“ባለፉት 50 ዓመታት የተከሰቱት ጦርነቶች የተጀመሩት ሚዲያው ባስተጋባው ውሸት መሆኑን ደርሼበታለሁ” ጁሊያን አሳንዥ፤ የዊኪሊክስ መሥራች። የአገራችን ሚዲያ አውታሮች በተለይም የግሉ ሚዲያ የሚባሉትና በ1997 ምርጫ ወቅት የነበሩት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲቀጭጭ፣ የሃሳብ ልዩነት እንዳያድግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ጉያ ሥር ገብተው የፈጸሙት ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው። ለቀጣዩ ትውልድ መማሪያ ይሆን ዘንድ በወጉ ተጠንቶና ተሰንዶ ሊቀመጥ ይገባል። ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲከሰት ያየነው ፖለቲካው ወይም ፓርቲዎች ሚዲያውን አጀንዳ እያስያዙ ሲመሩት ይቆዩና በኋላ ፖለቲከኞቹ እርስበርስ ሽኩቻ ውስጥ ሲወድቁ የሚፈልጉትን ለማጥቃት ወይም በሐሰት ለመወንጀልና ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ሲሉ ለሚዲያ ባለቤቶቹ ባሪያና ተገዢ በመሆን እነርሱ ሚዲያውን መምራት ሲገባቸው … [Read more...] about ቀጣዩ የዳያስፖራ ፖለቲካና የሚዲያው አሰላለፍ
Archives for February 2024
የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ማረጋገጫ ሰጠ
* በ“ጋዜጠኛነት” ስም የሚፈጸመው የሚዲያ ሸፍጥ በትግራይ ክልል "ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ጀምረዋል" በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት "ከእውነት የራቀ ነው" ሲሉ የከሰሱት የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ 212 ኢንዱስትሪዎች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ሥራ እንዲጀመሩ ክስ ባቀረቡበት ዜና ጎን ለጎን አስታወቁ። ዜናው የክስ ሳይሆን አሃዱና ቲክቫህ በቅብብሎሽ አንዱ ሌላውን ዋቢ አድርገው ባሰራጩት ዜና መግቢያና ርዕስ ቀዳሚ ያደረጉት "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓርላማ ያቀረቡት ሪፖርት ከዕውነት የራቀ ነው" በሚል ነው። ዜናው በመሪ ርዕሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የቀረበውን ክስ አላብራራም፣ እርሳቸው ካሉት ጋርም አላነጻጸረም። የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረሚካኤል "በአሁኑ ወቅት በክልሉ ሥራ የጀመሩት ለትላልቅ … [Read more...] about የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ማረጋገጫ ሰጠ
ስለ ዓድዋ ሙዚየም ዋና አርኪቴክቱ ምን ይላል?
በአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ፤ የሚኒሊክ ሀውልት እና የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያዋስኑት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። በቅርቡ ከታደሰው እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ማዘጋጃ ቤት ጋር ደግሞ በድልድይ ተገናኝቷል። እስከ ዛሬ ድረስ የራሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይኖረው የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም ቋሚ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚያገኘው በዚህ ፕሮጀክት ነው። እየተጠናቀቀ ያለው ይህ ፕሮጀክት ሁለት ሺህ ሰዎችን የሚይዝ የከተማ አዳራሽም በውስጡ ይዟል። ከሁሉም በላይ ግን የዓድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት ግዙፍነት የሚነሳው ሊዘክረው ካሰበው ታሪካዊ ሁነት ነው። ይህ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክት፤ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በተለየ የኢትዮጵያን ነጻነት ያስጠበቀው እና በተለያዩ አገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴን ያነሳሳው የዓድዋ ድል መታሰቢያ … [Read more...] about ስለ ዓድዋ ሙዚየም ዋና አርኪቴክቱ ምን ይላል?
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይመረቃል
ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረጓት አባቶቻችንን የሚዘክር የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ፒያሳ ተገንብቶ ዛሬ ይመረቃል። መታሰቢያው የተገነባው ጀግኖች ወደ ጦርነቱ ሲተሙ በአንድነት ተሰባስበው ጉዟቸውን የጀመሩበት ቦታ ላይ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ላይ የሚታየው 00 ኪሎ ሜትር መነሻ ቦታ የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። አጠቃላይ ከታች እስከ ላይ በ5ቱ ወለል ላይ ያለዉ መሬት ስፋት 12 ሄክታር ነው። ሙዚየሙ ከምድር በታች ያለውን ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለሎች አሉት። ከ1 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ፣ ሲሲቲቪ ካሜራ፣የራሱ መቆጣጠሪያ ያለው ስማርት ፓርኪን ሥርዓት … [Read more...] about የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይመረቃል
37 ቢሊዮን ብር የት ገባ? “ትግራይ ውስጥ አዲስ አጀንዳ ተተከለ”
ትግራይን ማቃናት ያቃተው ካድሬ - አቅቶሃል ተባለ “ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ብር ለትግራይ አስተዳደር መሰጠቱን ስንሰማ ደንገጠናል። ዜናውን የሰሙ ሁሉ ብሩ የት ገባ? የሚል ጉምጉምታ እያሰሙ ነው። አካል ጉዳተኞች ጸጉራቸውን እየነጩ ነው። ጉዳዩን ትግራይ ያሉ ፖለቲከኞችም እየመከሩበት ነው። ሕዝብ ተናድዷል” ስትል ተቀማጭነቷ አዲስ አበባ የሆነ የትግራይ ተወላጅ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ ነግራዋለች። ወጣቷ በጦርነቱ አንድ ወንድሟን አጥታለች። ኮምቦልቻ እስከሚደርስ በሕይወት ስለመኖሩ መረጃ እንደነበራት፣ ከዚያ በኋላ ደብዛው ጠፍቶባት መጨረሻ ላይ እናቷ መርዶ እንደተነገራቸው የምትናገረዋ ወጣት፣ ስለ ትሕነግ (የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ስትናገር ያንዘዘርታል። ኃላፊዎቹን ስታያቸው ያማታል። ኃፍረትና ጸጸት የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው መሆናቸውን ስታስብ... “ትግራይን … [Read more...] about 37 ቢሊዮን ብር የት ገባ? “ትግራይ ውስጥ አዲስ አጀንዳ ተተከለ”
አወዛጋቢው የአቡነ ጴጥሮስ የጉዞ ሰነድ
የአሜሪካንን ዜግነት ለመውሰድ ቀኝ እጅን ወደ ላይ ቀስሮ መማል ግድ ነው። እከሌ ከገሌ ሳይባል “ቀደም ሲል የነበረኝን ዜግነት እክዳለሁ” በማለት የሚከናወነው ምህላ “እግዚአብሔር ይርዳኝ” በሚል ማሳረጊያ ይቋጫል። “ቀደም ሲል የነበረኝን ዜግነቴን፣ የማንኛውንም የልዑል፣ የግዛት፣ የአገር፣ ወይም የሉዓላዊ መንግሥት ተገዢነቴን በሙሉና በፍጹም መካዴን በምሕላ አውጃለሁ" በሚል የሚከናወነው የመሐላ አሰጣጥ፣ ምሕላውን በፍጹምና ያለምንም ማወላዳት መቅበልን የሚጠይቅ ሲሆን ይህንንም ቀኝ እጅ በማውጣት የሚከናወን ሥርዓት ነው። Oath"I hereby declare, on oath, that I absolutely and entirely renounce and abjure all allegiance and fidelity to any foreign prince, potentate, state, or … [Read more...] about አወዛጋቢው የአቡነ ጴጥሮስ የጉዞ ሰነድ
ትህነግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂደውን ሽብር እንደሚቀጥል አስታወቀ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትሕነግ) በማለት ራሱን የሚጠራው ቡድን በዓለምአቀፉ የአሸባሪ ቋት ተመዝግቦ የሚገኘው የወንበዴዎች ስብስብ ነው። ከስድሳ ቀናት በላይ ስብሰባ ተቀምጦ የነበረው ትህነግ የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሚገባው አልተተገበረም በሚል በመንግሥት ላይ የተቃውሞ መግለጫ አውጥቶ ነበር። በቀጣይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በጥር 23 ቀን 2016 ዓም ለትሕነግ መግለጫ አጸፋ ምላሽ የሰጠ ሲሆን በዋነኝነት ስምምነቱን ለመተግበር መንግሥት እንዴት ከሚገባው በላይ ርቀት እንደሄደ የጠቆመ ነበር። እንደ ማሳያም ከስምምነቱ ወዲህ መንግሥት ለትግራይ ክልል ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገልጾዋል። ለዚህ የመንግሥት ምላሽ ትሕነግ የአጸፋ ምላሽ ሰኞ የሰጠ ሲሆን ለክልሉ የተደረገውን 37 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ምንም ዓይነት ዕውቅና ሳይሰጥ የፕሪቶሪያው … [Read more...] about ትህነግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂደውን ሽብር እንደሚቀጥል አስታወቀ