• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር?!

September 14, 2012 09:08 am by Editor Leave a Comment

ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት ህወሓት የፖለቲካ የበላይነቱ ለመመናመኑ ምልክት መሆኑ ተጠቆመ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የህግ ለውጥ ሳይደረግ በደህንነት ሹሞች የቅርብ ቁጥጥር ስር መዋሉም ተሰማ። የጎልጉል ምንጮች ያነጋገሩዋቸው ክፍሎች መለስ በህይወት እያሉ ሁሉንም ቁልፍ ይዘውት ስለነበር ህወሃት የፖለቲካ የበላይነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ስለነበር የጦር ኃይሉ በፖለቲካው ዘርፍ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሲሆን አይታይም ነበር።

ኢትዮጵያን ወደ ፍጹም ወታደራዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ደፋ ቀና ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ህልፈት ሲያስተባብል የቆየው ኢህአዴግ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ለሰላሳ አራት ከፍተኛ መኮንኖች የብርጋዲዬር ጄኔራልነት፣ ለሶስት ብርጋዲየር ጄኔራሎች ደግሞ የሜጀር ጄኔራልነት ማዕረግ መስጠቱን ምንጮቹ ያስታውሳሉ። በተለይም ሃያ ሶስቱ ተሿሚ ጄኔራሎች የትግራይ ተወላጅ እንዲሆኑ መደረጉን አጥብቀው ይኮንናሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት በፊት በጥድፊያ የወታደራዊ ሹመት መቅደሙ የህወሓትን የፖለቲካ ሚዛን መናጋት እንደሚያሳይ ያመለከቱት ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር፣ “ህወሃት አነስተኛ ቁጥር የሚወክል ድርጅት ሆኖ የፖለቲካ የበላይነቱን እንደ ቀድሞው መቆጣጠር ስለማይችል የጦር ኃይሉን በማጠናከር አመራሩን በወታደራዊና በደህንነት ሃይሉ ቁጥጥር ስር አድርጎ ከጀርባ መሪነቱን ለማጠናከር የወሰደው ርምጃ ከመለስ ሞት መሰማት ማግስት ሲሰራበት የቆየ ነበር” ብለዋል።

የህወሓት የቀድሞ የፖለቲካ የበላይነት ከአቶ መለስ ህልፈት ጋር እንዳከተመ የሚናገሩት ምንጮች መለስ ህይወታቸው ካለፈበት ጊዜ አንስቶ ኃይል የማሰባሰቡ ስራ ብዙም ስላልተሳካ ህወሓት የጦር ኃይሉን ከቀድሞው በተለየ ወደ ፖለቲካ ወሳኔ ሰጪነት ለማዛወር መወሰኑን አመልክተዋል።

“ሹመቱ የአገሪቱን የመከላከያ ኃይል ለማጠናከር ቢሆን መልካም ነበር። አሁን እየሆነ ያለው ግን ወታደራዊ መንግሥት በመትከል ክልሎችን በጣጥሶ በሃይል ለመቆጣጠር የሚደረግ ሩጫ ነው። ለዚህም ማረጋገጫው ሹመቱ የቀድሞውን ሳያካትት የአንድ ብሄር ታማኞች እንዲበዙበት መደረጉ ነው” የሚሉት ሌላው ምንጫችን “በቅርቡ የጄኔራል ማዕረግ የነበራቸውን መኮንኖች ቁልፍ በሆኑ ተቋማት ውስጥ በሲቪል የመንግሥት ሠራተኝነት ስም በከፍተኛ ሥልጣን ላይ (እስከ ሚኒስትር በሚደርስ) ለመመደብ ተዘጋጅቷል። ይህም የሚከናወነው በመተካካት ስም ነው” ብለዋል።

በህወሓት ዘንድ የተከሰተውን የሚዛን መዋዠቅ ፍርሃቻና የጉልበት መላላት ለማጠናከር የቀድሞ ታጋዮች መሰባሰብ መጀመራቸውም ተሰምቷል። መለስ እያሉ መሰረታዊ የህግና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንስተው ዳግም የተደራጁት የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ድርጅታቸውን ለመርዳት ተሰባስበዋል። ይሁን እንጂ ድርጅቱ ለሁለት በተከፈለበት ወቅት አቶ መለስን ወግነው አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን እንደማይቀበሉ እየተሰማ ነው።

“ውህዳን” ተብለው ከህወሓት የተባረሩትን የሚደግፉ ክፍሎች ከመከላከያና ከደህንነት ባለስልጣናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላላቸው አንዳንድ የህወሓትና ሰርጎ ገብ የብአዴን አባላትን ማሳሰቡን የጠቆሙት ለጉዳዩ ቅርበት ያለቸው ክፍሎች፣ “ህወሓት አቶ አባይ ጸሃዬን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ማድረግ የለበትም” የሚል አቋም እንደሚታይባቸው ጠቁመዋል። በሌላ ወገን ደግሞ አቶ አባይ ጸሃዬን የህወሓት ሊቀመንበር ለማድረግ የመለስ ታማኞች እየሰሩ መሆኑን ያመለከቱት እኒህ ክፍሎች፣ የመጀመሪያ ምርጫቸው ግን አቶ ደብረጽዮን እንደሆኑ አስረድተዋል። አቶ ደብረጽዮን ቁጥር አንድ የሚባሉ የመለስ ታማኝ፣ የክፍፍሉን ጊዜ መለስ ባሸናፊነት እንዲወጡ ከገጠር እስከ ከተማ የሰሩና ጭካኔ የሚጠይቁ ውሳኔዎች ላይ የማያቅማሙ ከፍተኛ የደህንነት ሰው መሆናቸውን ጠቅሰን በሌላ ዜና መዘገባችን ይታወሳል።

በተመሳሳይ ዜና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በህግ ከሚያዘው ውጪ በደኅንነት አባላት ቁጥጥር ስር እንዲሆን መደረጉን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ይህ የተደረገበትን ምክንያት ሲያብራሩም “ድንገት የማፈንገጥና ከህወሓት ፍላጎትና እምነት ውጪ የሚወሰን ውሳኔ ቢኖር አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያመች ተብሎ የተደረገ ነው” ብለዋል።

ኢህአዴግ ፓርቲ ሊሆን ነው!!

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከመንገድ እየለቃቀመ ያቋቋማቸውን ድርጅቶች አሰባስቦ ራሱን ግንባር አድርጎ ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በሥልጣን ላይ ቆየው ኢህአዴግ ከግንባርነት ወደ ኅብረብሔር ፓርቲነት የሚሸጋገርበትን ጊዜ ሊያፋጥን እንደሆነ ተሰማ። ግንባሩ ፓርቲ ሲሆን በውስጡ የተካተቱት ፓርቲዎች ይከስሙና አደረጃጀታቸው በአዲሱ ፓርቲ ጥላ ስር ይሆናል፡፡

የጎልጉል የኢህአዴግ ምንጮች እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ወደ ኅብረብሔር ፓርቲነት እንዲሸጋገር ታስቦ የነበረው ከስድስት ዓመት በፊት ሃዋሳ ተካሂዶ በነበረው የድርጅቱ 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነበር። በወቅቱ የግንባሩ ወደ ኅብረ ብሄር ፓርቲነት የመሸጋገር ጥያቄ በቂ ጥናት ተደርጎበት ከሁለት ዓመት በኋላ ኦሮሚያ ጨፌ አዳራሽ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ይፋ እንደሚደረግ ከስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር።

ቀደም ሲል ከጉባኤ ጉባኤ ሲተላለፍ የቆየው ኢህአዴግን ወደ ፓርቲ የማሳደግ አጀንዳ አሁን ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደው ህወሓት በከፍተኛ የጦር ኃይልና የደኅንነት አቅም የበላይነቱን ካጠናከረ በኋላ “አገሪቱን አቅም ያላቸው ይምሯት” በሚል በከፍተኛ ደረጃ አመራሩን ለመቆጣጠር እንዲያስችለው ነው የሚል መላምት እየተሰጠ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቶቹ ውህደት ከፈጠሩ የፓርቲዎቹ ንብረት ስለሚዋሃድ ይህ ሃሳብ ከህወሓት ሊመነጭ እንደማይችል ዜናውን ከሰሙ ጀምሮ የማይቀበሉት ወገኖች አሉ።

የጎልጉል ምንጮች እንደሚሉት ግን ዝርዝር ጥናቱን እጃቸው የገባ ባይሆንም ኢህአዴግን ከግንባር ወደ ኅብረብሔር ፓርቲነት የማሸጋገሩ ስራ በጥብቅ እየተሰራበት እንደሆነ እንደሚያውቁ አስረድተዋል። ስለ ህወሓት የቀድሞ ታጋዮችና በአገሪቱ ህዝብ ላይ ሱቅ በደረቴ ከፍተው የሚነግዱ ጥቃቅን መንግስታት የአገሪቱ የወደፊቱ የለውጥ ስጋቶች ስለመሆናቸው ጠቅሰው ቃለምልልስ የሰጡትን የኢህአዴግ ሰው ሙሉ ቃለመጠይቅ እዚህ ላይ ያንብቡ።

(ሐብታሙ ሂካ ያምቦ፤ Habtamu Hiikaa Yaamboo; habtamu@goolgule.com)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
  • የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ October 9, 2026 12:33 pm
  • ሴቶችን በመሾም ኢትዮጵያ በእርግጥ ተወዳዳሪ የሌላት ነች?  October 8, 2026 11:20 pm
  • Ethiopian Defense Forces Capture Advanced TPLF Military Drones and Documents Linked to Sudan October 7, 2026 12:40 pm
  • በሱዳን በኩል ለትህነግ የተላኩ የM6 ድሮኖችና ወታደራዊ መሣሪያዎች በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተገለጸ October 7, 2026 11:20 am
  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
Copyright © 2026 · Goolgule