የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ከሠራዊቱ ጋር ለማክበር ማይጠብሪ ግንባር ተገኝተዋል። በማይጠብሪ ግንባር ከሠራዊቱ ጋር በዓልን ለማክበር የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌትናል ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የመከላከያ ኅብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ የምእራብ እዝ እና የማይጠብሪ ግንባር አዛዥ ሜጄር ጄኔራል መሠለ መሠረት ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል። የሠራዊት አባላት ተልዕኳቸን በላቀ ብቃት በመወጣት በአዲሱ ዓመት በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እናሰፍናለን ብለዋል። ሕዝባችን ያሳየንን ከፍተኛ ድጋፍ የሞራል ስንቅ አድርገን በአዲሱ ዓመት ለሕዝባችን ታላላቅ የድል ብሥራቶችን ለማሰማት እንዘጋጅ … [Read more...] about ባለፉት 100 ዓመታት ያልተገነባ ሠራዊት ለመገንባት እየሠራን ነው – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ethiopian terrorists
ከብርሸለቆ ውትድርና ማሰልጠኛ ተመርቀው ለግዳጅ የተዘጋጁት ባልና ሚስት
በትዳር ዓለም ለአንድ ዓመት ያህል የቆዩት ሮዛ አህመድ እና ኤሊያስ አባሜጫ የኢትዮጵያ ነገር አይሆንላቸውም። ጣፋጭ ጊዜያቸውን በቤታቸው ቁጭ ብለው ሲያሳልፉ የነበሩት ጥንዶቹ የእናት ሀገርን የሕልውና ጥሪ ሲሰሙ ልባቸው ለዘመቻ መነሳሳቱን ይናገራሉ። "እኛስ ለምን መከላከያ ሠራዊቱን ተቀላቅለን ሀገራችንን አናገለግልም?" የሚል ሃሳብ ያድርባቸዋል። ጥንዶቹ በጉዳዩ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመከሩ በኋላ ጅማ ዞን በሚገኝ አንድ ጣቢያ ሄደው ለውትድርና እንደተመዘገቡ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ተናግረዋል። የአጋጣሚ ነገር ሆነና ጥንዶቹ ለውትድርና ስልጠናው ወደብርሸለቆ ማሰልጠኛ አንድ ላይ ገቡ። አሁን ላይ ጥንዶቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው በመሰረታዊ ወታደርነት በመመረቃቸው ለዘመቻ ዝግጁ ሆነዋል። "ከዚህ በኋላ ዓላማችን ሁሉ የሀገር ጠላት የሆነውን ከሃዲ ቡድን … [Read more...] about ከብርሸለቆ ውትድርና ማሰልጠኛ ተመርቀው ለግዳጅ የተዘጋጁት ባልና ሚስት
ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ መቶዎችን ጨፍጭፏል
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት በነሃሴ 26ና 27 ሁለት ቀን ብቻ ከመቶ ሃያ በላይ ንጹሃንን መጭፍጨፉ ከአካባቢው መረጃ እየወጣ ይገኛል። ትህነግ ለምን ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ መረጃዎቹ እስካሁን ዝርዝር አላቀረቡም። ይሁን የቀብር ስፍራዎችን በፎቶ ማስረጃ ይፋ እየሆኑ ሲሆን፤ በጅምላ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማንነት እየተለየ መሆኑ ታውቋል። ትህነግ የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ በሁዋላ በርካታ የጅምላ ጭፍጨፋና የነብስ ወከፍ ግድያ መፈጸሙ ይፋ እየሆነ ነው። መረጃዎች መሰራጨት ከጀመሩ በሁዋላ ክልሉ የሚከተለውን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ገልጿል። እንዳለ አቅርበነዋል። የጀግኖቻችንን የተቀናጀ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና … [Read more...] about ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ መቶዎችን ጨፍጭፏል
በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የነበሩት ሳምሪዎች ለትህነግ ተዋግተዋል
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከትግራይ ክልል ወጥተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በጦርነት መሳተፋቸውን ባወጣው መግለጫ አመለከተ። ዩኤንኤችሲአር ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙና ድጋፍ የሚደረግላቸውን ስደተኞች የመረጃ ሁኔታን ከልሷል። በዚሁ መሰረት በመጠለያ ጣቢያው ተመዝግበው የነበሩ ስደተኞች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ መቀነሱንና በስደተኛነት ተመዝግበው የነበሩ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም የት ይሂዱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ይፋ አድርጓል። በግጭት ውስጥ የተሳተፈን ሰው በስደተኛነት የማይቀበለው ዩኤንኤችሲአር በስደተኛነት ተመዝግቦ በግጭት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውንም ሰው ዳግም እንደማይቀበል አድርጓል። ከኢትዮጵያ ግጭት ሸሽተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ … [Read more...] about በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የነበሩት ሳምሪዎች ለትህነግ ተዋግተዋል
የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን (Diaspora Cyber Team) ትላንት (Sep 5) ስብሰባ ነበራቸው።የእኛ ሰዎችም የሳይበር ውይይታቸውን ሰብረው በመግባት ታድመው ወጥተዋል። አጀንዳዎቹ:- 1- አለም አቀፍ ጫናዎችን በድጋሜ በአዲስ መልክ እንዴት እንፍጠር? 2- ትግራይ ውስጥ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው። ለዚህስ መፍትሄው ምንድነው? 3- ህወሓት/የትግራይ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የሚሉ ናቸው። የተስማሙባቸው ነጥቦች:- 1ኛ) ጦርነቱ ትግራይ መሬት ላይ በነበረበት ወቅት ተዘረፍን ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ በጅምላ ተገደልን ... ብለን የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና እንዲፈጥሩ አድርገናል። አሁን ያንን መንገድ መከተል አዋጭ ስላልሆነ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እየተጎዳና እየሞተ እንደሆነ ፣ ወደ ትግራይ እየገባ ያለው የእርዳታ እህልም እጅግ … [Read more...] about የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የስደተኛ መታወቂያ የያዙ የትህነግ ተዋጊዎች ተይዘዋል፤ ተመድ እያጣራ ነው ብሏል
“የስደተኞች መታወቂያን ይዘው ተገኝተዋል” የተባሉ ታጣቂዎችን ጉዳይ እያጣራ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲው “በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩና የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ተገኙ” የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩና በተለያዩ የሚድያ አውታሮች ሲዘገቡ መመልከቱን ስለ ጉዳዩ ለጠየቀው አል ዐይን አማርኛ በላከው የኢ-ሜይል መልዕክት አስታውቋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሰሞኑን በሱዳን አቅጣጫ መጥተው “ሽንፋ የተባለ ቦታን ለመያዝ የተንቀሳቀሱ የቅማንትና ህወሃት ታጣቂዎች መደምሰሳቸው”ን የሚያሳውቅ ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው ማጋራታቸው የሚታወስ ነው። ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ‘ህወሓት ሰብዓዊ እርዳታን እየዘረፈ ነው’ መባሉን “ከዓለም … [Read more...] about የስደተኛ መታወቂያ የያዙ የትህነግ ተዋጊዎች ተይዘዋል፤ ተመድ እያጣራ ነው ብሏል
መሃሪ ተከስተ ገብረኪዳን፤ ባለ 5 መታወቂያና 25 የባንክ ደብተሮች ባለቤት
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ አምስት የቀበሌ መታወቂያ እና 25 የተለያዩ የባንክ ደብተሮች ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ግለሰቡ በያዛቸው የባንክ ደብተሮች ውስጥ 2 ሚሊየን 966 ሺህ 189 ብር እንደተገኘበት ኮሚሽኑ አስታውቋል። አቶ መሃሪ ተከስተ ገብረኪዳን የተባለው ግለሰብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ናሆም አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ የፀጥታና ህግ-ማስከበር የቀጠና 1 ሻለቃ 2 ኃይል 1 አዛዥ ኢንስፔክተር አዲሱ ተሾመ ገልፀዋል። አሁን ያለውን ወቅታዊ የፀጥታ ችግር የአሸባሪው ህወሓት ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ለመፈፀም የተለያዩ ሰዎችን እየተጠቀመ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ አንጻርም የሽብር ቡድኑን ተግባር ለማስፈፀም … [Read more...] about መሃሪ ተከስተ ገብረኪዳን፤ ባለ 5 መታወቂያና 25 የባንክ ደብተሮች ባለቤት
ትህነግ ቤተ እምነቶችን እንደ ጦር ካምፕ እየተጠቀመባቸው ነው
የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያንን እና መስጅዶችን ከማውደም ባሻገር እንደ ጦር ካምፕ እየተጠቀመባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ። የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መድረክ በባህርዳር እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የህወሓት የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ላይ የጋረጠውን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ ኅብረተሰቡ በኅልውና ዘመቻው እንዲሳተፍ የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የህወሓት የሽብር ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት የሃይማኖት አባቶች የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆኑን የክልሉ መንግሥት በአድናቆት ይመለከተዋል ሲሉም ተናግረዋል። ነገር ግን ጥቂትም ቢሆኑ ሽማግሌ በመምሰል ለህወሓት … [Read more...] about ትህነግ ቤተ እምነቶችን እንደ ጦር ካምፕ እየተጠቀመባቸው ነው
“የትህነግ አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቋል” የዓይን እማኞች
አሸባሪው ህወሓት በደብረ ዘቢጥ ግምባር በተወሰደበት እርምጃ የተደመሰሱበትን የጦር አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን እየደበቀ መሸሹን በግምባሩ ላይ በውጊያ የተሳተፉ የዓይን እማኞች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል። በደብረ ዘቢጥ ግምባር ላይ ያሉት ሻምበል ጌታሁን ካሳዬ በስፍራው ለሚገኙት ዘጋቢዎቻችን በሰጡት መረጃ፤ በአውደ ውግያው አሸባሪው ቡድን የጦር አመራሮቹ ሲደመሰሱበት አንገታቸውን ቆርጠው በመደበቅ ማንነታቸውን ለመደበቅ እንደሚሞክሩ ተናግረዋል። እንደ ሻምበል ጌታሁን ገለጻ፤ የአሸባሪው ቡድን ከዚህ ቀደም በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት አዋጊዎቹ ሲሰው ማንነታቸው ይፋ እንዳይወጣ አንገታቸውን ይቆርጥና ይደብቅ ነበር። በህልውና ዘመቻ ወቅትም ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም በተለይም በደብረ ዘቢጥ ግምባር የተሰውበትን በርካታ የጦር አመራሮች … [Read more...] about “የትህነግ አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቋል” የዓይን እማኞች
ሽንፋን በአራት አቅጣጫ ከብቦ ጦርነት የከፈተው ትህነግ እርምጃ እየተወሰደበት ነው
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም አሸባሪው እና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በተካሄደው የሕግ ማስከበር እርምጃ የተረፈው የጠላት ጦር የሸሸው ምዕራብ ጎንደርን በሚያዋስነው የሱዳን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ነበር፡፡ ከሕግ ማስከበር እርምጃው በኋላ ላለፉት 10 ወራት በአካባቢው ጥቃት ለመሰንዘር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም በስፍራው ባለው የወገን ጦር እየተመታ ተመልሷል፡፡ ዛሬ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የጠላት ጦር ሽንፋን በአራት አቅጣጫ በኩል በመክበብ ጦርነት ከፍቶ ነበር ያሉት የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በሁሉም ግንባሮች በአካባቢው የጥምር ጦር አባላት ተገቢው እርምጃ ተወስዶበታል ብለዋል፡፡ በጦርነቱ የጠላትን ጦር በማገዝ እና በመምራት የአሸባሪው እና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን ሌላኛው ሴል … [Read more...] about ሽንፋን በአራት አቅጣጫ ከብቦ ጦርነት የከፈተው ትህነግ እርምጃ እየተወሰደበት ነው










