የአብን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ዩሱፍ ኢብራሒምና አቶ ጋሻው መርሻ በዛሬው ዕለት ከአማራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኅልውና ዘመቻውን እና ቀጣይ የትህነግን አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተዋል።
የአብን አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በቅድሚያ በዚሁ ቃለምልልስ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ወራሪውን የትግራይ ኃይል “የትግሬ ወራሪ ኃይል በማለት” በትክክለኛ ስሙ መጥራቱን አመስግነዋል። እንደ ምክንያትም አድርገው ያቀረቡት አንድን ቡድን በተገቢውና ትክክለኛ ስም በመስጠት መሰየም ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አውስተዋል።
ከዚህ በማስከተል ለደረሰው ነገር ሁሉ በኃላፊነት የሚጠየቀው ማነው ለሚለው ጥያቄ አቶ ጋሻው ሲመልሱ ትህነግ መሆን በመጠቆም ለማካካሻም የትህነግ ዋና የገቢ ምንጭ የሆነውና የአክሱምን ባንክ በመዝረፍ ተቋቁሞ ከአፍሪካ ትልቁ ተቋም ነኝ የሚለውን ኤፈርትን ሸጦ በጦርነቱ ለወደሙ አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም እንዲውል ሃሳብ ሰጥተዋል።
በቃለምልልሱ ማብቂያ ላይ አቶ ዩሱፍ በዋነኛነት እንዲወሰድላቸው የሚፈልጉትን ሃሳብ በዚህ መልኩ ተናግረዋል፤ “የፖለቲካ ቅኝቱ ራሱ መቀየር አለበት፤ የፖለቲካ ቅኝቱ እኔ ሁሉንም ነገር ካልወሰደኩኝ ብቻ ሳይሆን አንተን ሁሉንም ነገር ካላሳጣሁህ አሸናፊ ልሆን አልችልም የሚል የተዛባ የፖለቲካ እሳቤ ስላለ ነው። ከዛሬው እንዲወሰድልኝ የምፈልገው እስከዛሬ ድረስ በአገራዊ ቅን እሳቤ፣ በማኅበራዊ ቅን እሳቤ፣ ብዙ ነገሮችን፣ በጎነትን፣ ታሪክን፣ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ታሳቢ በማድረግ ስንገለገልባቸው የነበሩ አገራዊ እሴቶችን ያጎደፈ ስብስብ ነው ያጋጠመን፤ ይህንን ወደ ሕግ ማዕቀፍ ማቅረብ እንዳለ ሆኖ ግን አንድ እርምጃ ወደፊት እየተራመድን ጉዳዩ በሚመጥነው ልክ ልንቆም እንደምንችል የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ፖለቲከኛው፣ ምሑራኑ፣ ውይይት እንዲጀምር እኔ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ምን ለማለት ነው ካሁን በኋላ ስለ ትግራይ መገንጠል ለስልሳ፣ ለሃምሳ ዓመት ስናወራ፣ ስንሰጋ ወገናዊነታችን፣ ማኅበራዊ ቁርኝታችን ሊናጋ ነው በሚል (ስጋት) ስንዋጅጅ፣ ስንባዝን ኖረናል። ይህ መቆም አለበት። ካሁን በኋላ ወደ ሥርዓትና ወደ ፍትሕ የማይመጡ ከሆነ ትግራይን ስለመገንጠል ነው መወራት ያለበት፤ ስለ ትግራይ መገንጠል አይደለም አሁን ልናወራ የሚገባን”።
ሙሉውን ቃለምልልስ ማዳመጥ ተገቢ ስለሆነ ለዚሁ እንዲረዳ ከዚህ በታች አስቀምጠነዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Dushanbe says
As a fascist entity in Ethiopia and the region, the TPLF-Tigray will be a source of instability and violence in Ethiopia. The fate of Tigray should be determined not only by Tigrayans alone but also involve all Ethiopians. Independent Tigray will not be a viable state because it is the most resource poor in the country. Nor can it be sustained by foreign aid. I think it is time to discuss the fate of Tigray if the region will remain under the TPLF. The task of removing the TPLF from power should be left to the Tigrayans themselves. Ethiopia should not continue to bleed because of Tigray and a limit should be set for the price Ethiopians pay.
Dushanbe says
The cleansing of Tigray of fascism should be based on the experiences and approaches of nazi Germany.