• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር?!

September 14, 2012 09:08 am by Editor Leave a Comment

ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት ህወሓት የፖለቲካ የበላይነቱ ለመመናመኑ ምልክት መሆኑ ተጠቆመ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የህግ ለውጥ ሳይደረግ በደህንነት ሹሞች የቅርብ ቁጥጥር ስር መዋሉም ተሰማ። የጎልጉል ምንጮች ያነጋገሩዋቸው ክፍሎች መለስ በህይወት እያሉ ሁሉንም ቁልፍ ይዘውት ስለነበር ህወሃት የፖለቲካ የበላይነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ስለነበር የጦር ኃይሉ በፖለቲካው ዘርፍ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሲሆን አይታይም ነበር።

ኢትዮጵያን ወደ ፍጹም ወታደራዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ደፋ ቀና ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ህልፈት ሲያስተባብል የቆየው ኢህአዴግ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ለሰላሳ አራት ከፍተኛ መኮንኖች የብርጋዲዬር ጄኔራልነት፣ ለሶስት ብርጋዲየር ጄኔራሎች ደግሞ የሜጀር ጄኔራልነት ማዕረግ መስጠቱን ምንጮቹ ያስታውሳሉ። በተለይም ሃያ ሶስቱ ተሿሚ ጄኔራሎች የትግራይ ተወላጅ እንዲሆኑ መደረጉን አጥብቀው ይኮንናሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት በፊት በጥድፊያ የወታደራዊ ሹመት መቅደሙ የህወሓትን የፖለቲካ ሚዛን መናጋት እንደሚያሳይ ያመለከቱት ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር፣ “ህወሃት አነስተኛ ቁጥር የሚወክል ድርጅት ሆኖ የፖለቲካ የበላይነቱን እንደ ቀድሞው መቆጣጠር ስለማይችል የጦር ኃይሉን በማጠናከር አመራሩን በወታደራዊና በደህንነት ሃይሉ ቁጥጥር ስር አድርጎ ከጀርባ መሪነቱን ለማጠናከር የወሰደው ርምጃ ከመለስ ሞት መሰማት ማግስት ሲሰራበት የቆየ ነበር” ብለዋል።

የህወሓት የቀድሞ የፖለቲካ የበላይነት ከአቶ መለስ ህልፈት ጋር እንዳከተመ የሚናገሩት ምንጮች መለስ ህይወታቸው ካለፈበት ጊዜ አንስቶ ኃይል የማሰባሰቡ ስራ ብዙም ስላልተሳካ ህወሓት የጦር ኃይሉን ከቀድሞው በተለየ ወደ ፖለቲካ ወሳኔ ሰጪነት ለማዛወር መወሰኑን አመልክተዋል።

“ሹመቱ የአገሪቱን የመከላከያ ኃይል ለማጠናከር ቢሆን መልካም ነበር። አሁን እየሆነ ያለው ግን ወታደራዊ መንግሥት በመትከል ክልሎችን በጣጥሶ በሃይል ለመቆጣጠር የሚደረግ ሩጫ ነው። ለዚህም ማረጋገጫው ሹመቱ የቀድሞውን ሳያካትት የአንድ ብሄር ታማኞች እንዲበዙበት መደረጉ ነው” የሚሉት ሌላው ምንጫችን “በቅርቡ የጄኔራል ማዕረግ የነበራቸውን መኮንኖች ቁልፍ በሆኑ ተቋማት ውስጥ በሲቪል የመንግሥት ሠራተኝነት ስም በከፍተኛ ሥልጣን ላይ (እስከ ሚኒስትር በሚደርስ) ለመመደብ ተዘጋጅቷል። ይህም የሚከናወነው በመተካካት ስም ነው” ብለዋል።

በህወሓት ዘንድ የተከሰተውን የሚዛን መዋዠቅ ፍርሃቻና የጉልበት መላላት ለማጠናከር የቀድሞ ታጋዮች መሰባሰብ መጀመራቸውም ተሰምቷል። መለስ እያሉ መሰረታዊ የህግና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንስተው ዳግም የተደራጁት የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ድርጅታቸውን ለመርዳት ተሰባስበዋል። ይሁን እንጂ ድርጅቱ ለሁለት በተከፈለበት ወቅት አቶ መለስን ወግነው አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን እንደማይቀበሉ እየተሰማ ነው።

“ውህዳን” ተብለው ከህወሓት የተባረሩትን የሚደግፉ ክፍሎች ከመከላከያና ከደህንነት ባለስልጣናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላላቸው አንዳንድ የህወሓትና ሰርጎ ገብ የብአዴን አባላትን ማሳሰቡን የጠቆሙት ለጉዳዩ ቅርበት ያለቸው ክፍሎች፣ “ህወሓት አቶ አባይ ጸሃዬን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ማድረግ የለበትም” የሚል አቋም እንደሚታይባቸው ጠቁመዋል። በሌላ ወገን ደግሞ አቶ አባይ ጸሃዬን የህወሓት ሊቀመንበር ለማድረግ የመለስ ታማኞች እየሰሩ መሆኑን ያመለከቱት እኒህ ክፍሎች፣ የመጀመሪያ ምርጫቸው ግን አቶ ደብረጽዮን እንደሆኑ አስረድተዋል። አቶ ደብረጽዮን ቁጥር አንድ የሚባሉ የመለስ ታማኝ፣ የክፍፍሉን ጊዜ መለስ ባሸናፊነት እንዲወጡ ከገጠር እስከ ከተማ የሰሩና ጭካኔ የሚጠይቁ ውሳኔዎች ላይ የማያቅማሙ ከፍተኛ የደህንነት ሰው መሆናቸውን ጠቅሰን በሌላ ዜና መዘገባችን ይታወሳል።

በተመሳሳይ ዜና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በህግ ከሚያዘው ውጪ በደኅንነት አባላት ቁጥጥር ስር እንዲሆን መደረጉን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ይህ የተደረገበትን ምክንያት ሲያብራሩም “ድንገት የማፈንገጥና ከህወሓት ፍላጎትና እምነት ውጪ የሚወሰን ውሳኔ ቢኖር አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያመች ተብሎ የተደረገ ነው” ብለዋል።

ኢህአዴግ ፓርቲ ሊሆን ነው!!

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከመንገድ እየለቃቀመ ያቋቋማቸውን ድርጅቶች አሰባስቦ ራሱን ግንባር አድርጎ ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በሥልጣን ላይ ቆየው ኢህአዴግ ከግንባርነት ወደ ኅብረብሔር ፓርቲነት የሚሸጋገርበትን ጊዜ ሊያፋጥን እንደሆነ ተሰማ። ግንባሩ ፓርቲ ሲሆን በውስጡ የተካተቱት ፓርቲዎች ይከስሙና አደረጃጀታቸው በአዲሱ ፓርቲ ጥላ ስር ይሆናል፡፡

የጎልጉል የኢህአዴግ ምንጮች እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ወደ ኅብረብሔር ፓርቲነት እንዲሸጋገር ታስቦ የነበረው ከስድስት ዓመት በፊት ሃዋሳ ተካሂዶ በነበረው የድርጅቱ 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነበር። በወቅቱ የግንባሩ ወደ ኅብረ ብሄር ፓርቲነት የመሸጋገር ጥያቄ በቂ ጥናት ተደርጎበት ከሁለት ዓመት በኋላ ኦሮሚያ ጨፌ አዳራሽ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ይፋ እንደሚደረግ ከስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር።

ቀደም ሲል ከጉባኤ ጉባኤ ሲተላለፍ የቆየው ኢህአዴግን ወደ ፓርቲ የማሳደግ አጀንዳ አሁን ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደው ህወሓት በከፍተኛ የጦር ኃይልና የደኅንነት አቅም የበላይነቱን ካጠናከረ በኋላ “አገሪቱን አቅም ያላቸው ይምሯት” በሚል በከፍተኛ ደረጃ አመራሩን ለመቆጣጠር እንዲያስችለው ነው የሚል መላምት እየተሰጠ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቶቹ ውህደት ከፈጠሩ የፓርቲዎቹ ንብረት ስለሚዋሃድ ይህ ሃሳብ ከህወሓት ሊመነጭ እንደማይችል ዜናውን ከሰሙ ጀምሮ የማይቀበሉት ወገኖች አሉ።

የጎልጉል ምንጮች እንደሚሉት ግን ዝርዝር ጥናቱን እጃቸው የገባ ባይሆንም ኢህአዴግን ከግንባር ወደ ኅብረብሔር ፓርቲነት የማሸጋገሩ ስራ በጥብቅ እየተሰራበት እንደሆነ እንደሚያውቁ አስረድተዋል። ስለ ህወሓት የቀድሞ ታጋዮችና በአገሪቱ ህዝብ ላይ ሱቅ በደረቴ ከፍተው የሚነግዱ ጥቃቅን መንግስታት የአገሪቱ የወደፊቱ የለውጥ ስጋቶች ስለመሆናቸው ጠቅሰው ቃለምልልስ የሰጡትን የኢህአዴግ ሰው ሙሉ ቃለመጠይቅ እዚህ ላይ ያንብቡ።

(ሐብታሙ ሂካ ያምቦ፤ Habtamu Hiikaa Yaamboo; habtamu@goolgule.com)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule