• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!

February 15, 2018 09:27 am by Editor 14 Comments

በኢትዮጵያ በተከታታይ የዘለቀውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር የተሳነው ህወሓት በኢትዮጵያ በአስቸኳይ አዋጅ ስም አገሪቷን በወታደራዊ አስተዳደር ስር ለማስተዳደር ኣዋጅ አንደሚያወጣ ተሰማ። የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው አዋጅ ምናልባትም ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

  • ያለፈው የኢህአዴግ ስብሰባ ወቅት ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ምስረታ ህወሓት ኣልቀበለውም ብሏል፥
  • ይህንን ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣኑ እንዲወርድ በህወሓት ግፊት ሲደረግበት ቆይቷል፤
  • የሃይለማርያም በፈቃዱ ከስልጣን መውረድ ለህወሓት የደኢህዴንን ስጋት እንዲቀንስለት ታስቦ የተደረገ ግፊት ነው፥
  • የኦህዴድ መክዳትና የብአዴን መከተል ላይ ደኢህዴን ከተጨመረ የህወሓትን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉ ስላሰጋው ነው ህወሓት ሃይለማርያም በፈቃዱ ለቀቀ ማስባል የፈለገው፥
  • ወታደራዊ አገዛዝ ከታወጀ በኋላ ህወሓት ያለ ርህራሄ ማንኛውንም ተቃውሞ “የመጨረሻ ውሳኔ” በማስተላለፍ ታይቶ የማይታወቅ ደም ማፋሰስ በአገሪታ ላይ በማስከተል ስልጣኑን ለማረጋጋት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፤
  • ይህንን ተፈጻሚ ለማድረግና ከጌቶቹ ፈቃድ ለማግኘት በኦሮሞ ስም ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ/ወልደጻድቅ አሜሪካ ይገኛል፥
  • ጎልጉል የደረሰው መረጃ አንደሚያመለክተው በአሜሪካኖቹ በኩል ሙሉ ስምምነት ባይኖርም  አንዳንዶቹ ግን “የአሜሪካንን ጥቅም የሚያስጠብቁት ትግሬዎች ናቸው” በማለት ለህወሓት ሙሉ ስልጣን እንዲሰጠው በግልጽ ይናገራሉ፤
  • ከዚህ ጋር በተያያዘ ወታደራዊው አገዛዝ ዛሬ ሲታወጅ የአሜሪካ ድጋፍ ወደ ህወሓት ማዘመሙን በግልጽ የሚያሳይ ይሆናል፥
  • በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲን አስተዳደር አውርዶ የአሜሪካ ወኪል በሆነው አልሲሲ ለመተካት በተደረገው ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚ ዜጎችን የአልሲሲ ኃይል ሲጨፈጭፍ ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ የውስጥ ድጋፏን እንደሰጠችው በኢትዮጵያም በቀጣይ የሚከሰተው ይህ እንደሚሆን ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል
  • የኃይል አገዛዝ የትኛውንም መንግሥት እንዳላጸናው ከታሪክ የማይማረው ህወሓት አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የበቀል ርምጃውንም ለመውሰድ ሰይፉን ስሏል፥ የጌቶቹን ቡራኬም እየተቀበለ ነው።

(ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናትማለን)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: eprdf, Full Width Top, Middle Column, military rule, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    February 15, 2018 09:09 pm at 9:09 pm

    ሰዎች!! ልማታችንን የሚቃወሙትን በሙሉ ፤ እገሌ ከገሌ ሳይል ሰራዊቱ እየመነጠረ ማውጣቱን ይቀጥል ይመስለኛል፤ እንጂ የጎልጉል ዘጋቢዎች እንደሚኝኩት ጫት ኣይደለም!!! እመኑኝ!! ኣይታወጅም!!! ተሰብስበው ጫት እያኘኩ ፤ ወሬ የሚፈጥሩት ብዙ ናቸው!!

    Reply
    • Editor says

      February 16, 2018 10:53 pm at 10:53 pm

      Mulugeta Andargie,

      ይህንን ብለህ ነበር፤ “… የጎልጉል ዘጋቢዎች እንደሚያኝኩት ጫት ኣይደለም!!! እመኑኝ!! ኣይታወጅም!!! ተሰብስበው ጫት እያኘኩ፤ ወሬ የሚፈጥሩት ብዙ ናቸው!!”

      ምንድነው ምላሽህ? አለኝ የምትለው “የበረሃ ወኔ” አሁን ካለህ እስቲ “ይቅርታ” በል? ለነገሩ ከበረሃ ወንበዴ ምንም አይጠበቅም? ውርደት የማታውቁ ሃፍተረ ቢሶች ናችሁ!

      አርታኢ

      Reply
  2. Ezira says

    February 15, 2018 11:20 pm at 11:20 pm

    Bad News ! but the Struggle is Continue

    Reply
  3. Tesfa says

    February 16, 2018 04:21 am at 4:21 am

    አሁን በሃገራችን የሚታየው ሁኔታ አነቃቂም አሳሳቢም ነው። ንቃቱ በየስርቻው ተጥለው የነበሩ እስሮኞች መፈታት መጀመራቸው ነው። ገና በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው ስላሉ ሁሉም እንዲፈቱ መታገል ያሻል። የሃገሪቱ ሁኔታ አጣብቂኝ የገባው ደግሞ ጠ/ሚሩ ከሥልጣን ለመውረድ መጠያቃቸው አይደለም። ድሮውንም ለምልክት የተቀመጡ ምንም ሥልጣን የሌላቸው ስለነበሩ ፋይዳ የለውም። ሃገሪቱ ታላቅ ችግር ውስጥ ናት።
    1. በየምክንያቱ ንብረትና ሃብትን የሚያቃጥሉና አድማ ነክ የሥራ ማቋም የሚያስከትለው የኢኮኖሚ ጫና የወያኔ መልስ
    2. ግብጽ፤ ኤርትራና ሱዳን ያለውን ግርግር በመጠቀም ሊያደርሱ የሚችሉት ወታደራዊ ጥቃት
    3. ሃገሪቱ በዘር የተከፋፈለች በመሆኗ ቀን ሲጨልም ሁሉም ለብቀላ ተነስቶ ስለሚፈሰው የሰው ደምና የርስ በርስ መገዳደል
    4. በእርግጥም ወታደራዊ አመራር ሃገሪቷን ከመራት የበለጠ አስከፊ ሁኔታ ይፈጠራል። ወታደራዊው መዋቅር 99.9% በወያኔ ሃርነት ትግራይ የተያዘ በመሆኑ ህዝብ ወታደሩንም ወያኔንም አይቀበልም። ጎልጉል በትክክል እንደዘገበው አሁን ከሃገሪቱ የሚመነጩ የውስጥ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት በቅርቡ ለወታደራዊ ማእረግ መሰጠቱ ጦሩን የኢትዮጵያዊነት መልክ እንዳለው ለማስመሰል የተፈጸመ ሽንክ ሥራ ነው።
    5. በሃገሪቱ የተለያዪ ክፍሎች እንደልባቸው ሲፈነጥዙና ሲዘርፉ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች አሁን በሚደርስባቸው ተቃውሞ ከሥራቸውና ከንግድ ሥፍራቸው ሲባረሩ የሚያስከትለው ምሬትና የብቀላ ዝግጅትና አንዳንድ ግለሰቦችና አፍቃሪ ወያኔ ድህረ ገጾች ከሰሞኑ የትግራይ ህዝብ ራሱን የመከላከል መብት አለው፤ ካስፈለገም እንገነጣላለን በማለት የሚያስፈራሩት ደጋፊ ሃሳብ ፍለጋ ነው።
    6. ሁሉም የሃገራችን ህዝብ ዘር ጎሳ ቋንቋ ሳይለየው በፈለገው ሄዶ ሰርቶ የመኖር እድሉ በወያኔ የክልል ፓለቲካ ስለተመረዘ ወያኔ ያለው ምርጫ ህዝብ ለመረጠው ስልጣንን አስረክቦ ከጫወታ ቢወጣ ለታሪክም ሆነ በየበረሃው ደማቸውን ላፈሰሱ የትግራይ ልጆች ክብር ነው። በመነጣጠል እንጠፋለን እንጂ መልካም ነገር አይገኝም። የትግራይ ሰው ሲጎዳ ሌላው የሃገራችን ክፍል ህዝቦች እንደራስ የማይቆጥሩት ከሆነ በሽታ ነው። የወያኔ አሽቃባጮችና የጊዜው የፓለቲካ ተጠቃሚዎችና የትግራይ ህዝብም የሌላው ወገኑ መሞትና መሰቃየት ስቃዮ እንደሆነ አምኖ ለፍትህ መታገል አለበት። ያ ካልሆነ አንተና አንቺ ስንባባል ጀንበር መጥለቋ ነው። አማራነት፤ ትግራዊነት፤ኦሮሞነት ወይም ሌላው ወገናቸን በተናጠል ለማንም አይጠቅምም። መኖር በህብረት ነው። ወያኔ ልብ ይስጠው!!

    Reply
  4. Eunetu Yeneger says

    February 16, 2018 11:43 am at 11:43 am

    ይድረስ ለአደዋ ቤተሰባዊ መንግሥት!

    በእውነት ቤተ ሰባችሁን ትወዳላችሁ???????

    እባካችሁ ወደ አእምሯችሁ ተመለሱና ከሕዝባዊ የቁጣ ማእበል እራሳችሁንና ልጆቻችሁን እንዲተርፍ አድርጉ?

    መላው የትግራይ ሕዝብም በዚህ አሳሳቢ ወቅት ልትጫወተው የሚገባ ሚና ስላለህ ከጠባብ አመለካከት ተላቀህ የአባቶችህን ኢትዮጵያዊነትህን አስበህ ተነስ?

    የመንግሥት ቀኝ እጅ የሆንከው የኢት/ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሲኖዶስም መንኮሰ = ሞተ የሚለውን ትርጉም ዘንግታችሁ እንደ ቅጠል ለሚረግፈው ወጣት ስትሉ በካባችሁ ውስጥ የያዛችሁትን ሽጉጥ ጥላችሁ መጻፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም የማዳን ፍቅር ምልክት የሆነውን መስቀሉን ያዙት እባካችሁ?

    ወንጌል ገብቶኛል በማለት መጽሐፍ ቅዱስ በእጅህ ይዘህ ያለህ ደግሞ ሰው/ሃገር ሲሞት እያየህ ዝም/ጭጭ በል የሚል ከሆነ መጽሐፉ ንገሩንና ልዩ ወንጌል መሆኑን እንወቅ = ለሰው ከሞት መትረፍ ሲል ክብሩን ትቶ ከላይ ለመጣውን አዳኝ ምስክር ነን እያላችሁ ምነው አገሪቱ/ምድሪቱ እንዲህ አኬልዳማ ስተሆን ምነው በፍርሃት ቆፈን ተቀፈደዳችሁ?በእውነት በፍቅር ውስጥ ፍርሃት አለን???

    ኦሮሞ፣ አማራ፣ እውነተኛ ትግሬ፣ ከምባታ፣ ሃድያ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ አገው ወዘተ ያለባችሁን ሃገራዊ ሃላፊነት በሰከነ የአንድነት መንፈስ ዛሬ ተነስታችሁ ይችን ሃገር ከደም መፋሰስ በጋራ ካልታደጋችኋት የአባቶቻችሁ ደም ይጮህባችኋልና በፍቅር ለፍቅርና ለአንድነት በጋራ ተነሱ???

    ውጭም ሆነ ወይም አገር ቤት የምትኖር ሁሉ በተቻለህ መጠን በዚህ ወሳኝ ወቅት ድርሻህን ለእውነት በእውነትና በፍቅር ከጥላቻ በጸዳ መንፈስ ተነስተህ እሪ ያገር ያለህ በማለት ወድ ላይም ወደ ግራም ወደ ቀኝም ጩህ!ተመካከር!ተንቀሳቀስ!ለአሉባልታ ጆሮህን ድፈን!ከምናገባኝና ከቁም ሬሳነት ተፈወስ??

    ለፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ ከኢሕዴግ መሰሪ የማታለያ ዘዴ በመጠንቀቅ ወደ እውነተኛ እርቅና ሰላም የሚያመጣ ገለልተኛና በሃገር ፍቅር የተላበሰ የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ይህን የመጣውን የጥፋት ደመና ለመግፈፍ ሰፊና ታጋሽ ልብ ይዛችሁ ተነሱ???

    ለጠቅላላ የአገሪቱ ሠራዊት አባላት በሙሉ ኢትዮጵያዊነትህ ከትግሬነትህ፣ ከኦሮሞነትህ፣ ከአማራነትህ፣ ከጉራጌነትህ፣ ከከምባታነትህ፣ በአጠቃላይ ከዘርነትህ ካልበለጠብህ ስትቀጠር ላገሬ ደህንነት እቆማለሁ ያልከውን ቃልህን መካድ ነውና ለሚጠፋ እለታዊ እንጀራ ብለህ የወንድምህን ግንባር በያዝከው መሳሪያ የአባይ ሸለቆ አታስመስለው??? ከሰው ተፈጥረህ ሳለ እንደ ዱር እንስሳት በወገንህ ላይ አውሬ ለምን መሆን አስፈለገህ?አንተም የሠራሃውን ታጭዳለህና

    በውጭ ጠላት ያለተደፈረች ሃገር አስተምራ ባሳደገቻቸው ልጆቿ የተደፈረችና የተዋረደች ሃገር = ኢትዮጵያ ብቻ ነች!
    ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን??

    የሰላም ጌታ ሰላምን ይስጠን!
    አሜን።

    እውነቱ ይነገር
    ካለሁበት

    Reply
  5. Mulugeta Andargie says

    February 16, 2018 02:53 pm at 2:53 pm

    ሰዎች!! ከላይ የተነተነው ጭፍን ኣስተያየት፤ የኣንዳንድ መሃይም ፤ እውጭ ኮብልለው፣ ሕዝባችንን እርስ በርስ ለማናከስ የሚጥሩ፤ ጊዜው ያለፈባቸው፤ ኋላ ቀርነቱን የተዛመዱ፤ ቢጤ ቢፈልጉ ያጡ፤ ልማቱን የጠሉ፣ ከጥቃቅን ብሄረስብ የተከማቹ፣ ባጋጣሚ ኣምታተው የቋጠሩ፣ ህዝባችንን የከዱ፣ ምላሳቸው መርዝ እንጂ በጎ የማያፈልቁ፣ ክፋት እንጂ ጤናን የማያስተናግዱ፣ ሌላም ሌላም ኧረ ብዙ በጣም ብዙ እዚህ ሰሜን ኣሜሪካ ውስጥ ተኝተው በህዝባችን ላይ ልክ እንደ ባዕድ ይሳለቁብናል፤ ህዝባችን ግን ከያዛት ልማት፣ንቅንቅ ኣይልም። ከድህነት የምንላቀቅበት ብቸኛ መንገድ ነውና።

    Reply
    • አለም says

      February 16, 2018 06:32 pm at 6:32 pm

      “ከጥቃቅን ብሄረስብ የተከማቹ” ያልከው ህወሓትንና ማንን ነው?
      “ብቸኛ መንገድ”? = የደርጉ ስርዓት ናፍቆህ መሆን አለበት!

      Reply
    • aradw says

      February 16, 2018 09:11 pm at 9:11 pm

      Wow Mulugeta. I am admiring that you show your illogical, irresponsible and untimely thought. I never imagined some one with this senselessness can exist on this earth. But it happened. It is amazing to see ከጥቃቅን ብሄረስብ የተከማቹ, how ignorant is to say this, does it matter whether one comes from big or small nationalities as far as one is skilled and thoughtful. Secondly, የተከማቹ , you forgot that Ethiopia is a mosaic of nations and nationalities, what can we be except ከማቹ. Do you mean it is only TPLF from one nation is capable. You are wrong. Look where we are with their leadership. I exactly know who do you mean with “ክፋት እንጂ ጤናን የማያስተናግዱ” This is perfectly TPLF. ምላሳቸው መርዝ እንጂ በጎ የማያፈልቁ well done another characteristics of TPLF. Even the TPLF and its cronies acknowledged all their crimes recently and asking the Ethiopian people for forgiveness and here you are preaching futility and silliness. I am afraid that you read, may be you can read but do you understand what the writing says. I can only say let the Almighty forgive you for your silliness.

      Reply
    • Bek says

      February 17, 2018 12:17 pm at 12:17 pm

      Your lord woyaneas are insulting the Ethiopian people for the past 27 years day and night without interval by saying “timikitegna ,nefitegna & tebabb” we heard and learnt this insults on the past 27 years. They are not capable and good teaching leaders to teach us and lead the blessed land. Its over. When I come to you, you are be filled up your mind or selled yourself for the under sky previladges. You know what is in the ground. Can you count me the prisoners from tigrea tribe ??????? your answer is NO. God gives you brain to think. Think what is going on in Ethiopia.

      Reply
    • ለጥይበሉ says

      February 21, 2018 11:57 pm at 11:57 pm

      አቶ Mulugeta Andargie፣

      ይሄ ካፈርኩ አይመልሰኝ መሆኑ ነው? አይሆንም ብለህ ያልከው ነገር ሲሆን ምነው ይቅርታ መጠየቁ ተናነቀህ? እኔ አንተን ብሆን ደግሜ አልጽፍም ነበር። ደግሞ “ከድህነት የምንላቀቅበት ብቸኛ መንገድ” ስትል ባለፉት 27 ዓመታት ከድህነት እየተላቀቁ ያሉትንማ እያየን ነው። ህዝቡማ ከመጥፎው ወደ ባሰው እያሽቆለቆለ እንደሆነ አውቀህ ካልጨፈንክ በቀር በገሃድ የሚታይ ነገር ነው። መጥኔ ላንተና ለመሰሎችህ።

      Reply
  6. Bek says

    February 17, 2018 12:08 pm at 12:08 pm

    Dear the so called Mulugeta Andargie, I am ashamed on your toughts. Are you leaving on the 21st century ??? Your brain is full of hate and mud. TPLF is rulling the country for the past 27 years by insulting the people of Ethiopia. Its time to them to step down. They are not capable to lead the country. The golgule news paper editor right us down the wright thing. Themilitarys of WOYANEAS are taking power. Its not dream its true. We read this story in before the decision is made in 4 kilo.
    Let thy Almighty Lord protect our beloved Ethiopia from this evils WEYANEA.
    Golgul editors, keep up your wenderful work. God bless you all for your good efforts.

    Reply
  7. Mulugeta Andargie says

    February 17, 2018 10:15 pm at 10:15 pm

    ምንም!!! ምንም!!! ከልማታችን ንቅንቅ ኣንላትም!!!! ይህን የሚያስከብር የታጠቀ ኃይል ኣለን!!!! ደርግን ይደግፍ የነበረው ኢህኣፓና መሰሎቹ እዚህ ሰሜን ኣሜሪካ ኮታቸውን ቀይረው ብቅ ብለዋል!!! ልማታችንን የሚያደናቅፍ የህዝብ ጠላት ነው። ፌዴራሊዝማችን የተዋቀረው በብሄሮች ስብስብ ነው። ከዚያ ውጪ የሚያልም ካለ የህዝባችን ጠላት ነው። ጥቃቅን ብሄረሰቦች ግን ተንኮል ከመስራት ኣቆጠቡም። በቀላሉ ይደለላሉና ነው።

    Reply
  8. ታዛቢ says

    February 17, 2018 10:41 pm at 10:41 pm

    ሰላማዊ ትግል ኀይል ይሚኖረው የዐላማ አንድነት ሲኖረው ነው። አለዚያ ወታደራዊ አገዛዝ አይቀርልንም።

    Reply
  9. Eunetu Yeneger says

    February 19, 2018 08:40 pm at 8:40 pm

    ወገኖቼ!

    በእውነት በምድራችን በወገናችን መካከል እየሆነ ያለው ትርምስና ነፍስ መዋደቅ ብቻ በራሱ አይሰማችሁም? ሕሊና የተባለው ሚዛንስ የተ ገባ? ሰው እንደ ቅጠል እየረገፈ እያለ!ያንን መቃዎምና ይህኛውን ደግሞ መደገፍ ጊዜው ነውን? በምንም መልኩ ይሁን የሟቹን ገዳይ በልማት እያሳባቡ መደገፍ ለእኔ ሚዛን የጎደለው የእብዶች እይታ ነው የሚሆነው? ልማት ለሰው ሁሉ /ለሃገር/ ወይስ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ? ምንድነው እያላችሁን ያለው ጉዳይ? እየሆነና በገሃድ እየታዬ ያለው የጠቀላላ ወገናችን የኑሮ ምጥ ፈጽሞ አልታይ አላችሁ? ወይስ በቃሉ እያዩ የማያዩ እንደተባሉት ሰዎች ታውራችኋል? በርግጥ ግንባር ላይ ያሉ የሥጋ ዓይኖች በስብና በጮማ ከወፈሩ እንደማያዩ እርግጠኛ ነኝ!!! የማዝነው በደርግ ዘመን የመከራው ገፈት ቀማሽ ሆነው የነበሩ ሰዎች ዛሬ መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ /የእነ አሉላን ዘር ጭምር/ ገፈት ሳይሆን በባሰ መልኩ አተላ እያስጠጡት መሆኑ ነው??? ይገርማል ያንዳንድ ሰዎች አስተሳሰብና ጭካኔ!!! አሁንም ጨካኞች ወገኖቼን ሳይመሽ ወደ ማስተዋል እንዲመለሱ ከሰማይ በሆነው እውነተኛ ፍቅር አሳስባለሁ!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule