በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን፣ በቦረናና ጉጂ ዞኖች አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የምርጫውን ሒደት ለማስተጓጎል በተንቀሳቀሱ 26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ታወቀ፡፡ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 20ዎቹ ታጣቂዎች ከጅማ ዞን ናቸው፡፡ ጅማ ዞን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በጎማ 2 የምርጫ ክልል ዕጩ ሆነው የቀረቡበት አካባቢ ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን አመንቴ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩና በፓርላማ አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ ታጣቂ ቡድኖች በምርጫው ሒደት ላይ መስተጓጎል ለመፍጠር በመሞከራቸው ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በምርጫው ሒደት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለመከላከል፣ … [Read more...] about በኦሮሚያ ክልል በ26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ ተወሰደ
ethiopian terrorists
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ