"ሀገርን ለማዳን እዘምታለሁ የትም መቼም በምንም" በሚል መሪ ቃል ፀረ ሰላም ሀይሎችን ለመፋለም ቆርጠው የተነሱ የቁርጥ ቀን ልጆች በሀገሪቷ በሚገኙ የውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች በመግባት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከዚህ ቀደም በርካታ የሰራዊት አባላትን በሁለት ዙሮች አሰልጥኖ ያስመረቀ ሲሆን÷ በአሁኑ ጊዜም የ3ኛ ዙር ሰልጣኞችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡ አሰልጣኝ የ22ኛ ሻለቃ ዘመቻ ሀላፊ መቶ አለቃ ዲኔ መሀመድ የዚህ ዙር ሰልጣኞች ከሁለቱ ዙር ሰልጣኞች ለየት የሚያደርገው ሀገርን ለማፈራረስ የተነሱት የሀገር ሀዲዎች የህወሓት እና የሸኔ የሽብር ቡድኖችን ለመፋለምና ሀገርን ከመፈራረስ ታድጎ አንድነቷን ለማስቀጠል ለሀገሬ እዘምታለሁ በማለት ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ስልጠናው የተካተቱ መሆናቸው ነው … [Read more...] about የሁርሶ ሠልጣኞች በብቃት እየተዘጋጁ ነው
ethiopian terrorists
በጁባ የተበጣጠሰው የጁንታው የሽብር መረብ
ኢትዮጵያ ባለብዙ ጀግኖች ሃገር ናት ኢትዮጵያ ሃገራችን ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተግባር ከ1951 በኮርያ የጀመረው የሰላም አምባሳደርነት በሩዋንዳ በኮንጎ በቡርንዲ በላይቤርያ በዳርፉር በአብዬ በሱማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ሰላም ላጡ ህዝብ ሰላምን አስፍኖ ለተራበው አጉርሶ ለተጠማው አጠጥቶ ዛሬም በአለም አደባባይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ለሰላም ተመራጭ የሆነ ሃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ነው። ታድያ ዛሬም በቡዙ ሺዎች የሚቆጠር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአለም ሰላም ማስከበር ላይ ተሰማርቶ በጀግንነትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን በከፍታ ማማ ላይ ያለ ሠራዊትን ሊነቀንቁት አስበው በደቡብ ሱዳን ጁባ የሚገኝውን የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃን ላይ ደም ለማፋሰስ የሽብር ተግባር ለመፈፀምና የኢትዮጵያ ሃገራችንን ገፅታ ለማበላሸት … [Read more...] about በጁባ የተበጣጠሰው የጁንታው የሽብር መረብ
የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ብሎ በመጥራት ለበርካታ ዓመታት አገራችንን ሲያሸብር የኖረው እና በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት በአሸባሪነት የተዘመገበው፤ በቅርቡም በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተመዘገበውን ትህነግ “አሸባሪ” ብሎ ለመጥራት ሲጨንቃቸው የሚታዩ የአገር ውስጥና የውጪ (እንደ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ጀርመን ድምፅ) ሚዲያ ተቋማት መኖራቸው በግልጽ እየታየ የመጣ ክስተት ሆኗል። በቅርቡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀም የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንን አለማከበር ነው” ካለ በኋላ “እነዚህን ስያሜዎች በሚጠቀሙ ሚዲያዎች ላይ ባለስልጣኑ ፈቃድ እስከመሰረዝ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል። በአገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን ሕግ እና … [Read more...] about የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለምርጫ ያነሳሁትን ፎቶ ወስዶ የተጠቀመበትን መንገድ እንዲያስተካክል የተቻለውን ጥረት አድርጎ የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን በተመለከተ ተቋሙን ለመክሰስ እገደዳለሁ ሲል የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አማኑኤል ስለሺ አስታወቀ። ጋዜጠኛ አማኑኤል በጉዳዩ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረው፤ አምንስቲ ኢንትርናሽናልን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ነው። "በስልክና በኢ-ሜይል ለማግኝት ጥረት እያረግን ቢሆንም እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጡንም። አሁን 22 ሰዓታት አልፎታል። በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ይህንን የተቀናበረ ምስል ተቀባብለውታል። ለራሳቸው ዓላማ የሚያውሉት እንኳን ቢሆን መቀየር የተከለከለ ነው" ሲል ተናግሯል። አምነስቲ ለመረጃው የተጠቀመውን ፎቶ ግራፍ በተመለከተ በውይይት ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ … [Read more...] about የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
“ብቃት የለኝም፤ የሥነምግባር ችግር አለብኝ” ታምራት ላይኔ
https://youtu.be/fWtD-akMhSU?t=400 ታምራት ስለ ራሱ የሥነምግባር ጉድለት በአደባባይ የተናገረውን ቪዲዮውን በመጫን ይመልከቱ የወንበዴው ቡድን አምበል በሆነው መለስ ዜናዊ በያኔው “ፓርላማ” ፊት ሌብነቱ ተዘርዝሮ እና የሥነምግባር ብልሹነቱን አምኖ ከፓርላማው የተባረረው ታምራት ላይኔ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን እየተመኘ ነው። ከበረኻ ወዳጆቹ እነ ሰዬ አብርሃ ጋር በመሆን ነው በዚህ ሥራ የተጠመደው። ታምራት በመለስ ትዕዛዝ በፓርላማው ፊት ሌብነቱን፣ ሥነ ምግባሩ የጎደፈና መሪ መሆን የማይችል መሆኑን አምኖ መባረሩ ትክክል ነው በማለት ተቀብሎ የላሰውን ስኳር ሳያጣጥም ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ነበር የተወረወረው። ጥያቄያችን ያኔ በዚህ መልኩ ብቃት የለኝም፣ ሥነ ምግባሬ ለተቀመጥኩበት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር … [Read more...] about “ብቃት የለኝም፤ የሥነምግባር ችግር አለብኝ” ታምራት ላይኔ
በአዲስ አበባ 325 የትህነግ አሸባሪዎች ከነመሣሪያቸው ተይዘዋል
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በጥናት ላይ በመመስረት እና ከህዝብ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በከተማችን በስጋትነት በተለዩ የተለያዩ ንግድ ቤቶች እና ድርጅቶች ላይ ባደረገው ብርበራ እና ፍተሻ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን፣ ሰነዶችን እና የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ። መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ህግ የማስከበር ዘመቻው በድል ተጠናቆ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ጨምሮ መላው ትግራይን መቆጣጠሩ ይታወቃል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ሐምሌ 11 ቀን 2013 ዓ/ም በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት በዚህ ሀገርን የማዳን እና ትግራይን የመታደግ ዘመቻ አብዛኞቹ የጁንታው አመራሮች ሲማረኩ፣ የተወሰኑት ደግሞ ተደምስሰዋል። ወቅቱ … [Read more...] about በአዲስ አበባ 325 የትህነግ አሸባሪዎች ከነመሣሪያቸው ተይዘዋል
ከ 170 በላይ ሴት የጁንታው አባላት በራሱ የጁንታው ታጣቂዎች ተደፍረዋል
በማይካድራ ንጹሃንን ጨፍጭፎ የሸሸው የአሸባሪው የህወሓት ወንጀለኛ ታጣቂ ቡድን በሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሴቶችን መድፈሩን በመከላከያ ሰራዊት የተማረኩት የህክምና ባለሙያና ወታደራዊ አመራር የሆኑት ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ማጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። በሱዳን የስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙ ከ170 በላይ የሚሆኑት የጁንታው አባላት ሴቶች ላልተፈለገ እርግዝናና ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጣቸውንም ምረኮኛው ገልጸዋል። ወንጀል ፈፅመው ወደ ሱዳን የሸሹ የትህነግ ታጣቂዎች በስደተኞቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈፀሙና በዚህም ያልተፈለገ እርግዝናና የአባላዘር በሽታዎች መስፋፋታቸውን ሲታዘቡ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ተክለወይኒ ታረቀ ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ትውልዳቸውና ዕድገታቸው በሰሜን ምስራቅ ትግራይ ታህታይ አዲያቦ በባድመ አካባቢ ሲሆን ከሰራዊቱ … [Read more...] about ከ 170 በላይ ሴት የጁንታው አባላት በራሱ የጁንታው ታጣቂዎች ተደፍረዋል
አዲስ አበባ ሳያርፉ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል በአየር ዕርዳታ ማድረስ አይቻልም
ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት ዓርብ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳሰታወቀው፣ የተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ የሆነው ተቋም፣ የኢትዮጵያን ሕግ ያላከበረ ድርጊት በተደጋጋሚ እየፈጸመ ከመሆኑም በላይ፣ በትግራይ ክልል ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያዛባ መግለጫ እያወጣ መሆኑን በመግለጽ ለተቋሙ ማስጠንቀቂያ ጽፏል፡፡ “በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ድርጅት የትግራይ መከላከያ ኃይል በማለት በሚያወጣው መግለጫ በተደጋጋሚ ጊዜ እየጠቀሰ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ የሚያወጣው መረጃ የተዛባና ሕገወጥ የተባለውን ኃይል የሚያበረታታ ነው” በማለት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ … [Read more...] about አዲስ አበባ ሳያርፉ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል በአየር ዕርዳታ ማድረስ አይቻልም
ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሕወሓት ባለሥልጣናት ሕንፃዎችን ሊያስተዳድር መሆኑ ተነገረ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት ቡድን አባላት ሕንፃዎችን በገለልተኛ አካል እንዲተዳደር በወሰነው መሠረት፣ ሕንፃዎቹን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ተረክቦ ሊያስተዳድር መሆኑ ተሰማ፡፡ በሰኔ 2013 ዓ.ም. አጋማሽ የሕወሓት ቡድን አባላት ንብረት የነበሩ ከ30 በላይ የንግድና የመኖሪያ ሕንፃዎች፣ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟል በሚል በተከናወነ የወንጀል ምርመራና የሀብት ጥናት መሠረት በገለልተኛ አካላት እንዲተዳደሩ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ እነዚህን ንብረቶች የማስተዳደር ጉዳይ አስመልክቶ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ለሪፖርተር የተናገሩት፣ የኮሜርሻል ኖሚኒስ የቢዝነስ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ገብረ ሕይወት ጌታሁን ናቸው፡፡ ንብረቶቹ የሕወሓት አመራሮችና ደጋፊዎች በተለያዩ መሠረተ ልማቶችና ሲቪል ተቋማት ላይ ላደረሱት ውድመትና ጉዳት … [Read more...] about ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሕወሓት ባለሥልጣናት ሕንፃዎችን ሊያስተዳድር መሆኑ ተነገረ
“አማራው ጌታቸው ረዳ ትግራይን አይመራም” በረኸኞቹ ትህነጎች
በተከታታይ በቲውተር ገጹ መረጃ የሚያሰራጨው የአሸባሪው ትህነግ አባል ጌታቸው ረዳ ትግራይን እንደማይመራ ክርክር ተነስቷል። የራያ ልጅ የሆነውና ፍጹም የአማራ ደም ያለው ባንዳው ጌታቸው ቀደም ሲል በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ወቅት በረኸኞቹን ትህነጎች “ህግ የማያውቁ፣ ደደቦች፤ ምንም የማይገባቸው፤ መሃይም ደናቁርት” እያለ ክፍል ውስጥ ሲያንኳስስ እንደ ነበር የሚናገሩት ተማሪዎቹ የትህነግ አባል መሆኑ ይፋ ከሆነ ማግስት ጀምሮ ግን ለትህነግ አጎብዳጅና ተገዢ እየሆነ መምጣቱን እነዚሁ ተማሪዎችና በቅርብ የሚውቁት ይመሰክራሉ። “እዳ በዝቶበት መክፈል ሲያቅተው የትህነግ አባል ሆኖ ማገልገል ጀመረ፤ ለፕሮጀክት የተሰጠውን ገንዘብ ሙልጭ አድርጎ በላው፤ ወሰበበት፣ ጠጣበት፤ ትህነጎችም በስልት አበሰበሱት” ሲሉ ጌታቸውን በቅርብ የሚውቁት ይናገራሉ። በቀጣይም “ዕዳ ስረዛ ተደርጎለት … [Read more...] about “አማራው ጌታቸው ረዳ ትግራይን አይመራም” በረኸኞቹ ትህነጎች