ተጠናቀቀ በተባለው የጋምቤላ ክልል ግምገማ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ለመሾም የገንዘብ ኃይል ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑ ተሰማ። ግምገማውን እንዲመሩ የተመደቡት ግለሰቦች የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ምደባ በተመለከተ ከሌሎች ጋር በመሆን በገንዘብ ኃይል የሚፈልጉትን ለመሾም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ማለታቸውን ጠቅሶ በክልሉ የተንሰራፋውን ግፍና ሙስና (ሌብነት) በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ ካወጣ በኋላ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ለመሾም በታቀደው ድብቅ አጀንዳ ላይ ችግር መፈጠሩ ተሰምቷል። ለአሥር ቀናት የተካሄደውን ግምገማ የመሩትን በተመለከተ ጎልጉል ዘገባውን ሲያቀርብ “ግምገማውን እንዲመሩ ከፌዴራል መንግሥት የተወከሉት ፈቃዱ ተሰማ እና ተፈራ … [Read more...] about ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ
gatluak
“ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ዑመድ ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን “የቀድሞ ደጃዝማቾች ካባቸውን አውልቀው ለሚፈልጉት በመስጠት እንደሚሾሙት ጋትሉዋክም ለዘመዱ የስልጣኑን ካባ ያጎናጸፈበት ቀልድ ነው” ሲሉ አውግዘውታል፤ ይልቁኑም ጋትሉዋክ ቱት በበርካታ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ ስለሆነ ሌሎቹንም አመራሮች ጨምሮ ሁሉም “ለፍርድ መቅረብ … [Read more...] about “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች