
ወልድያ የበቀል ዱላ አትፎባታል። ግድያና አፈናው ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል። የወያኔ ቅልብ ጦር የጅምላ ግድያውን የፈጸመው ከዚህ ቀደም በወልድያ ስታድየም የተፈጠረውን ክስተት ለመበቀል መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።
ከልምድ እንዳየነው ህወሃት ሕዝብን መጨፍጨፍ ሲፈልግ – አጋዚ ወታደሮቹን ሕዝብ በሚሰበሰብበት ስፍራ ያሰማራና በመተንኮስ እንዲነሳሱ ያደርጋል። ብሶቱ ከቅጥ ያለፈበት ሕዝብ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር ህወሃት የበቀል ስራውን ይሰራል። ከዓመት በፊት የእሬቻ በዓል ላይ የሆነው ይኸው ነበር። በወልድያው ጭፍጨፋም ያየነው ይህንኑ ነው።
የቴዲ አፍሮ የባህርዳር ኮንሰርት ላይ አጋዚ ቢኖር ኖሮ እልቂቱ አይቀሬ ነበር። የዘንድሮው እሬቻ በዓል ከአጋዚ ነጻ ቢሆን እንደ አምናው ወገን ይገደል ነበር።
እለተ ቅዳሜ፣ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. የጥምቀት በዓልን ለማክበር የታደመ ሕዝብ ላይ የጥይት ናዳ ወርዷል። የደብረጺዮን ታዛዦች በታቦት ፊት የንፁሀንን ደም አፍስሰው ህዝቡን በደም አጥምቀውታል። ይህ ግድያ በእጅጉ ከልክ ያለፈ፣ ፍጹም አረመኔያዊ ድርጊት ነው።
እርግጥ በአስተሳሳባቸው ገና ከጫካ ያልወጡ ጉዶች ለሰው ልጅ ክብር ሊኖራቸው አይችልም። ታቦት ስር ገብቶ ደም ማፍሰስ ግን እምነትንም፣ ፈጣሪንም መድፈር ይሆናል። ከሰው የተፈጠሩ ቢሆኑ ኖሮ፣ ችግር እንኳን ቢፈጠር ታቦቱ በክብር እስኪገባ ጠብቀው መግደል ይችሉ ነበር። እንዲህ አይነቱ ንቀት በቀይ ሽብር ግዜም የተከሰተ አይመስለኝም። እርግጠኛ ልንሆን የምንችለው ይህ ነገር እንደሌሎቹ ግድያዎች አሻራ ጥሎ ብቻ የሚያልፍ አለመሆኑን ነው።
ለሰሩት ሁሉ ይከፍሉበታል! ለዚህም ይመስላል ይህ ግድያ፣ ይህ ጭካኔ፣ ይህ ግፍ ዝም ሊባል አይገባም ሲል ሕዝብ ያመረረው። “የሞተ አህያ ጅብ አይፈራም” እንዲሉ በቁም የገደሉት ሕዝብ ተቃውሞውን ዛሬም ቀጥሏል። አውራ መንገዶችን እየዘጋ፣ የህወሃት የሆነውን ንብረት እያወደመ አመጹን ቀጥሎበታል።
አነጣጥረው የሚተኩሱ የወያኔ-አጋዚ ወታደሮች በወልድያ ቀድመው በመግባት አመቺ የሆነ ስፍራ ይዘው እንደነበር እማኞች ይናገራሉ። ላለፉት ሁለት አመታት በነበረው አመጽ የወሎ ዝምታ ስርዓቱን ስጋት ውስጥ ከትቶት እንደነበርም ግልጽ ነው። ወሎ የፍቅር ሕዝብ ነው። ፍቅርን ጥግ እንደሚተገብር ሁሉ ሲደፍሩት ደግሞ የጭካኔ ጫፍንም ያውቅበታል።
የወሎ ዝምታ ስርአቱን በእጅጉ አስፈርቶት ነበር። ወያኔ በእንዲህ አይነቱ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ሽብር ፈጥሮ፣ ዝምታውን መስበር የተጠቀመበት ታክቲክ ሊሆን ይችላል። ዝምታውን ለመስበር ሲል በዚህ መልኩ የንጹሃንን ደም ማፍሰሱን እንደ መፍትሄ መውሰዱ ግን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው የተረዳው አሁን ነው። ባይተዋር ታጣቂዎች ከበዓሉ በፊት ወደ ወልድያ መግባታቸው ግድያው ታስቦበት እና ተጠንቶበት መሆኑን ያስረግጥልናል።
በወሎ ውስጥ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው። በደሴ፣ በወልዲያ እና በኮምቦልቻ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የወያኔ-አጋዚን የግድያ ወንጀል እንዲያወግዝ የሚደረገው ቅስቀሳ ቀጥሏል። በበርካታ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ እና ደም ማፍሰስ ወንጀል ተፈጽሞ መላቀቅ እንደማይኖር ሕዝቡ እየተናገረ ነው።
ዜናው ሁሉ የግድያ ሆነና ሕዝቡም አለምዓቀፉ ህብረተሰቡም ለመደው። ከትላን በስትያ ዜጎች ተገደሉ፣ ትናንትናም ዜጎች ተገደሉ፣ ዛሬም ተገደሉ፣ … ዜጎች እንደዋዛ ይገደላሉ፣ ወገን እንደ ዛፍ ግንድ ይጨፈጨፋል፣ ሕዝብ ይሰማል፣ ሕዝብ ይጮሃል፣ ከዚያም ይረሳዋል። የአጋዚ ሃይሎችም ባሰኛቸው ግዜ ዜጋውን እየተኮሱ የሚገድሉት፣ ይህ ሕዝብ ዛሬ ይጮህና ነገ ይረሰዋል በሚል እሳቤ ይመስላል።
ለቅሶ እና ቀብር ላይ ሰው የሚገደልበት ሃገር፣ በቤተ መቅደስ እና በመስጊድ ህይወት የሚጠፋበት ሃገር፣ በእግር ኳስ ጨዋታ ደጋፊዎች የሚተኮስባቸው ሃገር… ሌላው ቀርቶ ኮንሰርት ማዘጋጀት ብርቅ የሆነበት ሃገር… ባጠቃላይ የመኖር ዋስትና የሌለበት ሃገር! ይህ እንዴትስ ሆኖ ሊለመድ ቻለ?
ማማው ላይ ያወጣቸው፣ ይህንን ሕዝብ ንቀውታል። አስተሳሰባቸው አሁንም ከጫካ ላልወጣ እነዚህ ድኩማን ንፁሃንን መግደል የችግሮቻቸው መፍትሄ አድርገው ነው የሚወስዱት። ይህ አካሄዳቸው ግን እንደማይቀጥል ቄሮ እና ፋኖ በሚገባቸው ቋንቋ እየነገራቸው ይገኛል። በወልድያም ደም ፈስሶ እንቅልፍ እንደሌለ እነሆ እያሳየን ነው።
ትእቢት ውድቀትን ትቀድማለች!
በቀጣዩ ጽሁፌ ስለ ቴዲ አፍሮ የባህርዳርና ቀጣይ ኮንሰርት ከመጀመርያ ምንጭ ያገኘሁትን አስደማሚ መረጃ ጀባ እላለሁ።
ክንፉ አሰፋ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ በታቦት ፊት የህዝባችን ደም ማፍሰስ ብቻ ሳይሆን ታቦትም የሚሰርቅ ድርጅት ነው። ህዝባችንን አንድ የሚያደርገውን ነገር ማፍረስና ጥላቻና ቂምን በህዝባችን ለዘመናት የሚዘራው ይህ ጠባብ ቡድን ከአፍንጫው አርቆ ማሰብ አይችልም። የሃገሬ ሰው ሞኝ ነው። ወያኔ ማለት ያለፈ ቂምን ቆጥሮ የሚበቀል በዘር የተለከፈ ድርጅት መሆኑ ላፍታም ሆነ ወገኖቼ ሲዘነጉት ይገርመኛል። ለምሳሌ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አ. አበባ ላይ ከትግራዮ አቻቸው ባደረጉት የኳስ ግጥሚያ ወያኔ በቀሉን ሳይረሳ በመቶ የሚቆጠሩ የፋሲል ደጋፊዎችን አጋፎ እስር እንደከተተ የአይን እማኞች በሰሙኑ ዘግበዋል። ያው ቂመኛው ወያኔ በወልዲያ ከተማ በታቦት ፊት በመኪና ላይ በተጠመደ መትረጌስ የፈጀው በቂም በቀልነት ነው። ይህም ባለፈው ከተናኩሶበት የኳስ ግጭትና ከዘረኝነት የመነጨ ነው።
የትግራይን ህዝብ አፍኖ ለዘመናት ለራሱ ጥቅም የሚገለገልበት ይህ አጥፊ ድርጅት በምንም መልኩ ቢሆን ራሱን ማደስም መለወጥም አይችልም። ለምሳሌ የትግራይ መስተዳድር ሃላፊና የወያኔ ሃርነት ትግራይ የቡድን መሪ የነበሩትን አቶ አባይ ወልድን በማውረድ በዶ/ር ደብረጽዮን የተካው ይህ እቡይ ድርጅት ጎልቻ ለዋጭ እንጂ ስለ ወጡ መጣፈጥ ደንታ አይሰጠውም። ይህም በመሆኑ አቶ አባይ ወልድን በሚስታቸው አሳቦ ወደ አውስትራሊያ አምባሳደር በማድረግ እንደላካቸው ወያኔ አፍቃሪ ያልሆኑ ድርኸ – ገጾች ዘግበዋል። የሻቢያው መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ በቅርቡ በራሳቸው የዜና ማሰራጫ ላይ ቀርበው ባራገቡት ሃሳብ እንዲህ ብለዋል። “የኢትዮጵያ ችግር አንቀጽ 39 (መገንጠልን የሚፈቅደው) ድንጋጌና ወያኔ ነው ብለውናል። ይህ አባባል እውነትነት አለው። ግን በግልባጩ ተጨፈኑና ላሞኛቹሁ የሚልም ነው። የኤርትራው የእድሜ ልክ መሪ ለኢትዮጵያ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሲሰጡ አንቀጽ 39 ተደግፈው አልነበረንም? እኛ ስንናከስ ኤርትራ የአፍሪካ ታይዋን ልትሆን? የተዋጋነው ለኤርትራ ነጻነትና ልዕልና ነው ያለው ሻቢያ ዜሬ ሃገሩን የዓረቦች መናህሪያ ሲያደርገው እውነቱን አይተው ለሚረዱ ምን ያህል የህሊና ጉዳት እንዳለው መገመት አይከብድም። ይታያቹሁ ሻቢያ የተራዶ ድርጅቶች በምጽዋና በአሰብ ለተራቡ ኢትዮጵያዊን ምግብ እናስገባ ተብሎ ሲጠየቅ አይሆንም ያለ ድርጅት ነው። ድሮም የአረብ ሽርከኛ ዛሬም የአረብ ምርኮኞ ነጻነቱ የቱ ላይ ነው? የራስን ጠልቶ ለአረብ ማጎብደድ! ያ ነጻነት በአፍንጫየ ይውጣ!!
በአኳያው በተዘረፈ ሃብትና ንብረት ቤታቸውና ሆዳቸው ያለ ልክ የሞላው የመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ለባህርዳር ደጋፊዎችና ተጫዋቾች በመቀሌ ከተማ ያደረጉላቸው አቀባበል በድላ፤ በእስራትና በስድብ የታጀበ ነው። እጠቅሳለሁ “ገና መቶ ዓመት እንገዛለን”። በቁጥር ሂሳብ ሻቢያና ወያኔ አንድ ናቸው። መቶ ዓመት የእነርሱ የዘመን መዝጊያ ነው። የጠባብ ብሄርተኞች በሽታ መድሃኒት የለውምና!
አሁን እንሆ ወያኔ እስረኛ እፈታለሁ/ፈትቻለሁ፤ እታደሳለሁ/ታድሻለሁ የሚለው ለጊዜው ከገባበት አጣቢቂኝ ለመውጣትና በየተራ ለአንድነትና ለህብረት የቆሙ ወገኖችን ጉድጓድ ለመክተት የጊዜ መግዣ ብልሃት እንጂ በምንም ታአምር ወያኔ ራሱን ለውጦ ህብር ለሆነ ህዝብ ይቆማል ብሎ መጠበቅ ራስን ማጃጃል ነው። ስለሆነም ከሻቢያም ሆነ ከወያኔ እንጆሪ ይገኛል ብሎ የሚጠብቅ እይታው የተወላገደ የጊዜው ፍርፋሪ ለቃሚና ተለጣፊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ያለፈ ታሪካቸውም ሆነ አሁን የምናየው ፍሬያቸው ኩርንችና እሾህ ነው።
ሰዎች!!! መቼም ነገርን ነገር ያነሳውና፣ ጨዋታው ይደምቃል፣ወይም ይመራል። ህዝባችን ትግል ውስጥ፣ ህዝባዊ ወያን የተጫወተችው ገድል የሚናቅ ኣይደለም። ግንባሯን ለጥይት በረሃን ለጥሜት፣ ችግርን ያለስሜት፣ ብሎም በስደት፣ ወይም በሞት ተፈትና ብቅ ያለች እንጂ እንደ ደርግ ስልጣን ባቋራጭ ይዛ ያረበረበች ድርጅት ኣይደለችም። ሜዳ የተለደች ትግል የወለዳት ታግላ ያታገለች ናት። ከሜዳውም ስለ ነበርንበት ታዝበን ነው የወጣነው። ኣሁን እንዲህ ተጣልተው ማየት ሆነብን እንጂ ህዝባዊ ወያን ታሪክ በኤርትራ በረሃ ኣስመዝግባለች። ኣንዳንዴ የሻቢያን ድርሻ ደርግን መክታ የሸኘችበት ጊዜ ይታወሰኛል። ድንቅ ስራዎቿ ከፊቴ ይነበባል!!! ሃቅ ስለሆነ ልክደው ኣልችልም!!! እስቲ ማነው ለሌላው ግንባሩን ለጥይት የሚሰጥ?? ወያንን በዚህ ታዝቢያት ወጥቻለሁ። እሳት ውስጥ ተማግዳ ይህን ትውልድ ለብቃት ጋብዛዋለች!! ሆድ እኮ ፋታ ኣይሰጠንም ነበር!! ጥሜት እኮ ለሳምንታት ኣያቆየንም!! ሰው ነበር የሚሞተው!! በነሱ መቃብር ላይ በብቃት ቀርበን ድግስ እየላፍን ነው!!! ለማለት የፈለኩት የግሉ ተዋናይ ነበረች!!! ያውም ሻቢያን እያገዘች!!! እሳት ውስጥ ትገባ ነበር!!! ሳህል በረሃ ውስጥ ነበርኩ። ታዝቤ የወጣሁት ነገር ቢኖር፣ ይህን ነበር!!! ለብቃት፣በብቃት ጋብዛናለች!!! ዘላለማዊ ስም ለተሰዉልን ሰማዕታት!!!
አቶ ሙሉጌታ – ሰለ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተጋድሎ የአንተ ምስከርነት አያሻም። ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቀዋል። ወያኔ በጫካና በገደል ሲዋጋ አንተ የት ነበርክ? ወስላታ! የጊዜው ጥቅም አይንህን ያሳወረህ እንዳንተ ያለ ሌባ ነው የሃገራችንን ሰቆቃ ያራዘመው። ማንም ቢሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያለፈበትን የትግል ዘመንና የተከፈለውን መስዋእትነት ዓሊ የሚል የለም። መታገል ሌላ ማስተዳደር ሌላ። የትግራይ ልጆች ደማቸውን ያፈሰሱት ጥቂቶች የሚፈነጩባት እልፍ የሚያለቅስባት ሃገር ለመፍጠር ከሆነ እንኳን ደስ አለህ። አንድ ነገር ይገርመኛል። ፓለቲከኞች ልበ ቢሶች ናቸው። ከዘመናት በፊት ያለፈ ድርጊትን እያስታወሱ ታምቡር በመምታት የዛሬውን እውነት ለማዳፈን ይከጅላል። ወያኔ የተዋጋው ከወንድሙ፤ ከእህቱ ጋር ነው። ባህር አቋርጦ የመጣ ጠላትን አልመከተም። የእርስ በርስ እልቂት ቡራ ከረዮ አያሰኝም። ያረጀ ያፈጀ ያለቀለት የበረሃ ታሪክ ታላንት እንደሆነ ሁሌ ሲደገም አይኖርም።
በናቅፋም ሆነ በተለያዪ የሃገራችን ክፍሎች በትግል የተሰውትን ሰማእታት ማክበር ከተፈለገ ለህዝባችን የመጻፍ/የመናገር/የመሰብሰብ/መሪዎችን የመምረጥ ነጻነት ሊኖር ይገባል። ያ ግን ህልም ነው በወያኔዋ ኢትዮጵያ። ያለፈ ጊዜ የወያኔን ውዳሴ እንደደገምክ ማጥ ውስጥ እንደገባ ተሽከርካሪ ስትዳክር ትኖራለህ። ዛሬ ትላንትን መሆን አይችልም። በዛሬ ላይ ሆነህ እውነቱን ተመልከት!
አቶ ሙሉጌታ አንዳርጌ ሰላም ኖት?
ስለ ውያኔ ቆራጥነት ጀግንነት በዉሃ ጥም ሆነ በረሃብ አይበገሬነት ወዘተ አወጉን መልካም ነበርኩበትም ብለዋል ለመመስከር – ይሁን። መቼስ ማል ጎደኒ ብለን ሁሉን ያሉትን ያለጥያቄ ወይ አለአስተያየት አንደማንቀበል የውቃሉ ምንም እንኳን ‘አብዮታዊ ዴሞክራሲ’ የተባለን ሁሉ ተቀበሉ ግርፍ ቢሆኑም። ለሳምንትም ለወርም ተወያይ ተከራከር መጨረሻው ግን ይተነገረህን ተቀበል ነው። አብዮታዊም ዴሞክራቲክ ያለመሆኑ አንዱ ምልክት። ወደ ዋናው ጉዳይ እንለፍ እስቲ።
1) ወያን – አዲስ ናት? ወያኔ ቀረ? – የተዋጋችው ውሃ የተጠማችው ሊሎችስ አላዳረጉትም? የተዋጋችሁት ሠራዊት እራሱ – የደርግ የምትሉቱ – አልሞተም? ውሃ አልተጠማም? አካለ ጎዶሎ አልሆነም? ስለዚህ አቶ ሙሉጌታ ሰከን ይበሉ እንደው ካለኛ ጀግና ተራራ አንቀጥቃጭ ገለመሌ ይቁም። ጦር ሜዳ የነበረ ሁሉም ቀምሶታል። ሌላም ልጨምርሎት፡ ወያን አሥራሰባት ዓመት ተዋጋች የሚባለው የእምዬ ምንሊክ አሥራ ሰባት ሰዓት አልፈጀበትም ጥልያንን በታትኖ ስንት ጄኔነራል ሲማርክ – ተግባባን? ወያን የውሃ ጥሙን ብትችለውም የአንስታይ ፍቅሩ ግን ረታት – ሕጓንም ቀየረች ተራባችም! በተለይ አመራሯ!
2) ወያን እስከምናቃት እሷም የምትለው የትግራይ ነፃ አውጪ ናት። ይኸው ዓመታት አለፉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስትፈተፍት። ከላይኛው ነጥብ ጋር ይያያዛል – ተዋጋሁ ተቀነጠስኩ ማለት እኮ ሕዝብና አገርን እንደፈልጉ ረግጦ የመግዛት ፈቃድ ወይ ሊቼንሳ አይደለም። የሃገር ባለቤት ሕዝብ ነው። ራሳቸው በአስተሳሰብና በግብር ነፃ ያልወጡ ‘ነፃ አውጪዎች’ አይደሉም ባለቤቶቹ። እንደው ካለኛ ብላችሁ አትገግሙ። ግትርነትም ትምክሕትም ይተነፍሳል። እስቲ ታሪክና ምሣሌን እንይ – ከወያን በፊት ነው የተፃፈው
ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አንገት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንደባለሉ
3) ሻቢያስ ኤርትራን ገንጥዬ ነፃ አወጣለሁ ብሎ ነው፤ ወያን ምን ቤት ናት ጦር መድ ድረስ የምታሽቃብጠው? የሃገር ክህደት እኮ ነው ድርጊቱ። ሻቢያ ኢትዮጲያዊ አይደለንም ብሎ የኢትዮጲያን ሠራዊት ወጋ፤ እነወያንስ? ኢትዮጲያዊ አይደሉም? እንዴት ከሃገር ጠላት ያብራሉ? እንዳይካድ አሁንም ሻቢያ ያው ነው አቋሙ!
Milu gets Andargei,
What would the ‘cadres’ say now?
ሰዎች!! ያለፈን ታሪክ እንደ እውነት ኣጣፍጣችሁ ታቀርቡልናላችሁ። በህይወት ያለን ድርጅት ስም ማጉድፍ ግን ያለበቂ ዕውቀትና ጥላቻ እንጂ የምለው የለኝም!! ወያን ታግላ፣ተወርውራ ለኛ ብቃትን ኣውርሳናለች፣ ብቃትን የምንጠቀምበት እኛው ነን፣ ካልተጠቀምክበት እሷ መጥታ ኣታሽሞነሙንህም!!! ብቃትን ኣስመዝግባለች!! ብቃትህን ማሳየት ያንተ ፈንታ እንጂ ድርሻዋ ኣይደልም!!!
አቶ ሙሉጌታ አንዳርጌ ሰላም ኖት?
ስለ ውያኔ ቆራጥነት ጀግንነት በዉሃ ጥም ሆነ በረሃብ አይበገሬነት ወዘተ አወጉን መልካም ነበርኩበትም ብለዋል ለመመስከር – ይሁን። መቼስ ማል ጎደኒ ብለን ሁሉን ያሉትን ያለጥያቄ ወይ አለአስተያየት አንደማንቀበል የውቃሉ ምንም እንኳን ‘አብዮታዊ ዴሞክራሲ’ የተባለን ሁሉ ተቀበሉ ግርፍ ቢሆኑም። ለሳምንትም ለወርም ተወያይ ተከራከር መጨረሻው ግን ይተነገረህን ተቀበል ነው። አብዮታዊም ዴሞክራቲክ ያለመሆኑ አንዱ ምልክት። ወደ ዋናው ጉዳይ እንለፍ እስቲ።
1) ወያን – አዲስ ናት? ወያኔ ቀረ? – የተዋጋችው ውሃ የተጠማችው ሊሎችስ አላዳረጉትም? የተዋጋችሁት ሠራዊት እራሱ – የደርግ የምትሉቱ – አልሞተም? ውሃ አልተጠማም? አካለ ጎዶሎ አልሆነም? ስለዚህ አቶ ሙሉጌታ ሰከን ይበሉ እንደው ካለኛ ጀግና ተራራ አንቀጥቃጭ ገለመሌ ይቁም። ጦር ሜዳ የነበረ ሁሉም ቀምሶታል። ሌላም ልጨምርሎት፡ ወያን አሥራሰባት ዓመት ተዋጋች የሚባለው የእምዬ ምንሊክ አሥራ ሰባት ሰዓት አልፈጀበትም ጥልያንን በታትኖ ስንት ጄኔነራል ሲማርክ – ተግባባን? ወያን የውሃ ጥሙን ብትችለውም የአንስታይ ፍቅሩ ግን ረታት – ሕጓንም ቀየረች ተራባችም! በተለይ አመራሯ!
2) ወያን እስከምናቃት እሷም የምትለው የትግራይ ነፃ አውጪ ናት። ይኸው ዓመታት አለፉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስትፈተፍት። ከላይኛው ነጥብ ጋር ይያያዛል – ተዋጋሁ ተቀነጠስኩ ማለት እኮ ሕዝብና አገርን እንደፈልጉ ረግጦ የመግዛት ፈቃድ ወይ ሊቼንሳ አይደለም። የሃገር ባለቤት ሕዝብ ነው። ራሳቸው በአስተሳሰብና በግብር ነፃ ያልወጡ ‘ነፃ አውጪዎች’ አይደሉም ባለቤቶቹ። እንደው ካለኛ ብላችሁ አትገግሙ። ግትርነትም ትምክሕትም ይተነፍሳል። እስቲ ታሪክና ምሣሌን እንይ – ከወያን በፊት ነው የተፃፈው
ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አንገት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንደባለሉ
3) ሻቢያስ ኤርትራን ገንጥዬ ነፃ አወጣለሁ ብሎ ነው፤ ወያን ምን ቤት ናት ጦር መድ ድረስ የምታሽቃብጠው? የሃገር ክህደት እኮ ነው ድርጊቱ። ሻቢያ ኢትዮጲያዊ አይደለንም ብሎ የኢትዮጲያን ሠራዊት ወጋ፤ እነወያንስ? ኢትዮጲያዊ አይደሉም? እንዴት ከሃገር ጠላት ያብራሉ? እንዳይካድ አሁንም ሻቢያ ያው ነው አቋሙ!
ጌታዬ!! ለዚህ መልስ የለኝም!!