አሜሪካ የአፍሪካ አገራት የተለያዩ ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነፃ ወደ ግዛቷ እንዲያስገቡ ከሚፈቅደው የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት ኢትዮጵያን ለመሰረዝ መወሰኗ በአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ኢንዱስትሪዎች ላይ ድንጋጤ ፈጥሯል ተባለ። የአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ማኅበር (AAFA) የቦርድ ሰብሳቢ፣ ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ያገለገሉት ሪክ ሄልፌንቤይን ፎርብስ መጽሄት ላይ እንደፃፉት ውሳኔው ትልቅ ስህተት ነው ብለውታዋል። ውሳኔው ማንም ያለጠበቀውና የአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ኢንዱስትሪዎች በአፍሪካ ያደረጉትን ኢንቨስትመንት ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ አጎዋን የአገራትን ለመጫን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመችበት መሆኗን ነው ሄልፌንቤይን በጽሁፋቸው የገለጹት። ይህ ደግሞ ፍጹም ስህተት ነው ሲሉም አካሄዱን እንደተቃወሙት ነው ኢዜአ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ከአጎዋ መሰረዝ የአሜሪካ ኩባንያዎችንም አሳስቧል