በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ? የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውም ጊዜ ለህገመንግስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል። ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዝቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል። ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ … [Read more...] about ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
Politics
አልሰሙም አልታረሙም
እነሆ ራሳቸው በጠሩዋቸው ጉባዔዎችና ኮንፍረንሶች ላይ ሁሉ በተደጋጋሚ ተነግረዋል አልሰሙም፤ ተመክረዋልም አልታረሙም። እኒህም የኢትዮጵያ ገዢዎች የኢህአዴጋውያን አዛዦች የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ህወሃታውያን ናቸው። ማስረጃ ቢባል ማርሻል መለስ ከመራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉባዔ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ የዘለቁት መሰል ጉባዔዎች ዋቢዎቻችን ናቸው(1)። እነሆም ህወሃታውያኑ በወጣትነት ዘመናቸው በሽፍትነትና ዘረኝነት እንደታበዩ ገድለው ዘርፈውና አጥፍተው በጎልማሳነታቸው ምኒልክ ቤተመንግሥትን በጠመንጃ ማረኩ። እነሆም በስተርጅና ዘመናቸው ባልገነቡት ቤተመንግሥት እየፏለሉ ከሽፍትነት የድውይ አስተሳሰባቸው፤ ከድኩም ባህሪያቸው፤ ከመሃይምነታቸው፤ ከመሰሪ ተፈጥሯቸው፤ ከናዚስት ዕምነታቸው ይታረሙና ይፀዱ ዘንድ ግን ከቶም አልተቻላቸውም። እነሆም በኢትዮጵያ መንበር ላይ ተኮፍሰው … [Read more...] about አልሰሙም አልታረሙም
ለጨለንቆ ሰማዕታት
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ነፍጥ አንጋቢዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት የጨለንቆ ወገኖች በነቀምቴና በአዳማ ተማሪዎች መታሰቢያ አድርገዋል። የቢቢሲ የኦሮሚኛ ዘገባ እንዳስረዳው ከአንድ ቤት አምስት ሞተዋል። (ፎቶዎቹ ከማህበራዊ ድረገጾች የተገኙ ናቸው) በነቀምቴ ወለጋ አዳማ ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ለጨለንቆ ሰማዕታት
ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር
መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ተፈረደባቸው ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም። ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት እንደማትሆን የሆላንድ ፍትህ ሚኒስትር አስታወቁ። አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም። በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየት ሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት … [Read more...] about ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር
“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”
እነዚህም የህወሓት ነፍሰበላዎች ይፈለጋሉ! የሰላም ሰዎች የሆኑት አኙዋኮች ከህወሓት ጋር መቃቃር ውስጥ የገቡት ገና ከጅምሩ ነበር። የቀድሞው የአኙዋክ ምክርቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኦባንግ ሜቶ እንደሚሉት ችግሩ የተያያዘው ህወሓት የጋምቤላን ለም ምድር የራሱ ለማድረግ ከመፈለጉ ጋር ነው። ህወሓት ሥልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ የጋምቤላን ብቸኛ ጄኔሬተር በመንቀል ከመውሰድ አልፎ በአሎሮ ግድብ ላይ የነበሩትን ወደ 400 የሚሆኑ ማሽነሪዎች እና የእርሻ መሣሪዎች በምሽት ወደ ትግራይ ነቅሎ ወስዷል ይላሉ አቶ ኦባንግ። በመቀጠልም ተዝቆ የማያልቀውን የጋምቤላን ድንቅ ሃብት በረኸኞቹ ህወሃቶች ለመዝረፍ ውሳኔያቸው አደረጉ። “መሬቴን አላስነካም” በሚለው አኙዋክና ህወሓት መካከል ያለውን መቃቃር አንድ “ዕልባት” ላይ ለማድረስ በሚል አኙዋክን ማጥፋት የህወሓት ቀዳሚ ሃሳብ ሆነ እንደ አቶ … [Read more...] about “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”
የተማሪዎች ዓመጽና የየአካባቢው አጫጭር መረጃዎች
አክሱም ዩኒቨርሲቲ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በየግማሽ ቀኑ ሲነሳና ሲበርድ ነው የሰነበተው። በካፌ ሰዓት ብዙ ጊዜ ድንጋይ ይወረወራል። ማምሻውን በራት ሰዓት በተፈጠረው ብጥብጥ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ቢሔዱም እስካሁን መውጣት የሚፈልጉ ከሁለት ሺህ በላይ የዐማራ ተማሪዎች አሉ። አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጠዋት በነበረው ብጥብጥ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር። በአዲግራት እስካሁን የተረጋገጠ 9 ያክል ተማሪዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ በርካቶች ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ወደ 30 የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች በአዲግራት የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው ቶርች ተደርገዋል፤ እስካሁንም አልተፈቱም። ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሔድ ቢፈልጉም አልተቻለም። ገዳም … [Read more...] about የተማሪዎች ዓመጽና የየአካባቢው አጫጭር መረጃዎች
እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው
ንጉሥ ሳልማን በቅርቡ ከሥልጣናቸው ወርደው በአልጋ ወራሹ ይተካሉ እስራኤል ከሳዑዲ ጋር የመረጃ (የስለላ) ልውውጥ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለች በሙስና እና የመንግሥትን ሃብት አለአግባብ በመጠቀም በሚል በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የሳውዲ ልዑላንና ሌሎች ታላላቅ ባለሥልጣናት ከእስር ለመውጣት እስከ 70 በመቶ ሃብታቸውን ለመንግሥት ለማስረከብ እየተደራደሩ መሆናቸው ተሰማ። አል-አሙዲ በ30 በመቶ መቀጠል አሳሳቢ ሆኗል። ንጉሥ ሳልማን ሥልጣናቸውን ለአልጋ ወራሻቸው ሊያስረክቡ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሳዑዲ ጋር ለየት ያለ ግንኙነት የጀመረችው እስራኤል ከሳዑዲ ጋር በሚፈለገው መልኩ ለመተባበር ፈቃደኝነቷን አስታወቀች። በኢትዮጵያ ላለፉት 26ዓመታት ከግብር ነጻ ንግድ በማካሄድ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የነበረው የህወሓት የቅርብ ወዳጅ አል-አሙዲ በሳዑዲ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ጊዜ ጀምሮ … [Read more...] about እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው
“9ኙ የእግር ጣት ጥፍሮቼ በጉጠት ተነቅለው” ንቃዩን ይዤ እንዳልቀርብ ተጥለውብኛል – ንግሥት ይርጋ
ንግስት ይርጋ አቃቤ ህግ ባቀረበባት የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረበችው መቃወሚያ ላይ የተወሰደ (በጌታቸው ሺፈራው) በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ አባተ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበበት የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረበው መቃወሚያ ላይ የተወሰደ↓(በጌታቸው ሺፈራው) በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ 2ኛ ተከሳሽ እና የጎንደር ዙሪያ የመኢአድ ሰብሳቢ የነበሩት ዓለምነህ ዋሴ ካቀረቡት የሰነድ መቃወሚያ ላይ የተወሰደ ↓↓(በጌታቸው ሺፈራው) የወልቃይት ሕዝብ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆኑት መብራቱ ጌታሁን፣ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዛፌ፣ አለነ ሻማ እና ነጋ ባንተይሁን ለተመሰረተባቸው ክስ ካቀረቡት የክስ መቃወሚያ የተወሰደ ↓↓(በጌታቸው ሺፈራው) (ምንጭ: Addis Gazetta) … [Read more...] about “9ኙ የእግር ጣት ጥፍሮቼ በጉጠት ተነቅለው” ንቃዩን ይዤ እንዳልቀርብ ተጥለውብኛል – ንግሥት ይርጋ
“አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ
መቀሌ ወሩን ሙሉ ውጥረት ውስጥ ከርማለች። ከተማዋ ላይ እየወረደ ያለው ዶፍ የሚያባራ አይመስልም። የህወሃቶቹ የዘንድሮ መሰባሰብ ለጤና እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎቹ እንደወትሮው “በሃገር ጉዳይ ላይ” ለመዶለት ወደ መቀሌ አልተጓዙም። ቀደም ሲል ጠላታችን ድህነት ነው ሲሉን ነበር። አሁን ግን ለሁለት ተቧድነው አንዱ ሌላውን ጠላት ሲል ይሰማል። በግል ጸብ ለሁለት መሰንጠቃቸው የአደባባይ ምስጢር ይሁን እንጂ፤ እርቅ እና ሰላም በአጀንዳቸው ውስጥ አልተካተተም። ሃገሪቱ የገባችበትን ችግር ወደጎን ትተው፣ “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” ሲባባሉ እንደከረሙ ነው እየተሰማ ያለው። ይህንን የማይታረቅ ቅራኔ ይዘው አብረው ስለማይዘልቁ የአንዱ ቡድን ማሸነፍ ግድ ይላል። በዚህ ‘ታሪካዊ’ ስብሰባ የሙስና እና የሌብነት ፋይሎች ተጠርዘው ቀርበዋል። ህወሃቶች አፍ አውጥተው “በስብሰናል”ም ብለዋል። … [Read more...] about “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ
ህወሓት የኦህዴድን የበላይነት በመቀበል ኦሮሞ ጠ/ሚኒስትር ሊሾም ነው
ጉዳዩ በህወሓት ዘንድ መጠነኛ መከፋፈል ፈጥሯል “ኃይለማርያም ደሳለኝ የመስዋዕት በግ?” ሲሉ የመረጃው ሰዎች አዲሱን ዜና ይጀምራሉ። የጎልጉል ታማኝ መረጃ አቅራቢዎች በኦሮሚያ ከአሁን በኋላ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ኃይል - ህወሓት ዕድል ፈንታ እንደሌለው ማመኑን ይጠቁማሉ። የኦሮሞ ጥያቄ የወንበር መሆኑን ህወሃት እንዳመነና ይህንኑ እምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መነሳቱን ለ“ወዳጆቹ”፣ ጌቶቹና አሳዳሪዎቹ ማሳወቁንም ይጠቁማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ይኸው ሁኔታ በህወሓት ውስጥ መጠነኛ መከፋፈልን እንደፈጠረ ይነገራል። እንደዜናው ሰዎች ከሆነ ህወሓት “የወለደውን፣ ያሳደገውንና፣ የሾመውን” ካድሬ ኢትዮጵያን እንዲመራ አጭቶታል። መረጃው ጎልጉል ካነጋገራቸው የተለያዩ ወገኖች በአሉታዊና በአዎንታዊ መልኩ አስተያየት ቢሰጥበትም ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆንና የኦሮሞ … [Read more...] about ህወሓት የኦህዴድን የበላይነት በመቀበል ኦሮሞ ጠ/ሚኒስትር ሊሾም ነው










