• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በኤሊባቡር ከ20 በላይ ዐማሮች በአንድ ቀን ብቻ በገጀራ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል

October 22, 2017 11:13 am by Editor 1 Comment

በኤሊ አባ ቦራ (ኤሊባቡር) ዞን ደጋና ጮራ ወረዳዎች የዐማራ ተወላጆች ተለይተው እየተጠቁ እንደሆኑ የተጎጅ ቤተሰቦች ትናንት ጥቅምት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በስልክ አረጋግጠዋል፡፡ መንግሥትን በመቃወም የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ ዐማሮችን በጅምላ መግደልና ቤትና ንብረታቸውን ወደ ማውደም መዞሩን የሚግልጹት ተጎጂዎች ትናንት ብቻ በአንድ ቀን ከ10 በላይ ሰዎች በገጀራ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፡፡

የዐማራ ተወላጆች ቤትና ንብረት እየወደ እንደሆነ የሚናገሩት በተለይ በደጋ ወረዳ ጎሮ፣ ሰፌና ደፎ ቀበሌዎች የዐማራ ቤትና ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችም በጫካ ተዘርተው እንደሚገኙ ገልጸውልናል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች የግድያው ዋና ተሰላፊ እንደነበሩም አክለው ገልጸዋል፡፡

ለጊዜው በጎሮ ቀበሌ የተገደሉ 6 ያክል ሰዎች ስም ዝርዝር የደረሰን ሲሆን የተቆራረጡ የዐማራ አስከሬኖች ሁሉ በጮራ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተከማችቶ እንደሚገኝም ተገልጧል፡፡ ትናንት ከተገደሉ ሰዎች መካከል፤

1. አቶ ክንዱ
2. አቶ ምስጋናው የዚህ ግለሰብ ገዳይ የክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባል ነው፤
3. አቶ ሙላት
4. አቶ ባቡ
5. አቶ ይማም
6. ሼህ ሁሴን ናቸው፡፡

በኤሊባቡር ጫካዎች ተዝርተው የሚገኙ ዐማሮች የድረሱልን ጥሪም አስተላልፈዋል፡፡

(ምንጭ: Muluken Tesfaw)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    October 27, 2017 02:17 am at 2:17 am

    ” በኢሉ አባ ቦራ..ቡኖ በደሌ ፰ ኦሮሞዎችና ፫ አማራዎች ሞቱ…በሰፊ ደጎቻ ቀበሌ የ፭ ዐማሮች ቤት ተቃጥሎ አድሯል።ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ወደ ጮራ የገጠር አካባቢዎች ቢሔድም የወረዳው አስተዳዳሪ ገጠር ችግር የለም፤ በከተማው አካባቢ የተወሰነ ግርግር ነበር አሁን ተረጋግቷል በሚል መልሷቸዋል፡፡በአንዳንድ አካባቢዎች ችግር ሊከሰት ይችላል በሚል የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የዐማራ ተወላጆችን ከቤታቸው ወጥተው በቀበሌ ጽሕ/ቤቶችና በገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡‹‹በቂ ገለልተኛ ጥበቃ ስለሌለ በአንድ ቦታ እንደተዘጉ በጅምላ የማለቅ እድል አላቸው›› ሥጋት አለ በማለት ዛሬም ኦክቶበር ፳፬ /፳፲፯ ዲማ ጋዮ በተባለ አካባቢ በዐማሮች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በርትቶ መዋሉን የሚገልጹት ተጎጂዎች በሁለቱም ወረዳዎች ከ፲፭ ሺህ በላይ ዐማሮች መፈናቀላቸውን የሚገልጹት ምስክሮች በምግብ እጦት የታመሙ ሕጻናት ሁሉ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
    ___________________!
    __ ይህ ሁሉ በኪራይ ሰብሳቢዎች የተቃጣ ነው ሲሉ አቶ አዲሱ አረጋ ያረጋጋሉ!? ማፈናቀል ወይም የሜንጫ ጭፍጨፋ የሱማሌና የኦሮሞ ባሕልና ወግ አደለም የሚሉት አቶ አዲሱ ኪራይ ሰብሳቢዎቹ የየት ሀገር ሰዎች እነደሆኑ አይጠቅሱም!? ይልቁንም በኦሮሚያ በሚባል ከልል የተገኘ ሁሉ መጤና የምኒሊክ ሰፋሪ ተብሎ ስለሚፈረጅ የከንባታ ተወላጆችን አስረው አማራን ገደሉ ብለው ለሚዲያ ማቅረብ በራሱ ሰብዓዊነት እና ሕግን የተከለ ውንጀላ አደለም።እነኝህም ታሳሪዎች የሚሞግትላቸው ሰው የሆነ ሰው ያስፈለጋቸዋል!።

    **ኢንን ቲሌቪዥንና እና ዛሚ ራዲዮ ላይ የተነሳ የፌደራሉ የኮምኒኬሽን ሚ/ር እና የክልሉ ቃል አቀባይ ተቀናጅተው ያቀረቡት ጠንካራ ትችት/ከስ/ዛቻ/ማስፈራሪያ ምን እደሆነ አለየትም። ግን ይህ ዳውን ዳውን ወያኔ! ዴሞክራሲ! ፊሪደም! ነፃ ፕረስ ! እየተባለ ተቃዋሚ/ታቋቋሚ ተብዬዎች በተለያዩ አህጉሮች የሚጮኸው አያድርገውና ወደፊት ሥልጣን ቢኖረው ሚዲያውን ቢቆጣጠር ችግሮችን ለመደበቅ፡ ለማጥፋት፡ ለማዛባት ከሆነ ከደርግ/ኢህአዴግ ተቋዋሚው በምን ሊለይ ነው!? ማናቸውም የሕዝብ ጉዳይ በወቅቱ ጉዳዩ ለሚመለከተው ባልሥልጣን አካልና ችግሩ ለደረሰበት ወገን ማድረስ ወይም የሀግር ሠላምና የሕዝብ ደህንነት ለሚያገባው ዜጋ ነቅቶ እንዲጠብቅ በሰበር ዜና ማቅረብ ወንጀሉ የት ጋ ነው? የእንግሊዙ አርሰናል ቸልሴን አሸነፈ በሚል ሰበር ዜና ነው ወጣቱ የነፈዘው ብላችሁ ነው? ሕዝቡ የሚፈለገው የስኳርና ዘይት መጣ መብራት ይጠፋል ኢንተርኔት ይቋረጣል ሰበር ዜና ብቻ ነው ? መንግስት ይህንን ጭፍጨፋ፡ ንብረት ማወደምና ማፈናቀል ከአንድ ወር በኋላ ቢያወራው ጥሩ ነበር ? ማናቸውም ኦሮሚያ ውስጥ የሚጠፋ የሰው ሕይወት የንብረት ውድመት ሁሉ ጸጋ ሲሆን በኦሮሞ ላይ የሚደርስ ሁሉ የዘር ጥፋት የዓለም መጨረሻ እያደርጉ ማቅረብ እጅግ በጣም አሳፍሪና እርባና ቢስነት ነው።
    ** በዚህ አጋጣሚ ግለስቡ የዘር ወይም የፖለቲካ ቱማታ ውስጥ የገባሁ ስላልሆነ በሕግ አንጻር ..የሕዝብ ግንኝነት ኅላፊው አቶ ነገሪ ሊንጮ…ወይም አቶ አዲሱ እረጋሳ ፌደራላዊ ሥርዓቱ ምንነት ሆነ የሚዲያ ሕግ አጠቃቀም ሥርዓትን የሚቃረን ጉዳይ ገጠሟቸው ሳይሆን ጄነራል አባዱላ የሥራ ማቆም ምክንያት በሚዲያ የሰጡት ዝግ የሆነ ዓረፈተነገር “ሕዝቤ ስለተጎዳ..ይህን ያህል ሥልጣን ይዤ ሕዝቤ ሲናቅ እያየሁ በዚህ ባለሁበት ሁኔታ መቀጠል ስላልቻልኩ” ያሉት ግልፅ አደለም?አልተብራራም? የተባለው ዓረፍተነገር የበታችነት ስሜትን ጭሮባቸዋል። አቶ ዘርዓይ አስገዶም በአደባባይ ዶር ነጋሪ የተናገሩት በማጣጣል ለነ ሚሚ ስብሃቱ ድጋፋቸውን የሰጡበትን ሁኔታ ሳይሆን ነገሩ ሲጀምርም የውደቀ ስለሆነ ነው። ጄነራሉ ቆሜለታልሁ ለሚሉት ኦሮሞ ሕዝብ ደረሰበት ያሉትን ጉዳትና የህወሓት መር ንቀቱን በዛሚ ኤፍ ኤምና እና ፋና ቲሌቪዥን ቀርበው በነጻና በነጻነት ቢያፍረጠርጡት ሌላውም የክልል ቀበኛ/ሆድ አደር ሁሉ ትምህርት ያገኝ ነበር። ይህ ግን ጭራ ሸጉጦ ሽሽት/ስልታዊ ማፈግፈግ ነው። ኦሚኔ ያልዘገበው ሁሉ ወንጀል ከሆነ አደጋ አለ።
    __ በመሠረቱ የቀደሞው አፈጉባኤ የአሁኑ የኦህዴድ ልዩ መልከተኛ ጄነራል አባዱላ ገመዳ በዛሚ ኤፍ ኤም ወይም ኢ ኢን ኢን ቲቪ ቀርበው መሞገት የውዴታ ግዴታቸው ነበር። ግን አሁን ጋሻ ጃግሬዎቻቸውን ጃስ ብለው ሥሜ ለምን ተጠቀሰ? ከዚህ በፊትም ስለአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የተቃወምኩት ለኦሮሞ ሕዝብና ለወከልኩት ፓርቲ ኦህዴድ ነውና ሕዝቤን አጯጩሁልኝ ካሉ መዘዝ አለው !? ዓሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…! ለኦሮሞ ሕዝብ አሳቢ የከተማ ለማትና ስፋት አይከለክልም/አይቃወምም የሚከለክለው የሚያሳድምና ንብረት የሚያጠፋው ኪራይ ሰባሳቢው አካል ነው አባዱላ የማን ወግን ሆነው የአዲስ አበባን መስፋት ሲቃወሙ የአዲስ አበባን ፊንፊነ… የመንገድና የሥራ ቋንቋ መለወጥን ከዲሲ/ከሜኒሶታ የሜንጫ አብዮተኞች ጋር ለምከር የነፃ አወጭ ሚዲያ ሲያቋቁሙ ሲኳትኑ (አሸባሪ) ሳይባሉ፡ጭራሽም ከአሜሪካ አወስትራሊያ ካናዳ ‘ሬድ ኢንዲያንስ ‘አክት ቃል በቃል ነጠላ ሰረዝ ሳይቀር ኢንዲጂነስ (ሜጫና ቱለማ) አክት የፊንፊነ ሕግ አርቅቀው በግላቸው ፓርላማ ለማፀደቅ ሲሰሩ ኖሩ? በኩራትም ኦሮሞ በአሁኑ ወቅት ከውስጥም ከውጭም አንድ ነው ሲሉ ተኩራተዋል። ለምሆኑ ውጭ ማን አለ ጁነዲን፤ጀዋር፤አራርሳ እስቅዬል?
    ____ስለሆነም እርጥብ እሬሳ ደረቅ አስነሳ ከመባሉ በፊት እነኝህ አዳዲስ ዶ/ር..ፕሮፍ..ኢንጂነር ወጣት መሪዎች ቤታቸውን በደንብ ቢያፀዱ የተሻለ ነው። ይህ ቱሪናፋ/ቱማታ ያዋርዳል እንጂ በሕግ አንጻር ይሸነፋሉ? ይሾፍባቸዋልም ..ቢቻል በፍቅር ቢተላለፉ ይበጃል። በፖለቲካውም ቢሆን አማራና ኦሮሞን ነገድን ማቀራረቡን አላወቁበትም። ወጣቱ ጣና ኢትዮጵያ ኬኛ! ሲል በልጧቸዋል … ኦሮሞ በተንኮል ተከልሎ የበይ ተመለካች ሆኗል!!
    **አማራ ብዙ ቦታ በገሃድ በአዋጅ ተጠቅቷል…ከደቡም ክልልም ቢሆን ህወሓት/ትግሬ ፀብ ቀስቃሽም፡ አባባሽም ቢሆን ተጠያቂው የክልሉ አስተዳዳሪ ኦህዴድ ብቻ ነው። ባለፉት ፳፯ ዓመት ጉዞ በአብዛኛ ሁከት፡ ሰውና ንብረት ሠላም የጠፋው፡ ኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር ውስጥ ነው፡ ያ ማለት ክልሉ ለማስተዳደር የተሰጠውን ሕዝብና ከልላዊ ግዛት(መሬት) በሠላምና በዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ሕሳቤ መምራት ባለመቻሉ ካርታው ተቀንሶ፡ የሞግዚት አስተዳደር ይሾማል፡ ወይንም አካባቢው ለአስተዳደር አመቺና ለሕዝቦች አብሮ መኖር ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና፡ ድህነትን ለመዋጋት አስጊና አደገኛ በመሆኑ ይህንን የጫካ ልዩ ጥቅማጥቅም ውድቅ ያደረገ ኦሮሚያ ሰፈርን ልክ እንደጋራ ጠላታቸው የሸዋ ጠቅላይ ግዛትን በኅብረት አራት ቦታ እንደቆረሱና እንደበሉት ሁሉ ኦሮሞን አራት ቦታ ቆረጦ ከመቀነስ ሌላ አማራጭ የለም።ማናቸውም ዜጋ በኢትዮጵያዊ ተዘዋወሮ ወይንም ቋሚ ንብረት መሥርቶ የማይኖርባት ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል የለባትም! ከቀድሞው (አኅዳዊ) ሥርዓት የተሻለ ፌደራላዊ ሥርዓት ማለት ሀገራዊ እሴትና ሉዓላዊነትን በጎጥ፡ በቋንቋ፡ እየጠበቡ አደለም አስተዋይና በጋራ ሠርቶ፡ በጋራ ለማደግ ፍትሃዊ የሀበት ተጠቃሚ ለመሆን ማረጋገጫ ሲባል ብቻ በቀዬው ተወላጆች ይተዳደሩና ሁሉም የዕድገት ተፎካካሪ ይሁን ማለት ነበር። አሁን ግን አዝማሚያው ክልሌ፡ ሕዝቤ፡ መሬቴ፡ባሕሌ፡ ቋንቋዬ አትድረሱብኝ፡ አትበክሉኝ…ራስ ገዝ ነን፡ በፌደራል መንግስት አንመራም! ፅንፎችም ጎልተው ወጥተዋል ይህ ‘ ከዕውቀት ሳይሆን ከዕብደት’ ነው!።አራት ነጥብ።
    እየተስተዋለ ለሁሉም ሠላም!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule