“አውሬው ቆስሏል*። ቆስሎ ስላልተኛ፣ ማቁሰሉ ብቻ በቂ አይደለም። ተመልሶ እንዳይመጣ እርግጠኞች መሆን አለብን።" የሚለው ቃል የወጣው ከ"ጽንፈኛው ዲያስፖራ" ወይንም ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አይደለም። ከአውሬው ጋር አጋር ሆኖ ከሚሰራ ድርጅት መሪ ነው። ያውም በገዥው ፓርቲ ልሳን። የ26 ዓመቱ ፖለቲካ እየተንከባለለ እዚህ ላይ ደርሷል። አንድ ሰው እውነትን በመናገሩ ጀርባው ተጠንቶ፣ ደሙ ተለክቶ፣ ግንባሩ ተገላልጦ፣ በሽብር በሚፈረጅባት ሃገር ውስጥ፣ ጥቂቶች የእድሜ-ልክ ፈራጅ ሆነው በተሰየሙበት ሃገር ይህ ተከሰት። እነ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዷለም አራጌ ከዚህ የባስ ነገር አልተናገሩም። በፍትህ ስም የሚቀለድባቸው እነ ፕ/ር መረራ ጉዲና እና በቀለ ገርባ ይህችን ያህል እንኳን አልተነፈሱም። መቀሌ ላይ በዝግ ስብሰባ፣ አዲስ አበባ ላይ በዝግ ስብሰባ፣ ፓርላማውም በዝግ … [Read more...] about “አውሬውን አቁስለነዋል፤ ይህ ግን በቂ አይደለም” ለማ መገርሳ