ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት ዓርብ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳሰታወቀው፣ የተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ የሆነው ተቋም፣ የኢትዮጵያን ሕግ ያላከበረ ድርጊት በተደጋጋሚ እየፈጸመ ከመሆኑም በላይ፣ በትግራይ ክልል ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያዛባ መግለጫ እያወጣ መሆኑን በመግለጽ ለተቋሙ ማስጠንቀቂያ ጽፏል፡፡ “በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ድርጅት የትግራይ መከላከያ ኃይል በማለት በሚያወጣው መግለጫ በተደጋጋሚ ጊዜ እየጠቀሰ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ የሚያወጣው መረጃ የተዛባና ሕገወጥ የተባለውን ኃይል የሚያበረታታ ነው” በማለት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ … [Read more...] about አዲስ አበባ ሳያርፉ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል በአየር ዕርዳታ ማድረስ አይቻልም
ethiopian terrorists
ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሕወሓት ባለሥልጣናት ሕንፃዎችን ሊያስተዳድር መሆኑ ተነገረ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት ቡድን አባላት ሕንፃዎችን በገለልተኛ አካል እንዲተዳደር በወሰነው መሠረት፣ ሕንፃዎቹን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ተረክቦ ሊያስተዳድር መሆኑ ተሰማ፡፡ በሰኔ 2013 ዓ.ም. አጋማሽ የሕወሓት ቡድን አባላት ንብረት የነበሩ ከ30 በላይ የንግድና የመኖሪያ ሕንፃዎች፣ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟል በሚል በተከናወነ የወንጀል ምርመራና የሀብት ጥናት መሠረት በገለልተኛ አካላት እንዲተዳደሩ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ እነዚህን ንብረቶች የማስተዳደር ጉዳይ አስመልክቶ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ለሪፖርተር የተናገሩት፣ የኮሜርሻል ኖሚኒስ የቢዝነስ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ገብረ ሕይወት ጌታሁን ናቸው፡፡ ንብረቶቹ የሕወሓት አመራሮችና ደጋፊዎች በተለያዩ መሠረተ ልማቶችና ሲቪል ተቋማት ላይ ላደረሱት ውድመትና ጉዳት … [Read more...] about ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሕወሓት ባለሥልጣናት ሕንፃዎችን ሊያስተዳድር መሆኑ ተነገረ
“አማራው ጌታቸው ረዳ ትግራይን አይመራም” በረኸኞቹ ትህነጎች
በተከታታይ በቲውተር ገጹ መረጃ የሚያሰራጨው የአሸባሪው ትህነግ አባል ጌታቸው ረዳ ትግራይን እንደማይመራ ክርክር ተነስቷል። የራያ ልጅ የሆነውና ፍጹም የአማራ ደም ያለው ባንዳው ጌታቸው ቀደም ሲል በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ወቅት በረኸኞቹን ትህነጎች “ህግ የማያውቁ፣ ደደቦች፤ ምንም የማይገባቸው፤ መሃይም ደናቁርት” እያለ ክፍል ውስጥ ሲያንኳስስ እንደ ነበር የሚናገሩት ተማሪዎቹ የትህነግ አባል መሆኑ ይፋ ከሆነ ማግስት ጀምሮ ግን ለትህነግ አጎብዳጅና ተገዢ እየሆነ መምጣቱን እነዚሁ ተማሪዎችና በቅርብ የሚውቁት ይመሰክራሉ። “እዳ በዝቶበት መክፈል ሲያቅተው የትህነግ አባል ሆኖ ማገልገል ጀመረ፤ ለፕሮጀክት የተሰጠውን ገንዘብ ሙልጭ አድርጎ በላው፤ ወሰበበት፣ ጠጣበት፤ ትህነጎችም በስልት አበሰበሱት” ሲሉ ጌታቸውን በቅርብ የሚውቁት ይናገራሉ። በቀጣይም “ዕዳ ስረዛ ተደርጎለት … [Read more...] about “አማራው ጌታቸው ረዳ ትግራይን አይመራም” በረኸኞቹ ትህነጎች
“ለዶሮ በሽታ በሬ ማረድ ትክክል አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ
አንዳንዶች ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ በቆዩበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የመጨረሻ ዘመንና የመጨረሻው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ሰኔ 28 ቀን 2013. ዓ.ም. በነበራቸው ጥያቄና መልስ፣ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን 561 ቢሊዮን ብር የ2014 ዓመታዊ በጀት እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ የመጨረሻ የውሳኔ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ የአገሪቱ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮችና ሌሎችም አካላት በተገኙበት በዚሁ የፓርላማው ስድስተኛ ዓመት አራተኛ ልዩ ስብሰባ በወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያመዘኑ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከ15 የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበውላቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን … [Read more...] about “ለዶሮ በሽታ በሬ ማረድ ትክክል አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ
በኦሮሚያ ክልል በ26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ ተወሰደ
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን፣ በቦረናና ጉጂ ዞኖች አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የምርጫውን ሒደት ለማስተጓጎል በተንቀሳቀሱ 26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ታወቀ፡፡ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 20ዎቹ ታጣቂዎች ከጅማ ዞን ናቸው፡፡ ጅማ ዞን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በጎማ 2 የምርጫ ክልል ዕጩ ሆነው የቀረቡበት አካባቢ ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን አመንቴ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩና በፓርላማ አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ ታጣቂ ቡድኖች በምርጫው ሒደት ላይ መስተጓጎል ለመፍጠር በመሞከራቸው ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በምርጫው ሒደት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለመከላከል፣ … [Read more...] about በኦሮሚያ ክልል በ26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ ተወሰደ
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ