ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ዑመድ ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን “የቀድሞ ደጃዝማቾች ካባቸውን አውልቀው ለሚፈልጉት በመስጠት እንደሚሾሙት ጋትሉዋክም ለዘመዱ የስልጣኑን ካባ ያጎናጸፈበት ቀልድ ነው” ሲሉ አውግዘውታል፤ ይልቁኑም ጋትሉዋክ ቱት በበርካታ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ ስለሆነ ሌሎቹንም አመራሮች ጨምሮ ሁሉም “ለፍርድ መቅረብ … [Read more...] about “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች