እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል እንባ ከየት አባቱ ደርቋል ከረጢቱ: ሳቅ ሳቅም ይለኛል ስቆ ላይስቅ ጥርሴ ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነብሴ:: (በአሉ ግርማ “ኦሮማይ”) ምነው! ፈጣሪ አምላክ! አላለቅስም ያልኩት ... እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣ አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣ ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን ምነው? የኛን ጩኸት ሰምተህ ጨከንክብን ብዬ ወተውትኩት አልኩበት እዬዬ አሁንም ይፈሳል አልቆመም እንባዬ ምነው! ፈጣሪ አምላክ! ... ወለላዬ የዛሬ 25 ዓመት ህወሃት የጀመረው በዚህ ነበር - … [Read more...] about #ተቃውሞ #እምቢተኝነት #ተጋድሎ
Politics
ኢትዮጵያ፡ #ከተቃውሞ እና #ከተጋድሎ በኋላ!?
አሰላሙ አሌይኩም፣ እንደምን አላችሁ፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone)፡፡ የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡[1] ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ ይህም ቀውስ በአንድ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ለዓመታት ሲጠራቀምና ሲከማች የቆየ ነው፡፡ የአገራችን የወደፊት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስበን በመሆኑ እናንተም ይህንኑ ሃሳብ እንዳቀርብ በጠየቃችሁኝ መሠረት እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በመሥራት ለአገራችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ማምጣት እንዴት እንደምንችል ሃሳቤን ከዚህ … [Read more...] about ኢትዮጵያ፡ #ከተቃውሞ እና #ከተጋድሎ በኋላ!?
ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራው ሕዝብ ላይ የዘር ዕልቂት (genocide) አወጀ
በአማራ ክልል እየተቀጣጠለ የመጣውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት (#AmharaResistance) ፖለቲካዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የመከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስድ ሃይለማርም ደሳለኝ በኦፊሴል አዟል፡፡ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ሙሉ ቁጥጥር ሥር ያለው የሃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን በየቦታው “በቃን፤ አንፈልግም” የተባለውን የህወሃት የበላይነትን እንደገና ለማስፈን የጦርነት አዋጅ አውጇል፡፡ በኦሮሚያ (#OromoProtests) ለ10 ወራት የዘለቀው የኦሮሞን ሕዝብ የመፍጀት ሥልታዊ ጥቃት አሁንም የበርካታዎችን ደም እያፈሰሰ ባለበት ባሁኑ ወቅት በአንድ ክልል ሕዝብ ላይ የተነጣጠረው ይህ በሃይለማርያም ትዕዛዝ የተሰጠው የህወሃት እርምጃ ታሪክ የማይረሳው፣ ሰላም ሊያመጣ የማይችል፣ የዕድሜ ልክ ቁርሾ የሚያስከትል የዘር ማጥፋት (genocide) ወንጀል … [Read more...] about ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራው ሕዝብ ላይ የዘር ዕልቂት (genocide) አወጀ
ኦሮሞና አማራ – “ሁለት ዛፎች”!
ኦሮሞ እና አማራ “እሣት እና ጭድ ናቸው” ብላችሁ ክብሪት ለመጫር ለምትቋምጡ የወያኔ ሎሌዎች የሚከተለውን ብትገነዘቡ መልካም ነው፡፡ 1) ኦሮሞ እና አማራ መታየት ያለባቸው እንደ እሳት እና ጭድ ሳይሆን ጎን ለጎን በቅለው ለረጅም ጊዜ አብረው እንዳደጉ ትልልቅ ዛፎች ነው። እነዚህ ዛፎች ለረዥም ጊዜ ተጎራብተው ከመኖራቸውና ከግዙፍነታቸው የተነሳ በመሬት ውስጥ የተሳሰሩት ሥሮቻቸው ምግብ ሊሻሙ ይችላሉ። በአየር ላይ የሚነካኩት ቅርንጫፎቻቸው በንፋስ ጊዜ እርስበእርስ ሊላተሙ ይቻላሉ። ነገር ግን ዛፎቹ ሥር የሰደዱና የተዋሃዱ እንደመሆናቸው መቼም ውሃ አያጡምና፣ እንደ ጭድ ደርቀው በክብሪት እሣት አይቀጣጠሉም። 2) ምናልባት ከሁለቱም ዛፎች ደርቀው የረገፉ ቅጠሎችን እና ጭራሮዎችን ተጠቅማችሁ እሳት መለኮስ ካሰባችሁም ጉዳቱ ለናንተው እንደሚያመዝን እውቁ። የምትለኩሱትን እሳት የንፋስ … [Read more...] about ኦሮሞና አማራ – “ሁለት ዛፎች”!
የሰሜን ምዕራብ ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ነገ…
* ኢህአዴግ የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዞታል * ከገዳዮች ቁጥር በላይ ለመሞት የተዘጋጀዉ ህዝብ ይበልጣል እንደ መግቢያ የኢትዮጵያን ነገረ-ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ የአገር ውስጥና የምዕራቡ አለም ምሁራን የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን ያደርጋል ብለው በተስፋ ቢጠብቁም ከታሰበው በተቃራኒ መንገድ ሲጓዝ እየታየ ነው። ተራማጅ የፖለቲካ ሀሳብ ያረጠበት ድርጅት አፈናና ግድያ መገለጫው ሆኗል። የአገዛዙን ምሰሶ ለማጥበቅ ሲባል ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ የሌላቸውን የፖለቲካ ሹመቶች በመንግስታዊ መዋቅር ከመሰግሰግ ጀምሮ በፓርቲና በመንግስት መካከል ፍጹም ልዩነት የለሽ አሰራሮችን አጠንክሮ መጓዝን መፍትሄ አድርጎ ይዞታል። በአራት ነጥብ ግትር አቋም የታጠረው ኢህአዴግ፤ የፖለቲካ ተቋማት የፖለቲካ ብዝሃነትን እንዲያስተናግዱ ምቹ መደላድል ከመፍጠር ይልቅ የአንድ ፓርቲ ፍጹም … [Read more...] about የሰሜን ምዕራብ ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ነገ…
“ለባለ ራዕዩ” 4ኛ ሙት ዓመት “ተዝካር”
ይህ ቃለ ምልልስ “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ May 20, 2013 አትመነው ነበር፡፡ የኢትዮጵያን የውድቀት ጉድጓድ ሲቆፍሩ የነበሩትና በአገዛዝ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ጉድጓዱን በጥልቀት ሲቆፍሩ የነበሩት መለስ ከኢትዮጵያ ቀድመው ጥልቁ ጉድጓድ ገብተዋል፡፡ ዛሬ በሙት መንፈስ የሚመሩት “ተዝካራቸውን” የሚያወጡበት ቀን ነው፡፡ ለዝክሩ ይህንን ደግመን አቅርበነዋል፡፡ ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ … [Read more...] about “ለባለ ራዕዩ” 4ኛ ሙት ዓመት “ተዝካር”
ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
አንድ በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡ ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ … [Read more...] about ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
እሁድ እለት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል። ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም። ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። … [Read more...] about መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡ የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት … [Read more...] about የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ምስለ – ብአዴን
ለፖለቲካ ስልጣን ሁለተኛነት ሁሌም የሚጫወተዉ ብአዴን፤ ኢሕኢፓ በገጠመው የመበታተን አደጋ ለኢሕዴን ጥንሰሳ ምክንያት የሆነው የበለሳ ንቅናቄውን በመጀመር ብዙዎች ወደ ደርግ ሲኮበልሉ፣ እልፎች ወደ ሱዳን ሲሰደዱ ‹‹ጥቂቶች ቆራጦች›› ህዳር 11/1973 ዓ.ም በህወሓት አጋፋሪነት ኢሕዴንን እንደመሰረቱ በግነታዊ ቃላት የታጀበው የድርጅቱ ታሪክ ያትታል፡፡ የዘመናዊው አርበኛ (ኢሕአፓ) ኃይል በደርግ፣ ሻዕብያና ወያኔ ታክቲካል ህብረት ውልቅልቁ በወጣበት ሂደት ውስጥ የተፈጠረው ኢህዴን ደርግን ለመጣል ካደረገው ወታደራዊ አበርክቶ ይልቅ የፖለቲካ አበርክቶው እጅግ ላቅ ያለ እንደነበር ይነገርለታል፡፡ በተለይም በሰሜን ምዕራብ፣ ደብረታቦር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሰሜን ሸዋን የመሳሰሉ የደርግ ጠንካራ ወታደራዊ ቤዞች የነበሩትን ቦታዎች ሰብሮ ለመግባት የኢሕዴን ውስን ሰራዊትና አመራሮች የየአካባቢውን … [Read more...] about ምስለ – ብአዴን