• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አውሬውን አቁስለነዋል፤ ይህ ግን በቂ አይደለም” ለማ መገርሳ

December 27, 2017 12:57 pm by Editor 1 Comment

“አውሬው ቆስሏል*። ቆስሎ ስላልተኛ፣ ማቁሰሉ ብቻ በቂ አይደለም። ተመልሶ እንዳይመጣ እርግጠኞች መሆን አለብን።” የሚለው ቃል የወጣው ከ”ጽንፈኛው ዲያስፖራ” ወይንም ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አይደለም። ከአውሬው ጋር አጋር ሆኖ ከሚሰራ ድርጅት መሪ ነው። ያውም በገዥው ፓርቲ ልሳን። የ26 ዓመቱ ፖለቲካ እየተንከባለለ እዚህ ላይ ደርሷል። አንድ ሰው እውነትን በመናገሩ ጀርባው ተጠንቶ፣ ደሙ ተለክቶ፣ ግንባሩ ተገላልጦ፣ በሽብር በሚፈረጅባት ሃገር ውስጥ፣ ጥቂቶች የእድሜ-ልክ ፈራጅ ሆነው በተሰየሙበት ሃገር ይህ ተከሰት። እነ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዷለም አራጌ ከዚህ የባስ ነገር አልተናገሩም። በፍትህ ስም የሚቀለድባቸው እነ ፕ/ር መረራ ጉዲና እና በቀለ ገርባ ይህችን ያህል እንኳን አልተነፈሱም።

መቀሌ ላይ በዝግ ስብሰባ፣ አዲስ አበባ ላይ በዝግ ስብሰባ፣ ፓርላማውም በዝግ ስብሰባ። ሁሉም ተዘጋግቷል። በሃገሪቱ እና በህዝቧ ላይ በዝግ ይዶለታል። ለመፍትሄ ሳይሆን ስልጣን ይዶለታል። በግልጽ ሳይሆን በድብቅ ይዶለታል። መቶ በመቶ መርጦናል ላሉት ሕዝብ ችግሩን ለመደበቅ ይሞክሩ እንጂ፣ ምጣድ ላይ እንዳለ ቡና የሚያምሳቸው ነገር አደባባይ ላይ እንደተሰጣ እንኳ አልባነኑም። ስውር ድርጊታቸው እየገዙት ላለው ሕዝብ ባይተዋር ስለመሆናቸው ማስረገጫ ይሆናል።

ለ35 ቀናት መቀሌ ላይ ዘግተው የዶለቱት፣ ከዚያም አልፈው የነቀሉት እና የተከሉት ነገር፣ መስመር እንደያዘላቸው ተናግረዋል። የህልውናቸው መሰረት የሆነው የመደምሰስ እና የመቆጣጠር ፖሊሲ፣ የህወሃት ስብሰባ ላይ ሰርቶላቸው ሊሆን ይችላል። ሰሜን ላይ ያበጠውን ጎማ አተንፍሰው ሲያበቁ፣ ስንቅ እና ትጥቅ ይዘው ወደ ሸገር ነበር የዘመቱት። እነ ለማን ለማንበርከክ፣ እነ ገዱን ለመጠምዘዝ።

የሸገሩ ዱለታ እንደታሰበው አልሄደም። የመቀሌውን የፖለቲካ ፎርሙላ የአዲስ አበባው ኢህአዴግ ስብሰባ ላይ ለመተግበር መጣራቸው ጅል ያደረጋቸው ነው የሚመስለው። ወትሮውን እንደሮቦት የሚታዘዙ አጋሮቻቸው ባትሪያቸውን እንደጨረሱ አላስተዋሉትም። በሞግዚት አስተዳደሩን ቀጥሉበት-አንቀጥልም ትንቅንቅ፤ በቀድሞው የኢህአዴግኛ  ቋንቋ መግባባት አልቻሉም። እነ ለማ መገርሳን እንደ ቀድሞው ለማዘዝ የማይችሉበት ቅርቃር ውስጥ ተሸንቁረዋል።

የትርምሳቸው ክብደት በኪሎ ባይመዘንም፣ ከጥልቅ ተሃድሶ ወደ ጥልቅ ዝቅጠት መግባታቸውን ግን በይፋ ነግረውናል። ትላንት በስብሰናል ብለው ነበር፣ ዛሬ ዘቅጠናል ብለዋል። ነገ ደግሞ ተልተናል ማለታቸው የሚጠበቅ ነው። የበሰበሰ ነገር የሚያዘግመው ወደዚያው ነው።

እዚያ አካባቢ ነገሮች በፍጥነት ተቀያይረዋል። እንደ ጅብ ከተሰበሰቡበት ዋሻ ለአፍታ ወጣ አሉና  በብሄራዊ ቴሌቪዥን፣ “ሰላም ነን” ለማለት ሞክረው ነበር። “ውስጡን ለቄስ” አሉ። በዚህ አባባላቸው፤ ጉልበታቸውና ፀጋቸዉ እንደበግ ቆዳ ከላያቸው ተገፍፎ እንደሄደ ለማወቅ የፖለቲካ ተንባይ መሆን አያስፈልግም።

“በመሃላችን የርስበርስ መተማመን ጠፍቷል!” ይላል በዝጉ ስብሰባ መሃል የተሰጠው መግለጫ። ይህንን መግለጫ በገለልተኛ ሜዲያ ብንሰማው ኖሮ ላይደንቀን ይችላል። እንግዳ የሆነብን ይህንን መግለጫ በራሳቸው ልሳን መስማታችን ብቻ ሳይሆን፣ ስብሰባው ገና ሳያልቅ መግለጫ መልቀቃቸው ነው። አሁንም ሃገሪቱ የገባችበት ችግር ያስጨነቃቸው አይመስልም። እነሱን እንቅልፍ የነሳቸው አይበገሬ ብለው ያሰቡት የስልጣን ግንዳቸው መንገዳገዱ ነው። ይህንን ሕዝብ መቶ አመት ለመግዛት የወጣው የባለ ራዕዩ እቅድ መሃል ላይ መክሸፉ ነው ይበልጥ የሚያሳስባቸው።

በመግለጫቸው እርስበርስ ተከፋፍለናል ማለትን በመጸየፋቸው፤ አደባባይ የወጣ ክፍፍሉን “መተማመን ጠፋ” በሚል ቃል ሊያሽሞነሙኑት ሞከሩ። መዝቀጣቸውን ግን አልካዱትም። ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? የዘቀጠ እና የበሰበሰ ነገር ነፍስ ስለማይዘራ መፍትሄው ልክ እንደ እንቦጭ አራሙቻ መነቀል ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ዛሬ እነ ሚሚ ስብሃቱ የሚቀልዱባት ሃገር ለመሆን መብቃትዋ የመዝቀጣቸው ምልክት ለመሆኑ ቀድሞውንም ወለል ብሎ ይታይ ነበር። አንድ ሺህ ኦሮሞ ሲገደል ለነሱ ዜና አይደለም፣ አስር ሺህ አማራ ሲፈናቀልም ዜና አይደለም፣ ኮንሶ እንደባርያ ንግድ በሰንሰለት እየታሰረ ሲገረፍም የነዚህ ሰዎችን ትኩረት አይስብም። አንድ የትግራይ ተወላጅ ሲገደል ግን ሰበር ዜና ሆኖ ሃገር ይደበላለቃል። የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው ካሉን፣ ስብእናቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚጨምረው ይህ ነው። ማንነታቸው ጫፍ የሚፈተነው እዚህ ላይ ነው። የሰው ዘር ደሙ በካራት እየተለካ፣ የወርቅ፣ መዳብና ነሃስ ስያሜ ካመጣብን አገዛዝ ከዚህ የተሻለ ነገር አንጠብቅም።

አንዱን ዘር ከፍ ሌላውን ደግሞ ዝቅ በማድረጋቸው የተወደዱ በሚመስላቸው አድርባዮችና አሽቃባጮች ታጭቀው ረጅም መዝለቅ እንደማችሉ ይመስላል አዲስ ዘመን ጋዜጣ በርዕሰ አንቀፁ “የአገር ጠንቆችን ይዞ ማዝገም ለህዝብ እና ለመንግስት አደገኛ” መሆኑን የገለጸው። “አይጥ ርሃብ ሲጠናባት የራስዋን ጅራት ትበላለች” ይባል የለ።

ለማ መገርሳ በኦሮምኛ ቋንቋ በተደረገ አንድ ዘጋቢ ፊልም ላይ ነው “አውሬውን አቁስለነዋል” ያሉት። ምን ለማለት እና፣ ማንን ለማለትም እንደፈለጉ ግልጽ ነው። አንድን ዘር ከሌላ ዘር እያጋጨ፣ ጎሳን ከጎሳ እያተራመሰ፣ ሃይማኖትና ከሃይማኖት እንዳይተማመን እያደረገ የነበረው አውሬ ቆስሏል። ከ26 ዓመታት ስራው በኋላ ይህ ትውልድ የባነነበት አውሬ። የቆሰለ፣ በሞት እና በህይወት መካከል ያለ አውሬ፣  መፍጨርጨሩ የግድ ነው። መሬት ልሶም የመነሳት እድል ይኖረዋል። ጣልያናዊው ማኪያቬሊ የሚለውም ከዚህ ጋር ይመሳሰላል። አልጋወራሹ ላይ ከተኮስክበት ጨርሰው፤ ካልጨረስከው ይመለስብሃል። በሳል ፖለቲከኞች የማይጨርሱትን አይጀምሩትም።

በሽፍታ የምትተዳደር ሃገር፣ በሽፍቶች የሚገዛ ሕዝብ፤ …       ስብዕናቸውን ባዋረዱ በፖለቲካ ዘገምተኛ ምሁራን ጭምብል ውስጥ ተጠቅልለው፣ ኢትዮጵያን እንደምስጥ እየቦረቦሩ፣ እንደ መዥገርም እየመጠጡ እስካሁን ዘልቀዋል። አሁን ግን ቆስለው እየተወራጩ ይገኛሉ። “ሌባ ተብሎ ከመፈረጅ የበለጠ ውርደት በታሪክ ሊኖር አይችልም” ይሉናል ለማ መገርሳ።

እስካሁን የፖለቲካ ንግድ የሸቀሉበትን የሙት ራዕይም መቀሌ ላይ ቀብረውት መጥተዋል። የሟቹን መነጽር በሮቦቱ ሰው ላይ አድርገው፣ የጀመሩት ‘የመለስ ራዕይ’፣ ‘የመለስ ቅርስ’፣ ‘የመለስ ሌጋሲ’፣ ‘የመለስ ሕልም’ እና ‘የመለስ ውርስ’ ሁሉ ብዙ አላስኬደም። እንዲያው ያልተሳካ ተውኔት ሆኖ አለፏል። ይልቁንም ሰውዬው የአዜብን ደጅ ጠንተው ያገኟት የቤተ መንግስት ወንበር ዛሬ እሾህ ሆና እየወጋቻቸው መሆኑን እየተናገሩ ነው።

ብዙዎች ሃገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆንዋን ሲናገሩ ይሰማል። አቅጣጫው በውል የማይታወቅ ግራ የሚያጋባ መንገድ። መስቀለኛ ሚሆነው መንገዱ ሲኖር አይደል? በእኔ እይታ ግን መንገድ የለም። ሁሉም ተዘጋግቷል። በሁሉም አቅጣጫ የተዘጋጋ መንገድ መጓዝ ቅርቃር ውስጥ መግባት እንጂ መስቀለኛ ሊሆን አይችም።

ከዚህም ከዚያም ብሶት እና ሕዝባዊ ማዕበል እንሰማለን። አመጹ፣ ስርዓቱን አላፈናፍን ያለው ይመስላል። ውጥረቱ ሊላላ የማይችልበት፣ እሳቱ ሊጠፋም የማይችልበት ደረጃ ደርሷል። ግን የህወሃት ቀብር እስከመጨረሻው የሚፈጸመው፣ አዲስ አበባ ሲያምጽ ብቻ መሆኑ ግልጽ ነው። መታሰር፣ መሰቃየት እና መገደልን ለምዶታል፣ መታረዝ እና መራብ አዲስ አይደለም። ውሃ፣ መብራት፣ ስልክ፣ … ሲፈልጉ የሚሉቅቁት ሲያሻቸው ደግሞ የሚከለክሉት ሕዝብ፣ አይቶ እንዳላየ ይምሰል እንጂ ልቡ ሸፍቷል። ይህ ህዝብ ጽዋው ሞልቶ እለት የት እንደሚገቡ እናያለን።

 አመጽ በቀጠሮ አይነሳም። መምጫው ባይታወቅም፣ ምልክቶች ግን ይታያሉ።

“መጀመሪያ ይንቁሃል። ከዚያ ቀጥሎ ይስቁብሃል። ገፋ ብለው ይጣሉሃል። … በመጨረሻ ግን ታሸንፋቸዋለህ!” ማህተመ ጋንዲ።

* ከዚህ ላይ የተወሰደ ነው (ፎቶ: ከግራ ወደቀኝ ፓስተር ገመቺስ ቡባ፣ ጌታቸው ረዳ፣ የኦሮሞዎች መገደል ትክክል ነው ያለ አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እና ለማ መገርሳ)

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: eprdf, gimgema, Left Column, legacy, lemma, meles, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Abdisa says

    December 28, 2017 12:08 pm at 12:08 pm

    I think he threw this phrase to indicate the fighting with contraband dealers. I hope he did mean that he has wounded TPLT, OPDO’s Godfather.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule