ በማስፈራራትና በዛቻ የሚደረገው አሠራር በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ገና በሁለት እግሯ ባልቆመችውን ደቡብ ሱዳንና በቀጣናው ከፍተኛ አለመረጋጋት እንደሚፈጥር በብዙዎች ይታመናል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Filed Under: News Tagged With: Gambella, gatluak, Left Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. ምንውየለት ፈንቴ says

    November 3, 2018 06:32 am at 6:32 am

    መቸ ነው ሃገሩ የባላገሩ የሚሆነው? ከዚህ ቀደም በጋምቤላ በ”የሠላምና የዲሞክራሲ ኮንፈረንስ” ስም በመጀመሪያ በአቶ ተፈራ ዋልዋ መሪነት የመጀመሪያው የክልሉ ፕሬዚደንት ከሥልጣን ወርደው ለእሥር ተዳርገዋል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በአቶ አባይ ፀሐዬ መሪነት እንዲሁ ግምገማ ተደርጎ የክልሉ መሪዎች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡ እነሆ አሁን ደግሞ ሌላ ዙር ሹም ሽር፡፡ ከመሃል አገር ገምጋሚ ወደነዚህ ክልልሎች እየተላከ እስከመቼ ይሆን አውጪና አውራጅ የሚሆነው? በክልሉ የሚገኙ ፊደል የቆጠሩ ተወላጆች አሥር ወይ ሃያ አይሞሉም ማለት ነው? እነርሱ ስለሕዝባቸው ግድ የሚላቸው መቸ ነው? ቆም በለው የሚያስቡት መቸ ነው? ለነገሩ ጋምቤላ ብቻ ሣይሆን እንዲህ ዓይነት ተመሣሣይ ተግባራት በደቡብ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሶማሌ ክልሎች በተደጋጋሚ ይፈፀማል፡፡ መቼ ይሆን እንዝህ ሰዎች ጡጦ የሚጥሉት?

    Reply
  2. Tesfa says

    November 4, 2018 01:18 pm at 1:18 pm

    የሻምበል ፍቅረስላሴ በቅርቡ ሰጡት በተባለው ውይይት ወያኔ ካልፈራረሰ ጤና የለም ሲሉ ይህኑ እይታ የሻቢያው መሪም ለሃገራቸው ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ደግመውታል፡፡ መቀሌ ላይ የተሰገሰጉት የወያኔ የቀድሞ ባለስልጣኖች በተለያየ መንገድ የሚሰጡት አስተያየቶች ማን አለብኝ፤ አንተ ማን ነህ የሚል ለመሆኑ ሜቴክን የመዘበረው ጀኔራል ክንፈ በቅርቡ የሰጠውን አሳፋሪ ቃለ መጠየቅ መመልከት በቂ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያን የወደፊት ፈተናዎችን በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን።
    1. የወያኔ መሰሪ እጆችና በእጃቸው ያለ ሃብትና የጦር መሳሪያ የሚያመነጨው ክፋት – አዎን ጥቂቶች በለውጡ የመደመር ህሳቤ ባቡር ላይ እንደተሳፈሩ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ሃይሎች አብረው ለመዝለቅ እቅድ ስለለላቸው ከውስጥ በመሆን ነገርን ማሰናከላቸውን ይቀጥላሉ። በኢትዮጵያ ሶማሊያ፤ በጋምቤላና ቤኒሻንግሉ ወዘተ የሚቀሰቀሱ ግጭቶ ሁሉ በወያኔ የተዘዋዋሪ ተላላኪዎችና እንደ ኦነግ ባሉ የዘር ፓለቲካ አራማጆች የሚፈጠሩ ችግሮች ናቸው።
    2. ሌላው ሃበሣ አመንጪ ድርጅት ኦነግ ነው – ኦነግ በራሱ የፓለቲካ ምህዳር የሰከረ ኦሮሚያ የምትባል ሃገር አለች እያለ የውጭና የውስጡን ዓለም ሲያማታ የኖረ የህዝባችንን ሰቆቃ ያራዘመ አጥፊ ድርጅት ነው። ህቡዕ በሆኑ የአውሮጳና የሰሜን አሜሪካ ሃገሮች እየኖሩ ዛሬም የኦነግን ባንዲራ በማውለብለብ እኔን እዪኝ የሚሉት እነዚህ ጠባቦች ቢዘፈን የማይዘፍኑ ቢለቀስ የማያለቅሱ በራሳቸው ታቡር ብቻ ዳንኪራ የሚወርድ ተምረናል ብለው የደነቆሩ ስብስቦች ናቸው። ዛሬ የወለጋን ህዝብ የሚያምሱት እነርሱ ናቸው፡፡ ሲመቻቸው ከቤተክርሲቲያኖች፤ ሳይመቻቸው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበርና ንዋይ በመለመን ሃገርን ለማፍረሰ ከሚጥሩ ልበ ቢስ ሃገር በቀል አራሙቻ የፓለቲካ ድርጅቶች መካከል ኦነግ ቀዳሚ ስፍራውን ይይዛል። ኦነግ ሚኒሊክ ጡት ቆረጠ በማለት የወያኔን የከፋፍለህ ግዛው ተንኮል በቁሙ የጠጣ ድርጅት ሲሆን በአንጻሩ የራሱ ደጋፊዎች ያለምንም ፍርድ በጠራራ ጸሃይ ሰው ዘቅዝቀው የሚሰቅሉበት፤ ያለምንም መረጃ ሴትና ወንድ ልጅን በደቦ የሚደበድቡበት አለቅጥ የተጣመመ ፓለቲካ አራማጆች ናቸው።
    3. የኢትዮጵያን መበልጸግና መጎልበት በጥርጣሪ አይናቸው የሚመለከቱት የአረብ ሃገራት በተለይም ሳውዲዎችና ግብጽዎች ሃገር በቀል የሆኑ የፓለቲካና የሃይማኖት ድርጅቶችን በማገዝ የሃገራችን ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋሉ። በማድረግም ላይ ናቸው።
    እነዚህ ሶስት ሃይሎች የዛሬና የወደፊት የሃገሪቱ ፈተናዎች ናቸው። አዎን ቀንና ሃላፊ ጎርፍ የሚያመጣው አይታወቅምና በውሉ ተምኖ ችግራችን ከእነዚህ ብቻ የሚመነጭ ነው ብሎ ማመን ራስን ማጃጃል ይሆናል። ያልታለሙ ነገሮች ብቅ ሊሉ ይችላሉና።
    በቅርቡ የትግራይ የዮንቨርሲቲ ተማሪዎች ትግራይ ላይ እንመደብ ሌላ ክልል መሄድ አንፈልግም በማለት ያሰሙትን ተቃውሞ ሳነብ ምን ያህል የሃገራችን ፓለቲካ ወልጋዳ እንደሆነ አስገንዝቦኛል። ማንም ዜጋ በፈለገበት ቦታ በዜግነቱ ኮርቶና ተምሮ ሰርቶ የማይኖርባት ሃገር ባፍንጫዬ ትውጣ።

    Reply
  3. degusa says

    November 5, 2018 04:54 pm at 4:54 pm

    በርግጠኝነት እንስሳ እንኳን ካንተ የተሻለ ያመዛዝናል፡፡ደንቆሮ፡፡ኦነግ ድርጅት ነው፣ድርጅት ደግሞ በሰዎች ይወከላል፡፡ሰዎች ደግሞ ሁሉም መጥፎ ሁሉም ጥሩዎች ባይሆኑም የሌላውን መብት እስካልነኩ ድረስ ማንም ሰው የመሰለውን ሃሳብ የመያዝ መብት አለው፡፡አህያ ነፍጠኛ ለራስህ እምዬ እትዮጵያ ብለህ የሌለህ ታሪክና ተረት ይዘህ ስታቦካ እንዴት ኦሮሚያ ሚባል ሀገር አለ ይላል ብለህ አፍህን ትከፍታለህ፡፡ሃዳራው፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule