ታላቁ መጽሐፍ የተጻፈበትን ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” ተጻፈ ይላል። በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ጊዜያት አሳልፈናል። በሥልጣን የተቀመጠ የሚወርድ እስከማይመስለውና ሰብዓዊነቱን እስኪዘነጋ ድረስ ሕዝብን ሲበድል ይኖራል። የሕይወቱ መጽሐፍ ሲጠናቀቅ ይሰናበታል። ስንብቱ ግን በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ሲሆን መመልከቱ በየዘመናቱ የመሰከርነው ሐቅ ነው። ንጉሡ በደርግ ሲተኩ፤ ደርግ “ለለውጥ ባጎፈረው” ህወሓት ሲተካ፤ አሁን ደግሞ አይደረስብንም፣ አንበገርም፣ እንደ ደርግ አንሆንም፣ ዓቅምም፣ ገንዘብም፣ ሁሉም ነገር አለን ሲል የነበረው በረኸኛው የወንበዴ ጥርቅም ከየጉድጓዱና ሰርጡ እንደ አውሬ … [Read more...] about ለትምህርት እንዲሆነን
Archives for January 2021
“ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
አባይ ወልዱ እና አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል፤ አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበረ አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ ዕቁባይ በርሄ የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች ንጋቱ አንገሶም አምደማርያም ተሰማ እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ … [Read more...] about “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 4 የቡድኑ አባላት ደግሞ እርምጃም ተወስዶባቸዋል። የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ብሎ የገለፀውን የጁንታው አፈቀላጤ ጨምሮ 4 ከፍተኛ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ በርካቶች ሲደመሰሱ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህም መሰረት፣ ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) 1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ 2. ዘርአይ አስገዶም … [Read more...] about የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ