የአብን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ዩሱፍ ኢብራሒምና አቶ ጋሻው መርሻ በዛሬው ዕለት ከአማራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኅልውና ዘመቻውን እና ቀጣይ የትህነግን አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተዋል። የአብን አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በቅድሚያ በዚሁ ቃለምልልስ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ወራሪውን የትግራይ ኃይል “የትግሬ ወራሪ ኃይል በማለት” በትክክለኛ ስሙ መጥራቱን አመስግነዋል። እንደ ምክንያትም አድርገው ያቀረቡት አንድን ቡድን በተገቢውና ትክክለኛ ስም በመስጠት መሰየም ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አውስተዋል። ከዚህ በማስከተል ለደረሰው ነገር ሁሉ በኃላፊነት የሚጠየቀው ማነው ለሚለው ጥያቄ አቶ ጋሻው ሲመልሱ ትህነግ መሆን በመጠቆም ለማካካሻም የትህነግ ዋና የገቢ ምንጭ የሆነውና የአክሱምን ባንክ በመዝረፍ ተቋቁሞ ከአፍሪካ ትልቁ … [Read more...] about “ካሁን በኋላ ወደ ሥርዓትና ወደ ፍትሕ የማይመጡ ከሆነ ትግራይን ስለመገንጠል ነው መወራት ያለበት” አቶ ዩሱፍ የአብን ምክትል ሊቀመንበር
Archives for December 2021
አበበ በለው በአማራ ሚዲያ? እንዴት ሆኖ?!
እንደ አገርም፣ እንደ ሕዝብም የገባንበትን የችግር ማዕበል በቅጡ የመረዳት ችግር እንዳለ የሚያመላክቱ ጉዳዮች አሉ። እነዚህን ጉዳዮች ባስቸኳይ ካላቆምን ውርደት በግል፣ በቤተሰብ፣ በቀዬና በአገር ደረጃ በደጅ ቆሞ እየጠበቀን ነውና “ግባ በለው” የማለት ያህል ይሆንብናል። ይህ ከሆነ ደግሞ ዕድሜ ልክ ቀና ማለት አይቻልም። እንግሊዞች ተንበርክከው እንደ ከብት ሳር እንደጋጡት እንኳን ዕድል የሚሰጥ የለም። ኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር ተነስታ፣ ልጆቿ አንድ ሆነው፣ የቻለ ህይወቱን፣ ያላቻለ በደጀን ተጋምዶ በከፈሉት ዋጋ ዛሬ የተገኘው ድል ተመዝግቧል። ከትግሬ ወራሪ ኃይል ነጻ በወጡ አካባቢዎች እንደታየው ዓላማው አገሪቱን መዘረፍ፣ ቀሪውን ማውደምና ወደ ዓመድነት መቀየር ነው። ይህ በዓይን ብረታችን ያየነው እውነት በመሆኑ ማስተባበያ አይቀርብበትም። ይልቁኑም ትምህርት ቤት፣ ክሊኒክና … [Read more...] about አበበ በለው በአማራ ሚዲያ? እንዴት ሆኖ?!
የኢትዮጵያ ከአጎዋ መሰረዝ የአሜሪካ ኩባንያዎችንም አሳስቧል
አሜሪካ የአፍሪካ አገራት የተለያዩ ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነፃ ወደ ግዛቷ እንዲያስገቡ ከሚፈቅደው የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት ኢትዮጵያን ለመሰረዝ መወሰኗ በአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ኢንዱስትሪዎች ላይ ድንጋጤ ፈጥሯል ተባለ። የአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ማኅበር (AAFA) የቦርድ ሰብሳቢ፣ ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ያገለገሉት ሪክ ሄልፌንቤይን ፎርብስ መጽሄት ላይ እንደፃፉት ውሳኔው ትልቅ ስህተት ነው ብለውታዋል። ውሳኔው ማንም ያለጠበቀውና የአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ኢንዱስትሪዎች በአፍሪካ ያደረጉትን ኢንቨስትመንት ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ አጎዋን የአገራትን ለመጫን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመችበት መሆኗን ነው ሄልፌንቤይን በጽሁፋቸው የገለጹት። ይህ ደግሞ ፍጹም ስህተት ነው ሲሉም አካሄዱን እንደተቃወሙት ነው ኢዜአ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ከአጎዋ መሰረዝ የአሜሪካ ኩባንያዎችንም አሳስቧል
“ይቺን ባንዲራ ሕይወታችሁ እስካለ ጠብቋት” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
ሙሉ በሙሉ ሸዋ፣ የኬሚሴ እንዲሁም ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ የደቡብ ወሎ ዞን አካባቢዎች ነፃ መውጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍም ድሉ ቀጣይ መሆኑን አሳውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰራው ጠንካራ ሥራ ጠላት የዘረፈውን አራፎግና ተበታትኖ ነው የወጣው ሆኖም የጠላት ኃይልን እየተከተልን እየደመሰስነው ነው ብለዋል። እየከፈልን ያለነው መስዋዕትነት ልንደፍር ልንሰርቅና ሌሎች ወንጀሎችን ልንፈፅም ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማዳን ነው ብለዋል። አሁን ላይ አብዛኛው የአማራ ክልልና የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ድሉ ይቀጥላል እናንተም ታሸንፋላችሁ ሲሉ የወገን ጦርን አብስረዋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ለአንዲት ተወካይ እንስት ኮማንዶ በመሸለም እንዲህ አሉ፤ … [Read more...] about “ይቺን ባንዲራ ሕይወታችሁ እስካለ ጠብቋት” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
ሸዋሮቢት ከተማ በአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!
"መግደልም መድፈርም መብታችን ነው" – “ተገድደነው የዘመትነው” የሚሉት የትህነግ ታጣቂዎች ዕድሜያቸው 50ዎቹን ያለፈው የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዋ አዛውንት በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በቡድን ከተደፈሩ በኋላ ራሳቸውን አጥፍተዋል። ፖሊስና የአካባቢው የዓይን እማኞች በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደገለጹት፤ ዕድሜያቸው 50ዎቹን የተሻገረውና የሸዋሮቢት ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ የነበሩት ወይዘሮ ሞሚና አህመድ (ስማቸው የተቀየረ) በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በመደፈራቸው የልጄን ዓይን ከማይ ብለው ራሳቸውን አጥፍተዋል። ወ/ሮ ሞሚና የማገዶ እንጨት በመሸጥና እንጀራ በመጋገር የሚተዳደሩ ሲሆን፤ የ15 ዓመት ታዳጊ ልጅ እንዳላቸው የሸዋሮቢት ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ለኢፕድ ገልጸዋል። ዛሬ ትህነግን … [Read more...] about ሸዋሮቢት ከተማ በአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!
ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”
መውጫው እንደመግቢያው ቀላል አልሆነም። በትግሬ ልሂቃን እብደት፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ላይ የእሳት ቀለበት ሰርተዋል። በእያንዳንዱ የትግሬ ጎጆ የመከራ ዜና፣ የመርዶ መልዕክት ገብቷል። በጦርነቱ እና ከጦርነቱ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች አራት መቶ ስድሳ ሺህ ትግሬዎች ረግፈዋል። ይህን እኔ ሳልሆን ያልኩት የሳልሳዊ ወያኔ (ሳወት) መሪ ተስፋ ኪሮስ ሳህለ ነው። ያለምንም ጥርጥር ጦርነቱ በሕዝባቸው ላይ የትውልድ ክፍተት ፈጥሯል። ምናልባትም አንድ ወንድ አምስት ሴቶችን እንዲያገባ በልዩ ሁኔታ የቤተሰብ ሕጉ ካልተሻሻለላቸው በስተቀር የትውልድ ክፍተቱን በቀላሉ አይሞሉትም። ወያኔ ራሱ በለኮሰው እሳት “እወክለዋለሁ” የሚለውን ሕዝብ የእሳት ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። ከዚህ ጦርነት የሚተርፍ ቢኖር እንኳ በርካታ የትግራይ ከተሞችና መንደሮች የአዛውንት እና የሕጻናት ስብስብ … [Read more...] about ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”
ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው
ባለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች ናቸው ተባለ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በወጣው መግለጫ 122,000 ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብሏል። ከእነዚህ የሀሰት መረጃ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አጀንሲው ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የህውሐት ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17,000 የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ ቡድን ተከፍተው ነበር ተብሏል።የኤጀንሲው የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ በቡድኑ በተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች … [Read more...] about ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው
የምስራቁና የምዕራቡ ድል በመሃል አገር ይደገማል
በምሥራቅና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄንን የተናገሩት በሦስተኛው ቁልፍ ግንባር ተገኝተው ከሠራዊቱ ጋር በመከሩበት ጊዜ ነው። ከሰሞኑ በሚሠሩ ኦፕሬሽኖች በወራሪው አሸባሪ የተያዙ ተጨማሪ ከተሞች ነጻ እንደሚወጡ የገለጡ ሲሆን ለወረራ የገባው አሸባሪ ምንም ነገር ይዞ እንዳይወጣ ሕዝቡ ተደራጅቶ ማስቀረት እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል። ጠላት ፈርሷል፤ ተበትኗል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ አሁን ጠላት ያለው አማራጭ የሰረቀውን አስረክቦ እጁን መስጠት ነው ብለዋል። የሰረቀውን አስረክቦ እጁን ከሰጠ ምርኮኞችን ተከባክቦ መያዝ የጀግና ባህላችን ነው ብለዋል። ከአሸባሪው ሕወሓት ነጻ በወጡ አካባቢዎች በአስቸኳይ መስተዳድሩን በቶሎ መልሶ ማቋቋም … [Read more...] about የምስራቁና የምዕራቡ ድል በመሃል አገር ይደገማል
“ከደሙ ንጹህ ነኝ” ሲነቃ – “የሽግግሩ አመራርና አሻጋሪ” ሲዶለት – ድራማው እንደ ወረደ
ማስታወሻ እንደ መጠቆሚያ - የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) በሚል ስያሜ ራሱን ጠርቶ ተመሥርቶ፣ በዚሁ ስም ከበረሃ ተነስቶ አገር የመራበትና የፈጸማቸው ተግባራት በሙሉ የቅርብ፣ በዚህ ትውልድ ላይ የተፈጸመ ነው። ያለ ነጋሪና መስካሪ ይህ ትውልድ በአይን ብረቱ ያያቸው፣ በጆሮው ያደመጣቸውና በጋራ ሲመክርባቸው የነበሩ ናቸው። አሁንም ጉዱ አላለቀም። እንደውም የአሁኑ “ተያይዘን እንጥፋ ወይም ልሳፈርባችሁና ልዝረፋችሁ” የሚል መፈክር ይዞ ዘጠና አምስት መቶኛ ሕዝብ በአምስት መቶኛ አጣፍቶ ለመንገስ አልሟል። ይህ ኃይል ዛሬ የሚያወራው፣ የሚሰብከውና የሚጫወተው ከዚህ ግብሩን በደንብ ከሚያውቀውና “በቃኝ” ብሎ ካፈናጠረው ትውልድ ጋር መሆኑን ይዘነጋል። በዚህ ከሥር እንዳለ በቀረበው የትርጉም መረጃ ኤፍሬም ይስሃቅ አምላካዊ ቅባ ቅዱስ የሚቀባው የሉሲፈር ሽል ብርሃነ፣ … [Read more...] about “ከደሙ ንጹህ ነኝ” ሲነቃ – “የሽግግሩ አመራርና አሻጋሪ” ሲዶለት – ድራማው እንደ ወረደ
መንግሥት ለመገልበጥ በኤፍሬም ይስሐቅ መሪነት የተሳተፉ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ
በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ሰብሳቢነት በተመራውና በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሕወሃት ለመደገፍ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በአሜሪካ ክገር ምርመራ ተካሂዶ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠይቋል። ህወሃትን ለመደገፍና በህዝብ የተመረጠን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ምርመራ እንዲካድባቸውና ክስ እንዲመሰረትባቸው የጠየቁት በአሜሪካ አገር ያሉ አራት የትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ናቸው። ብርሃኔ ገብረክርስቶስ፣ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ፣ ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን፣ በቀለ ገለታ፣ ዶ/ር ታደሰ ውሂብ ፣ ኩላሂ ጃለታ፣ ዶናልድ ይማማቶን ጨምሮ 14 ግለሰቦች ናቸው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ምርመራ ተደርጎባቸው ክስ እንዲመሰረትባቸው የተጠየቀባቸው። ግሰለቦቹ እንዲከሰሱ የሚጠይቀውን ማመልከቻ ድርጅቶቹ ለአሜሪካ ጠቅላይ … [Read more...] about መንግሥት ለመገልበጥ በኤፍሬም ይስሐቅ መሪነት የተሳተፉ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ