በአዲስ አበባ 1 ሺሕ 338 ሄክታር መሬት አሁንም በወረራ ተይዞ እንደሚገኝ አስተዳደሩ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በህገወጥ መሬት ወረራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ ካሉ 121 ወረዳዎች ውስጥ በ88ቱ የመሬት ወረራ ተፈጽሟል። በአጠቃላይ በከተማዋ 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት የተወረረ ሲሆን በተደረገው የህንጻ ቆጠራ 322 ህንጻዎች እና ቤቶች ባለቤት አልባ መሆናቸውን ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል። ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቤቶች ውስጥ 15 ሺህ 891 ቤቶች የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም። 850 ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4 ሺህ 530ዎቹ ደግሞ ባዶ … [Read more...] about በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ
Archives for January 2021
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠ ቅመው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡ ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ያሳውቃል። ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ … [Read more...] about የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል
በአድዋ ጦርነት ወቅት ለእናት ሀገራቸው ነፃነት የተዋደቁ ፈረሰኞችንና ፈረሶችን ለመዘከር በ1933 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ጥር 23/2013 ይከበራል፡፡ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፈረስ ትርዒት፣ በፓናል ውይይቶችና በእደ ጥበባት ኤግዚቢሽን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘውዲቱ ወርቁ ተናግረዋል፡፡ከ33 በማይበልጡ አባላት እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ እያስተዋወቀ ነው፡፡ በዓሉ የተነቃቃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የጎላ ሚና እያበረከተ ነው ተብሏል፡፡ (አብመድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል
በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ
በጋምቤላ ክልል የኦነግ አባላት ናችሁ በሚል እና ህወሀትን ትረዳላችሁ በሚል የታሰሩ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል የእስረኞች አያያዝ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ሊሻሻል እንደሚገባም አሳስቧል። ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በጋምቤላ ክልል ያለው የእስረኞች አያያዝ እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ በታኅሣሥ ወር በጋምቤላ ከተማ እና በአኝዋህ ዞን በመገኘት፣ በአካባቢው ስላለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ክትትል አድርጎ ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን ገልጿል። ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የክልሉ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች አያያዝና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው። በተለይም በኦነግ … [Read more...] about በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ
“…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ
ጁንታው ትግራይን ለ፴ ዓመታት ያስተዳደረው በሴፍቲ ኔት ነው በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ እንዳልሆነ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬም ከእውነት የራቀ ነው አሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ። የፌዴራል መንግሥት በክልሉ የተጠናከረ ሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል። “ድጋፉ እየቀረበ አይደለም” በሚል ሃሰተኛ መረጃ የሚያናፍሱ አካላት የፖለቲካ ትርፍ በመፈለግ የሚፈጽሙት ድርጊት ነው ሲሉም ገልፀዋል። በክልሉ የመብራት፣ የውሃ እና የባንክ አገልግሎቶች በበርካታ አካባቢዎች መጀመራቸውን አንስተው፤ አገልግሎት ባልተጀመረባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ደመወዝ ላልተከፈላቸው የመንግስት ሰራተኞች እንዲከፈላቸው እየተሰራ ነው ብለዋል። ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሙሉ ነጋ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የትግራይ … [Read more...] about “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ
የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ ስምምነትን የክልሎቹ መሪዎች ተፈራርመዋል።በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰላም እና የጋራ የልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል።ጽ/ቤቱ በሁለቱ ክልሎች 12 አዋሳኝ ዞኖችች ላይ ሰላምን በማስፈን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ጥናቶችን ይፋ አድርጓል።በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተዋቀረው የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ በቀጣይ በደቡብ፣ በጋምቤላ እና በቤቢሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለመተግበር ማቀዱን ነው የኦሮሚያ ክልል ያስታወቀው።የኦሮሞ እና ሱማሌ ሕዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት የተሳሰሩ እና ከ 1 ሺህ 872 ኪ.ሜ በላይ ወሰን የሚጋሩ … [Read more...] about የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በሰፊው ታስቦ እንደሚውል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል።125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።በዓሉ ሲከበር በወረዳዎች በመሰረተ ልማት ቦታዎች ላይ የጀግኖች ስም የሚሰየም እንደሚሆንና የመደመር የኪነጥበብ ትርኢቶች እደሚዘጋጁ የምሁራንና የህዝብ የውይይት መድረኮችም እንደሚካሄዱአድዋን ለአባይ በሚል መሪ ሀሳብም የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳልም ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሰው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ወቅት ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት አከባበር መለያ አርማ (Logo) ይፋ አድርጓል፡፡የአርማው መግለጫ፦- ጋሻ ጎራዴና ጦር፦ አባቶቻችን ጠላትን የተዋጉባቸው የጦር መሳሪያዎች፤- … [Read more...] about 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
በመቀሌ ከተማ ከ350 ሚሊዮን በላይ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ክምችት እንዳለ የፌደራል መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ። በትግራይ ክልል የመድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ወደ ጤና ተቋማት ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ተነግሯል። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከሆነ በትግራይ ክልል ለ47 ጤና ተቋማት 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ ወደ ክልሉ በመድረስ የማሰራጨት አገልግሎት ማከናወኑን አስታውቋል። ቅርንጫፉ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 የጤና ተቋማት ግብዓቶቹን በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን በተለይም በመቀሌ ለሚገኙ 4 ሆስፒታሎች ለዉቅሮ፣ ሀውዜን፣ አዲግራት፣ አክሱም ቅድሰት ማርያም፣ ኮረምና ሌሎች ሆስፒታሎች መድሃኒቶችን አሰራጭቻለሁ ብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን እና በምዕራብ አንዲሁም በማዕከል በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች የመደበኛ እና የጤና … [Read more...] about በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
ዊንጉ አፍሪካ የተባለው በምስራቅ አፍሪካ በመረጃ ማዕከልነት ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው ድርጅት አዲስ አበባ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ውስጥ 15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያለው የመረጃ ማዕከል (ዳታ ሴንተር - Ethiopia’s first-ever Carrier-Neutral Hyperscale Data Center Park) ሊገነባ ነው።ዊንጉ አፍሪካ በተሰኘ ድርጅት የሚገነባው ማዕከሉ በቀጣይም ድርጅቱ ሁለተኛ ፕሮጀክቱን ከአዳማ ከተማ በ96 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ለመገንባት ዕቅድ እንዳለውም ተነግሯል፡፡የመረጃ ማዕከላቱ ግንባታ በፓን አፍሪካ ፕሮጀክት ስር የታቀፈው ዕቅድ አንዱ አካል ነው የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል በጂቡቲ እና በናይሮቢ ከተማዎች በተመሳሳይ ስራ ላይ ተሰማርቶ ስራዎችን የሰራ ቆይቷል ተብሏል። (Extensia- ENA) … [Read more...] about ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ድሮኖችን ለማምረት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ (ምንጭ Tikvah) … [Read more...] about ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው